Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Freeseminar
Cloudbridge
Traininginstitute
Cryptocurrency
Аирдроп
Tikvahtechteam
Techdailly
Attention
Cbdc
Cryptocurrencies
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.51K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-06-15 22:32:20
በመዲናዋ ዋና መንገዶች ላይ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ክፍት እንዲሆኑ ተወሰነ።

የኮሪደር ልማት በሚከናወንባቸው አካባቢዎችና በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የሚገኙ የንግድና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከተለመደው የሥራ ሠዓት በተጨማሪ ቢያንስ እስከ ምሽቱ 3 ሰአት ድረስ ክፍት በማድረግ የንግድና የአገልግሎት ስራዎች እንዲካሄዱ መወሰኑ ተገልጿል።

ከአዲስ አበባ ከተማአስተዳደር ንግድ ቢሮ በትላንትናው ዕለት (ሰኔ 7፣ 2016 ዓ.ም) ተፈርሞ የወጣውና ለአሥራ አንዱም ክፍለ ከተሞች የተጻፈው ደብዳቤ ክፍለ-ከተሞች ይህንኑ ውሳኔ ለንግዱ ማህበረሰብ በአግባቡ እንዲያስገነዝቡ ያዛል።

@TikvahethMagazine
22.8K viewsedited  19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-15 15:08:22
ኢትዮጵያ የዲጂታል ምንዛሬ (Digital Currency) እንቅስቃሴ ጅማሮ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትላንት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በኢትዮጵያ የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ምንዛሪ (ሲ.ቢ.ዲ.ሲ) (Central Bank Digital Currency (CBDC) ) ማስተዋወቅ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ የሚያወጣውን ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል።

ይህ አሰራር ማለትም የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ምንዛሪ (CBDC) ከባህላዊ ገንዘብ ጎን ለጎን እየተዘዋወረ ለዲጂታል የኢትዮጵያ ገንዘብ መንገድ ይከፍታል ተብሏል።

  የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ምንዛሪ (ሲ.ቢ.ዲ.ሲ) - Central Bank Digital Currency (CBDC) ምንድነው?

የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ምንዛሪ  (CBDC) በአንድ ሀገር ማዕከላዊ ባንክ የሚሰጥ የዲጂታል ምንዛሪ አይነት ነው። በኢትዮጵያ ስናየው ደግሞ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚሰጥ የዲጂታል ምንዛሪ ማለት ነው።

ይህም እንደ ቢትኮይን ያሉ ክሪፕቶከረንሲዎች (Cryptocurrencies) አይነት ሆኖ ከእነሱ የሚለየው ፣ የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ምንዛሪ (CBDC)ን የሚያዘጋጀው ፣ ሚያወጣው እና የሚቆጣጠረው የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ መሆኑ ነው።

ይህ ማለት የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ የምንዛሬ ዋጋውን እና የተረጋጋ እንቅስቃሴ መኖሩን ያረጋግጣል። የመግዛት አቅሙም በማዕከላዊ ባንክ የተስተካከለ እና ከአገሪቱ የባህላዊ ገንዘብ (የ ኢትዮጵያ ብር) ምንዛሪ ጋር ተመጣጣኝ እንዲሆን ይደረጋል።

በጠቅላላ አገላለጽ የአንድ ሀገር CBDC በዲጂታል መልክ ሆነ እንጂ በመሠረቱ ከ ሀገሪቱ በማዕከላዊ ባንክ የተደገፈ ባህላዊ ገንዘብ (Fiat Currency) ምንዛሬ ጋር እኩል ነው ማለት ይቻላል።

በ ማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ምንዛሪ (CBDC) ዙሪያ የሌሎች ሃገራት ልምድ ምን ይመስላል?

