Get Mystery Box with random crypto!

ኢዜማ ፓርቲ ከመንግስት ጋር በመሰራቱ የጣሰው ምንም አይነት የፓርቲ መርህ እንደሌለ ገለጸ፡፡ በቅር | AHADU RADIO FM 94.3

ኢዜማ ፓርቲ ከመንግስት ጋር በመሰራቱ የጣሰው ምንም አይነት የፓርቲ መርህ እንደሌለ ገለጸ፡፡
በቅርቡ የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ከፓርቲው የለቀቁ አመራሮች እና አባላት ፓርቲው ከመንግስት ጋር በጋራ እየሰራበት ያለዉ ሂደት ከመርህ አንጻር ተገቢ እንዳልሆነ ማንሳታቸው ይታወሳል፡፡
ጉዳዩን አስመልክቶ ከአሃዱ መድረክ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ የብሄራዊ ስራ አስፈጻሚ አባል እና የሴቶች መምሪያ ሃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ግርማ ፓርቲው ከመንግስት ጋር በትብብር በመስራቱ ምንም አይነት የፓርቲ መርህ ጥሰት እንዳልፈጸመ አስታውሰው ከመርህ ጥሰት አንጻር የተነሱት ጉዳዮች ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው ብለዋል፡፡
አክለውም ፓርቲው ከመንግስት ጋር በጋራ ለመሰራት ሲወስን ጠቅላላ ጉባኤው በአብላጫ ድምጽ ተስማምቶበት እንደሆነ ገልጸው ከዛ ባለፈ በሃገሪቱ በአጠቃላይ መንግስት ፍጽሟቸዋል ብሎ ፓርቲው ያመነባቸውን ስህተቶች በሙሉ ያላወገዘበት ወቅት እንደሌለም ተናግረዋል፡፡
አክለዉም ከመንግስት ጋር በጋራ መስራት ማለት መንግስትን መደገፍ ማለት እንዳልሆነም አጽእኖት ሰጥተዉበታል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24