Get Mystery Box with random crypto!

ኢራን ብዙ መጠን ያለው የኑክሌር ቦምብ ልትሰራ ትችላለች ስትል እስራኤል አስጠንቅቃለች፡፡ የእስራ | AHADU RADIO FM 94.3

ኢራን ብዙ መጠን ያለው የኑክሌር ቦምብ ልትሰራ ትችላለች ስትል እስራኤል አስጠንቅቃለች፡፡

የእስራኤል የመከላከያ ሚንስትር ዮኦቭ ጋላንት በሰጡት ሰፊ ማብራሪያ ኢራን ባለችበት የአሁኑ ደረጃዋ አምስት የኑክሌር ቦምብ ለመስራት ከበቂ በላይ ዝግጅት አድርጋለች ሲሉ ነው ያስጠነቀቁት፡፡
የእስራኤሉ የመከላከያ ሚንስትር ግሪክ ውስጥ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ኢራን አምስት የኑክሌር ቦምብ ለመስራት የሚያስችላትን በሃያ በመቶና በስልሳ በመቶ የበለፀገ ዩራኒየም እንዳላት ደርሰንበታል ነው ያሉት፡፡

ጋላንት አክለውም ኢራን የዩራኒየም ማበልጸግ ስራዋን ዘጠና በመቶ ካደረሰች የመካከለኛው ምስራቅ ቀጣናም ይሁን መላዋ ዓለም ወደ ከፋ ጥፋት ማምራታቸው ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

ዘገባው፡-የሚይል ኢስት ሞኒተር ነው፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24