Get Mystery Box with random crypto!

በጦርነት እና ግጭቶች ምክንያት ንብረት የወደመባቸው ተቋማት ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ እና የባንክ | AHADU RADIO FM 94.3

በጦርነት እና ግጭቶች ምክንያት ንብረት የወደመባቸው ተቋማት ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ እና የባንክ ብድር ክፍያ እንዲራዘም ቢወሰንም ተግባራዊ ሊሆን እንዳልቻለ ተገለጸ፡፡

ባለፉት ጥቂት አመታት አገራችን ውስጥ በነበረው ተከታታይ ጦርነት እና ግጭቶች ምክንያት ንብረት የወደመባቸው ተቋማት መልሶ ለመቋቋም የሚያስፈልጋቸውን ቁሳቁስ ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ በሚንስቴሮች ምክር ቤት ቢወሰንም እስካሁን ተግባራዊ አለመደረጉን የኢትዮጵያ አሰሪዎች ኮንፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ኢንጂነር ጌታሁን ሁሴን ገልጸዋል፡፡

የሚንስቴሮች ምክር ቤት በ89 ኛው ጉባኤው ተቋማቱ ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ ከመወሰኑ በተጨማሪም ከባንክ የወሰዱትን ገንዘብ የሚከፍሉበት ጊዜ እንዲራዘምላቸው እንዲሁም የግብር ቅነሳ እንዲደረግላቸው ውሳኔ እንዳሳለፈ አስታውሰዉ ዉሳኔዉ አለመተግበሩ ግን ተቋማቱ ዘርፈ ብዙ ለሆኑ ችግሮች ተጋላጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ብለዋል፡፡

እነዚህ አምራች ተቋማት ከፍተኛ ቁጥር ላላቸው ዜጎች የስራ እድል የፈጠሩ እንደመሆኑ መጠን መሰል በህግ የተፈቀደላቸውን አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸው ከስራው እንዲወጡ ከማድረጉ በተጨማሪም ሌሎች የውጪ ባለሃብቶች ወደ አገር ውስጥ ገብተው የመስራት ፍላጎት እዳይኖራቸው ያደርጋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም የሚንስቴሮች ምክር ቤት ውሳኔ ወደ ገንዘብ ሚንስቴር፣ ቀጥሎም ወደ ባንኮች የወረደ ቢሆንም ተግባራዊ ሊያደርጉ አለመቻላቸውን አስታውቀዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24