ኢትዮጵያ ይህንን አይነት ሥርዓት ለመሞከር የመጀመሪያዋ ሀገር አይደለችም።  የስኬት ደረጃዎቻቸው ይለያይ እንጂ በተለያዩ ሀገራት ተግባራዊ ሆኗል።

የሌሎች ሀገራት ተሞክሮን በተመለከተ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።

Credit : Shega Media

#TikvahTechTeam #CBDC #Cryptocurrencies

@TikvahethMagazine
27.9K viewsedited  12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-15 14:53:16
#ATTENTION

" በምዕራብ ወለጋ ዞን የወባ በሽታ ተባብሷል " - ነዋሪዎች

" ባለፉት 10 ወራት በዞኑ ደረጃ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ ተይዘዋል " - የምዕራብ ወለጋ ዞን ጤና መምሪያ

በምዕራብ ወለጋ የወባ በሽታ ስርጭት መጨመሩን እና ባለፈው ሳምንት ብቻ በዞኑ 19ሺ ሰዎች በበሽታው ተይዘው 11 ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ።

በዞኑ ቆንዳላ እና ጌንጂ አካባቢዎች የወባ በሽታ ስርጭት መጨመሩን በበሽታው ቤተሰቦቻቸውን የተነጠቁ ነዋሪዎች ተናግረዋል። በዞኑ የወባ በሽታ ዝናብ በመጣሉ ስርጭቱ በጣም እየጨመረ ነው ተብሏል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ባለሙያ ባለፈው ሳምንት ገንጂ ወረዳ ውስጥ በምትገኘው ላሊሳ ዲቤ መንደር ሰባት ሰዎች በወባ በሽታ መሞታቸውን ገልጸዋል።

በዞኑ ገንጂ፣ ቢቂልቱ ኡምባኦ እና ላሊሳ ዲቤ የተባሉ አካባቢዎች በብዛት የተጠቁ መሆናቸውንም አስረድተዋል።

የምዕራብ ወለጋ ዞኑ ጤና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ መስፍን ጣሰው በበኩላቸው ሆስፒታሎች በአሁኑ ጊዜ በቀን ብዙ ሰዎችን እያስተናገዱ እንደሆነ ጠቁመዋል

በዞኑ በሳምንት ከ10ሺ እስከ 20ሺ ሰው በበሽታው እየተያዘ መሆኑንም የገለፁት ኃላፊው ባለፉት 10 ወራት በዞን ደረጃ 5 መቶ 19ሺ የሚደርሱ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸውንም ጨምረው ገልፀዋል።

በእነዚህ አካባቢዎች ለወባ በሽታ ተጋላጭ የሆኑ ነዋሪዎች በበሽታው ምክንያት ስጋት እንዳደረባቸው በመግለፅ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገቢው እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን መረጃ ያሰባሰበው ከአዲስ ስታንዳርድ እና ዶይቼ ቬለ የዜና ምንጮች ነው።

#ምዕራብወለጋ  #ወባ   #ጤና

@TikvahethMagazine
26.3K views11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-15 14:53:01
ታላቅ የዋጋ ቅናሽ ከአያት ሪል ኢስቴት!

እጅግ ከፍተኛ ቅናሽ የተደረገባቸውን የአያት ዘመናዊ አፓርትመንቶች በመሪ እና በአያት አደባባይ (ዞን 2፣ 3 እና 8) ከ72 እስከ 150 ካሬ ስፋት ያላቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች በ79,971 ብር የካሬ ዋጋ በመግዛት ዛሬውኑ የቤት ባለቤት ይሁኑ!

የረጅም ጊዜ የዱቤ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ከፈለጉ የቤቶቹን ዋጋ 60%ቱን ብቻ በ6 ጊዜ ክፍያ በ3 ዓመት ጊዜ ውስጥ ከፍለው ሲያጠናቅቁ ቤትዎን ይረከባሉ ቀሪውን 40% ክፍያ ቤትዎ እየኖሩበት ከ10 እስከ 30 ዓመት በሚደርስ በረጅም ጊዜ የዱቤ አገልግሎት በ9.5% ዝቅተኛ ወለድ መክፈል የሚችሉበት አማራጭ አዘጋጅተንልዎታል!

860 ሺ ብር ብቻ ቅድመ ክፍያ ከፍለው ከአያት ሪል ኢስቴት የዘመናዊ መኖሪያ ቤት ባለቤት ይሁኑ!

የ8 ትርፋማ ኩባንያዎች ባለቤት የሚያደርግዎትንና እስከ 51.38% ዓመታዊ ትርፍ የሚያስገኝልዎትን የአያት አክስዮኖች ፈጥነው በመግዛት ለልጅ ልጅ ልጅ የሚተላለፍ ሀብት ያኑሩ!

ለበለጠ መረጃና የቢሮ ቀጠሮ ለመያዝ:
0911141372/ 0910531565 ይደውሉ!
Telegram: https://t.me/Tese_Apartment
20.3K views11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-14 18:31:14
በአዲስ አበባ የ2017 የትምህርት ዘመን የትምህርት ካላንደር ይፋ ሆነ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2017 የትምህርት ዘመን በከተማ አስተዳደሩ ስር ባሉ የመንግስት፣ የግልና በሌሎች የተያዙ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛ ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ወጥነት ያለው የትምህርት የጊዜ ሰሌዳ /የትምህርት ካላንደር/ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

በዚህም፦

- ከሰኔ 24 እስከ 30/2016 ዓ.ም ድረስ የነባር ተማሪዎች ምዝገባ እና የመጽሐፍት ስርጭት

- ነሃሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም  ድረስ መምህራን በትምህርት ቤታቸው ተገኝተው ሪፖርት በማድረግ አጠቃላይ የመምህራን ጉባኤ ይደረጋል

- ከነሃሴ 21-30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የ7ተኛ እና የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ምዝገባ ይከናወናል

- ጳጉሜ 1 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን ድረስ አስፈላጊውን መረጃ አሟልተው የሚመጡ አዲስ የተማሪዎች ምዝገባ ይከናወናል

- መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም  ለተማሪዎች ስለ ት/ቤቱ ህገደንብና ተያያዥ ጉዳይ ላይ ገለጻ ይሰጣል

- መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም   መደበኛ ትምህርት ይጀምራል

- መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም ትምህርት በሬዲዮ ስርጭት ይጀምራል

- ህዳር 16-18 ቀን 2017 ዓ.ም አንደኛ ወሰነ ትምህርት አጋማሽ ፈተና ይሰጣል

- ከጥር 7-9 ቀን 2017 ዓ.ም ለ6ኛ ፣ ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ይሰጣል

- ከጥር 19-23 ቀን 2017 ዓ.ም አንደኛ ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና ይሰጣል

- ከጥር 26-29 ቀን 2017 ዓ.ም መምህራን ፈተና የሚያርሙበት እና ውጤት ማጠናቀሪያ ሳምንት

- ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም መምህራን የተማሪዎችን የፈተና ውጤት የሚያሳውቁበት ይሆናል

- የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም  የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት ይጀምራል

- ሚያዚያ 6-8 ቀን 2017 ዓ.ም  የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት አጋማሽ ፈተና ይሰጣል

- ግንቦት 19-22 ቀን 2017 ለ6ኛ፣ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ይሰጣል

- ከሰኔ 3-4 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ይሰጣል

- ከሰኔ 9-11 ቀን 2017 ዓ.ም  ድረስ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ይሰጣል

- ከሰኔ 16-20 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ሁለተኛ  ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና ይሰጣል

- ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ መምህራን የተማሪዎችን የፈተና ውጤት የሚያሳውቁበት ይሆናል

- ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም  የውጤት መግለጫ ካርድ በመስጠት የዓመቱ ትምህርት ይጠናቀቃል።

ቢሮው በ1ኛ ወሰነ ትምህርት 103 የትምህርት ቀናት ሲኖሩ በ2ኛ ወሰነ ትምህርት 101 ቀናት በጠቅላላው በዓመቱ 204 የትምህርት ቀናት መኖራቸውን ጠቅሷል።

በተጨማሪም ትምህርት ቢሮ የትምህርት ካላንደሩና ካላሻሻለ በስተቀር ማንኛውም ትምህርት ቤት ከካላንደሩ ውጪ የትምህርትን ስራ ማከናወን የተከለከለ መሆኑን አሳስቧል።

@TikvahethMagazine
27.5K viewsedited  15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-14 16:27:51
"ገንዘብ ለማግኘት ይጫወቱ" (play-to-win)  ጌሞች  መብዛት

