Get Mystery Box with random crypto!

በታይላንድ ሁለት ዋና ዋና ተቀናቃኝ ፓርቲዎች የጥምር መንግስት ለመመስረት ተስማምተዋል ተባለ፡፡ | AHADU RADIO FM 94.3

በታይላንድ ሁለት ዋና ዋና ተቀናቃኝ ፓርቲዎች የጥምር መንግስት ለመመስረት ተስማምተዋል ተባለ፡፡

የዴሞክራሲ ስርዓት አቀንቃኝ ናቸው የተባሉት ሁለቱ ፓርቲዎች ለአስርት አመታት በጦር ሰራዊቱና በዘውድ አገዛዝ ፖለቲካ ስርዓት ስር የነበረችውን ሀገር አስገራሚ ነው በተባለ የምርጫ ውጤት በማሸነፍ የጥምር መንግስቱን ለማቋቋም ነዉ የተስማሙት ተብሏል፡፡
ሰኞ እለት ጠዋት በተደረገው የአጠቃላይ ድምጽ ቆጠራ ሙቭ ፎር ዋርድ የተባለው ፓርቲ መቶ ሀምሳ አንድ መቀመጫ ማግኘቱን ሲያረጋግጥ ተቀናቃኙ ፔ ሁ ታይ ፓርቲ ደግሞ አንድ መቶ አርባ አንድ መቀመጫዎችን አግኝቷል ነው የተባለው፡፡
የሙቭ ፎር ዋርድ ፓርቲ መሪ የታይላንድ ህዝብ ፍላጎቱን በምርጫው አሳውቋል እኔም የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ለመሆን ዝግጁ ነኝ ማለታቸዉ ተሰምቷል፡፡
ዘገባው፡-የዩፒ አይ ነው
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24