Get Mystery Box with random crypto!

ከአዲስ አበባና ኦሮሚያ ልዩ ዞን ቤታቸዉ የፈረሰባቸዉ ዜጎች ለደብረ ብርሀን ከንቲባ ፅፈት ቤት የድ | AHADU RADIO FM 94.3

ከአዲስ አበባና ኦሮሚያ ልዩ ዞን ቤታቸዉ የፈረሰባቸዉ ዜጎች ለደብረ ብርሀን ከንቲባ ፅፈት ቤት የድጋፍ ይደረግልን ጥያቄ እያቀረቡ ነው፡፡
በአዲስ አበባና በዙሪያዋ አንዳንድ አካባቢዎች ህገ ወጥ ቤት ግንባታ በሚል የቤት ፈረሳ እየተካሄደ ነዉ፡፡
በዚሁ ቤት ፈረሳ ሳቢያ ዜጎች ወደተለያዩ አካባቢዎች እየፈለሱ ይገኛል ከነዚህም መካከል ቁጥራቸዉ በትክክል ያልታወቀ ዜጎች መግባታቸዉን የደብረ ብርሀን ከተማ አስተዳደር የስነ ህዝብ ባለሙያ እና አስተባባሪዉ አቶ አንተነህ ገብረ እግዚአብሄር ተናግረዋል፡፡
ቤታቸዉ ፈርሶ ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ ከገቡት ዉስጥ በአባወራ ደረጃ ብቻ ከ1 ሽህ በላይ ዜጎች ለደብረ ብርሀን ከንቲባ ፅፈት ቤት የቦታና ሌሎች አስቸኳይ ድጋፍ ይደረግልን ጥያቄ ማቅረባቸዉ ለአሀዱ ገልፀዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24