በማዝናናት እና በገንዘብ ለማግኘት መካከል ያለውን መስመር የሚያደበዝዙ አዳዲስ ጌሞች በብዛት እየታዩ ነው።

እንደ Notcoin፣ TapSwap እና Hamster Kombat ያሉ ጌሞች ተጫዋቾች በመጫወት የዲጂታል-ገንዘብ (Cryptocurrency) ሊያገኙ በሚችሉበት በ "ገንዘብ ለማግኘት ይጫወቱ" (play-to-win) ሞዴላቸው በአለም አቀፍ ደረጃ መነጋገሪያ እየሆኑ ነው።

ለምሳሌ ብናነሳው Hamster Kombat 3 ወር ባልሞላ ጊዜ ከ 110 ሚሊዮን በላይ ተጫዋቾች ማግኘት ችሏል።  ነገር ግን ለእዚህ ስኬታቸው ዋናውን ሚና የሚጫወተው ኤርድሮፕ (Airdrop) በመባል የሚታወቀው ፅንሰ-ሀሳብ ነው።

ኤርድሮፕስ (Airdrops) - ነፃ ክሪፕቶ (ገንዘብ) ወይስ አዲስ የማርኬቲንግ ዘዴ?

ከ’ኤርድሮፕስ' (Airdrops) በስተጀርባ ያለው መሰረታዊ ፅንሰ ሃሳብ ሰዎች ጨዋታ በመጫወት ብቻ በቀላሉ ነፃ ክሪፕቶከረንሲ (ዲጂታል ገንዘብ) እንዲቀበሉ የሚያደርግ ነው።

እስካሁን ባለው ይህ ፅንሰ ሃሳብ የክሪፕቶከረንሲ (ዲጂታል ገንዘብ) ባለቤቶች ተደራሽነታቸውን ለማስፋትና ተዓማኒነትን በማግኘት ወደ ገቢያው ለመግባት ይጠቀሙበት የነበረ ነው።

አዲስ የተፈጠሩ ክሪፕቶከረንሲዎች (ዲጂታል ገንዘባቸውን) በቀጥታ በነፃ ለተጠቃሚ በዚህ መንገድ ያሰራጫሉ። ብዙውን ጊዜ ግን ዝም ብለው ሳይሆን የሚያሰራጩት ቀላል ተግባራትን ማለትም፣ ጨዋታዎችን በማጫወት ወይም ኦንላይን ግሩፕ ለመቀላቀል ይሆናል።

አሁን ላይ በቴሌግራም ላይ በመምጣታቸው ስማቸው የገነነው እንደ Notcoin እና Hamster Kombat ያሉ ጨዋታዎች የ ኤርድሮፕን (Airdrops) ፅንሰ ሃሳብ ተጠቅመዋል።

'Notcoin' በይፋ ገበያዎች (Exchanges) ላይ ግብይት ከመጀመሩ በፊት ከ80 ቢሊዮን በላይ ቶከኖችን (ዲጂታል ገንዘብ) በሰፊው አሰራጭቷል።

ይህ ድርጊት ለተጫዋቾች አስደሳች ቢሆንም ይሄ የ ኤርድሮፖ' (Airdrop) ፅንሰ ሃሳብ ግን ለእዚህ ፕሮጀክት የማደግ ዋናውን ሚና ተጫውቷል። በዚህ ፕሮጀክት ዓላማቸውም፡-

መነጋገሪያ መሆን፡ ነፃ crypto (ክሪፕቶ) ትኩረትን ይስባል እና በጨዋታው እና በተጨዋቾች ዙሪያ ደስታን ይፈጥራል።

ማህበረሰብ መገንባት፡  ኤርድሮፕ (Airdrops) ተጫዋቾች የኦንላይን  እና የማህበራዊ ሚዲያ ቡድኖችን (ማለትም እንደ ቴሌግራም ቡድን እና ቻናል) እንዲቀላቀሉ ያበረታታል፣ ይህም ዲጂታል ማኅበረሰብን (Digital Community) ይገነባል።

የዲጂታል ገንዘብ  ምንዛሬ ልውውጥ ገበያ ላይ የመሳተፍ እድልን ማሳደግ፡ ትልቅ የተጠቃሚ እና ጥሩ ሚንቀሳቅስ ማኅበረሰብ (Active Community) የጌሙን ዲጂታል ገንዘብ የመገበያያ ገበያ ላይ የመውጣት እድሉን ይጨምራሉ።

