Get Mystery Box with random crypto!

አሁን ባለው ወቅታዊ የጸጥታ ስጋት ምክንያት ለቀድሞ የአማራ ልዩ ሃይል አባላት ለወራት ያልተከፈለ | AHADU RADIO FM 94.3

አሁን ባለው ወቅታዊ የጸጥታ ስጋት ምክንያት ለቀድሞ የአማራ ልዩ ሃይል አባላት ለወራት ያልተከፈለ ደሞዝ በወቅቱ መክፈል እንዳልተቻለ ተገለጸ፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጉዳት ደርሶባቸው በአዲስ አበባ ለሚገኙ የቀድሞ የአማራ ልዩ ሃይል የጦር ቁስለኞች ለወራት ያልተከፈላቸውን ደሞዝ ማድረስ እንዳልተቻለ የገለጹት በቀድሞ የአማራ ልዩ ሃይል የጤና መምሪያ ሰው ሃብት አስተዳደር ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ሽታውዓለም አሰጋ ናቸው፡፡

ከባህር ዳር እስከ አዲስ አበባ የትራንስፖርት በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ምክንያት የፋይናንስ ባለሙያዎችን ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ በመላክ ለአባላቱ ደሞዝ መክፈል አልተቻለም ብለዋል፡፡
ለአንዳንድ አባላት በመተማመኛ እና በሂሳብ ቁጥራቸው ለወራት ያልገባላቸውን ደሞዝ መክፈል መቻሉን ገልጸው ተንቀሳቅሰው የሂሳብ ደብተር መክፈት ላልቻሉ ቁስለኞች ግን የፋይናንስ አባላትን በአየር ትራንስፖርት ወደ አዲስ አበባ በመላክ ገንዘባቸውን ለማድረስ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ቁስለኞቹ በአዲስ አበባ የተለያዩ ካምፖች በቂ የህክምና አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውንም ጠቅሰው ነገር ግን ለቀላል የህክምና አገልግሎቶች ተደጋጋሚ ቀጠሮ የመስጠት ሁኔታ እንደሚስተዋልም ገልጸዋል፡፡ ይህንንም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ችግሩ እየተቀረፈ እንዳለም አንስተዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24