Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የሰራተኞች ደሞዝ የሚወስነው የደሞዝ ቦርድ ባለመቋቋሙ ምክንያት እስካሁን የአገራ | AHADU RADIO FM 94.3

በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የሰራተኞች ደሞዝ የሚወስነው የደሞዝ ቦርድ ባለመቋቋሙ ምክንያት እስካሁን የአገራችንን ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል መወሰን እንዳይቻል ማደረጉ ተገለጸ፡፡

በአገራችን የሰራተኞችን ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል አለመኖሩን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች በሰሩት ልክ እንዳያገኙ እና በተገቢው መንገድ ለመኖር ስለሚያቅታቸዉ ስደትን የመጨረሻ ምርጫቸዉ እንዲያደርጉ ይገደዳሉ፡፡
ይህንን ተከትሎም በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የሰራተኞች ደሞዝ ወለል የሚወስን የደሞዝ ቦርድ እንዲቋቋም በ2011 ዓ.ም በወጣው አሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ላይ የተወሰነ ቢሆንም ቦርዱ እስካሁን እንዳልተቋቋም የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለአሀዱ ገልፀዋል፡፡

የደሞዝ ቦርዱን እንዲያቋቁም ስልጣን የተሰጠው የሚንስቴሮች ምክር ቤት እንደሆነ ገልጸው በዚህም ምክንያት እስካሁን ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል ለመወሰን ሳይቻል መቆየቱን አስታውቀዋል፡፡
አያዘውም በአገራችን ዝቅተኛ ደሞዝ ከሚከፍሉ ተቋማት ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዙት ከፍተኛ የደሞዝ ክፍያ ከሚከፈልባቸው አገራት የመጡ የውጪ ባለሃብቶች እንደሆኑ ገልጸው በተቻለው ፍጥነት ቦርዱ እንዲቋቋም ማድረግ እና ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል መወሰን እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24