የክሪፕቶ ምንዛሬ ልውውጥ ገበያ ማለት ተጠቃሚዎች cryptocurrency መግዛት፣መሸጥ እና መገበያየት የሚችሉባቸው የኦንላይን መድረኮች ናቸው።

እነዚህ መድረኮች ለነዚህ  "ገንዘብ ለማግኘት ይጫወቱ" (play-to-win) ለሚሉት ጨዋታዎች ዘላቂነት እንዲኖራቸው ወሳኝ ናቸው።

የሚሸልሙትን ዲጂታል ገንዘብ በነዚህ የሽያጭ መድረኮች ላይ እንዲዘረዝሩ በማድረግ፣ ለጌሙ እና ለዚህ ዲጂታል ገንዘብ ፈጣሪ ደርጅት እና ለተጫዋቾቹ ከጌሙ ጋር የተሰራውን ዲጂታል ገንዘብ ወደ እውቅና ወዳላቸው (እንደ ቢትኮይን ያሉ) ዲጂታል ገንዘብ (Cryptocurrency) ወይም ወደ ባህላዊ ገንዘብ (ዶላር፣ ዩሮ እና ብር የመሳሰሉት) እንዲቀይሩ ያስችላቸዋል።

#ጥንቃቄ፡ ሁሉም ኤርድሮፕስ (airdrops) አንድ አይነት አይደሉም!

ኤርድሮፕስ (airdrops) አዳዲስ ጨዋታዎችን እና ሽልማቶችን የሚያገኙበት መንገድ ሊሆን ቢችልም ግን በጥንቃቄ ማስተዋል ግን ያስፈልጋል። ምክንያቱም፤ ትክክለኛ ዋጋ ላይኖራቸው ይችላል፣ ተሳክቶላቸው የዲጂታል ገንዘብ ምንዛሬ ልውውጥ ገበያ ውስጥ ላይገቡ እና የማጭበርበሪያ መንገዶችም ሊሆኑ ይችላሉ።

"ገንዘብ ለማግኘት ይጫወቱ" (play-to-win) ፅንሰ-ሀሳብ በመሠረቱ የሁለቱም የጨዋታዎችን (Games) እና  ዲጂታል ገንዘብ  (Cryptocurrency) ገጽታ እየለወጠ ነው። 

ነገር ግን፣ ጥንቃቄ በተሞላበት አቀራረብ እና ጨዋታ ላይ ትኩረት በማድረግ፣ እና  ተጫዋቾቹ ከኤርድሮፕስ (airdrops) ጋር ተያይዘው ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶችን እያወቁ እና እየተጠነቀቁ  በእነዚህ ጨዋታዎች ሊዝናኑ ይችላሉ።

#TikvahTechTeam   #TechDailly   #Cryptocurrency    #Airdrop

@TikvahethMagazine
26.7K viewsedited  13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-14 16:26:28
#ጥቆማ

በኢትዮጵያ የመጀመርያው የአቪዬሽን የቴሌቪዥን ዝግጅት፣ ዛሬ ምሽት በ2 ሰዓት በአርትስ ቴሌቪዥን ይቀርባል፡፡ ፕሮግራሙ በ90 ዓመታት የአቪዬሽን ታሪካችን ያልተሰነዱ ታሪኮችን በመሰነድ ለተመልካች ሊያደርስ መሆኑ ነው የተገለጸው።

የፕሮግራሙ ዋና አዘጋጅ እና አቅራቢ ዮናታን መንክር ካሳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጸው ይህ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ያሁኑና መጪው ትውልድ በታሪኮቹ ውስጥ ባሉት ዕሴቶች እንዲማር፣ የመጪውንም ዘመን እንዲሰራበት ለማበረታታት የተዘጋጀ ነው።

@TikvahethMagazine
21.7K viewsedited  13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-14 16:25:49
የኪነ ጥበብና ስነ ጥበብ ፈጠራ ውድድርና ትዕይንት በግዮን ሆቴል

ሀገር አቀፍ የኪነ ጥበብና ስነ ጥበብ ፈጠራ ውድድርና ትዕይንት ከሰኔ 13-15/2016 ዓ.ም በግዮን ሆቴል እንደሚካሄድ የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህ መርኃግብር በሙዚቃ፣ በስዕል እና በፋሽን ዲዛይን ውድድር የሚካሄድ ሆኖ ለአሸናፊዎች ሽልማት እንደሚሠጥና የዕደ ጥበባት ትዕይንትም ለእይታ እንደሚቀርብ ተገልጿል።

@TikvahethMagazine
19.5K viewsedited  13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-14 16:24:09
ታላቅ የዋጋ ቅናሽ ከአያት ሪል ኢስቴት!

በመኖሪያ አፓርትመንቶቻችን ላይ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል!

እጅግ ከፍተኛ ቅናሽ የተደረገባቸውን የአያት ዘመናዊ አፓርትመንቶችን በመሪ እና በአያት አደባባይ አጠገብ (ዞን 2፣ 3 እና 8) ከ72 እስከ 150 ካሬ ስፋት ያላቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች በ79,971 ብር የካሬ ዋጋ በመግዛት ዛሬውኑ የቤት ባለቤት ይሁኑ!

የረጅም ጊዜ የዱቤ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ከፈለጉ የመኖሪያ ቤቶቹን ዋጋ 60%ቱን ብቻ በ6 ጊዜ ክፍያ በ3 ዓመት ጊዜ ውስጥ ከፍለው ሲያጠናቅቁ ቤትዎን ይረከባሉ!

ቀሪውን 40% ክፍያ ቤትዎ እየኖሩበት ከ10 እስከ 30 ዓመት በሚደርስ በረጅም ጊዜ የዱቤ አገልግሎት በ9.5% ዝቅተኛ ወለድ መክፈል የሚችሉበት አማራጭ አዘጋጅተንልዎታል!

860 ሺ ብር ብቻ ቅድመ ክፍያ ከፍለው ከአያት ሪል ኢስቴት የዘመናዊ መኖሪያ ቤት ባለቤት መሆን ይችላሉ!

የ8 ትርፋማ ኩባንያዎች ባለቤት የሚያደርጉትንና እስከ 51.38% ዓመታዊ ትርፍ የሚያስገኙትን የአያት አክስዮኖችንም ፈጥነው በመግዛት ለልጅ ልጅ ልጅ የሚተላለፍ ሀብት ያኑሩ!

ለበለጠ መረጃና የቢሮ ቀጠሮ ለመያዝ:
0911141372/ 0910531565 ይደውሉ!
Telegram: https://t.me/Tese_Apartment
22.0K viewsedited  13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-13 21:12:07
ሶስተኛው ዙር ዳሸን ከፍታ የስራ ፈጠራ ውድድር በተለየ መልኩ ሊጀመር ነው

ዳሽን ባንክ የዳሸን ከፍታ የስራ ፈጠራ ውድድር ለሶስተኛ ጊዜ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሊጀመር መሆኑን ባንኩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ገልጿል።

የዘንድሮው ውድድር በባህር ዳር፣ ደሴ፣ መቀሌ፣ አዳማ፣ ድሬዳዋ፣ ወላይታ፣ ሃዋሳ፣ጅማ እና አዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን በነዚህ ከተሞች በባንኩ ቅርንጫፎች የሰልጣኞች ምዝገባ ከሰኔ 18 እስከ ሰኔ 29-2016 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።

ለተመዘገቡ ሰልጣኞች ስልጠና በነዚህ ከተሞች ተሰጥቶ የፈጠራ መነሻ ሃሳባቸውን በፅሁፍ በባንኩ ቅርንጫፎች በኩል እንዲያቀርቡ ይደረጋል። በኋላም የተመረጡ ተወዳዳሪች ወደ አዲስ አበባ መጥተው ለውድድር ዝግጁ እንደሚሆኑ ተነግሯል።

ባንኩ ውድድሩን ለማካሄድ ከአጋር አካላት ጋር ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን የውድድሩ አሸናፊዎች ከዕውቅና እና ሽልማት በተጨማሪ የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያገኙ እንደሚደረግም ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine
27.5K views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