Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ለነዳጅ ግዢ በዓመት የምታወጣውን ከፍተኛ ወጪ ለመቀነስ የነዳጅ ፍጆታ ያላቸውን ተሽከርካሪ | AHADU RADIO FM 94.3

ኢትዮጵያ ለነዳጅ ግዢ በዓመት የምታወጣውን ከፍተኛ ወጪ ለመቀነስ የነዳጅ ፍጆታ ያላቸውን ተሽከርካሪዎች በሂደት ከአገልግሎት ውጪ ማድረግ ይገባል ተባለ፡፡

ኢትዮጵያ ለነዳጅ ግዢ የምታወጣውን ከፍተኛ ገንዘብ ለመቀነስ የነዳጅ ፍጆታ ያላቸውን ተሽከርካሪዎች በነዳጅ ቆጣቢ ተሽከርካሪዎች መተካት ያስፈልጋል ሲሉ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የህዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ አለማየሁ ጸጋዬ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በዓመት ከ4 ቢሊየን ዶላር በላይ ለነዳጅ ግዢ እንደምታወጣ ገልጸው ነዳጅ አስፈላጊ ምርት በመሆኑ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንደሚገባ ነው ያነሱት፡፡ ይህን ከፍተኛ ወጪ ለመቀነስም የነዳጅ አጠቃቀማችንን ማስተካከል አለብን ብለዋል፡፡

ነዳጅ ለመቆጠብም አንዱ ሊታሰብበት የሚገባው መፍትሄ ከፍተኛ የነዳጅ ፍጆታ ያላቸውን ተሽከርካሪዎች በጊዜ ሂደት ወደ ነዳጅ ቆጣቢ ተሽከርካሪዎች መቀየር ነው ብለዋል፡፡ የሚመለከታቸው አካላትም በፖሊሲ ደረጃ አዘጋጅተው ተፈጻሚ ማድረግ አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል፡፡ ቀደም ሲል የነበረው ተሰብሳቢ ገንዘብ በየጊዜው በሚደረግ የዋጋ ክለሳ ተመላሽ ስለማይደረግ መንግስት በኪሳራ ለመሸጥ ተገዶ እንደነበር አንስተው ይህም ሀገሪቷን ከፍተኛ ዕዳ ላይ መጣሉንም አክለው ገልጸዋል፡፡

የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት መንግስት ተግባራዊ ባደረገው የነዳጅ ዋጋ ማረጋጊያ ፈንድ እስካሁን ኢትዮጵያ የ194 ቢሊየን ብር ዕዳ እንዳለባት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር መግለጹ አይዘነጋም፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en