Get Mystery Box with random crypto!

በዓላትና ስብሰባዎችን ምክንያት በማድረግ ያለፈቃዳቸው ከጎዳና ላይ እንዲነሱ የሚደረጉ ዜጎች እንዳሉ | AHADU RADIO FM 94.3

በዓላትና ስብሰባዎችን ምክንያት በማድረግ ያለፈቃዳቸው ከጎዳና ላይ እንዲነሱ የሚደረጉ ዜጎች እንዳሉ ኢሰመኮ ባወጣው ሪፖርት ቢገልጽም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ግን ጉዳዩን አስተባብሏል፡፡

ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ዜጎችን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ክትትል እና ሰፊ ጥናት መደረጉን የተናገሩት የኢትዮጲያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የህግና ፖሊሲ ስራ ክፍል ዳይሬክተር ታሪኳ ጌታቸው ናቸው፡፡ የኮሚሽኑ የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት በዓላትና ስብሰባዎችን ምክንያት በማድረግ ከጎዳና ላይ እንዲነሱ የሚደረጉ ዜጎች እንዳሉ መግለጻቸውም ይታወሳል፡፡

አሀዱም ስለጉዳዩ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህገወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል እና የተመላሽ ዜጎች ድጋፍ እና ክትትል መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ደረጄ ተግይበሉን ጠይቋል፡፡
በምላሻቸውም የሚወጡ ሪፖርቶች በማስረጃ እና መረጃ ላይ የተደገፉ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እንዲህ አይነት መረጃ አለኝ ካለ ለሚመለከተው የህግ አካል ማቅረብ ነበረበት ያሉት አቶ ደረጄ፤ የተለያዩ ስብሰባዎችን እና በዓላትን ምክንያት በማድረግ ከጎዳና ላይ የሚነሱ ዜጎች የሉም ሲሉም ገልጸዋል፡፡

መልሶ ለማቋቋም ሲባል ብቻ ዜጎች ከጎዳና ላይ ይነሳሉ እንጂ ስብሰባዎችን እና በዓላትን ምክንያት በማድረግ አይደለም ብለዋል፡፡ ከጎዳና የሚነሱ ዜጎች ወደ ማገገሚያ ማዕከላት ሲገቡም ተገቢው ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ እና የተቋማትን ተናቦ መስራት እንደሚጠይቅም ተመላክቷል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio