Get Mystery Box with random crypto!

ሶስተኛው ዙር ዳሸን ከፍታ የስራ ፈጠራ ውድድር በተለየ መልኩ ሊጀመር ነው | TIKVAH-MAGAZINE

ሶስተኛው ዙር ዳሸን ከፍታ የስራ ፈጠራ ውድድር በተለየ መልኩ ሊጀመር ነው

ዳሽን ባንክ የዳሸን ከፍታ የስራ ፈጠራ ውድድር ለሶስተኛ ጊዜ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሊጀመር መሆኑን ባንኩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ገልጿል።

የዘንድሮው ውድድር በባህር ዳር፣ ደሴ፣ መቀሌ፣ አዳማ፣ ድሬዳዋ፣ ወላይታ፣ ሃዋሳ፣ጅማ እና አዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን በነዚህ ከተሞች በባንኩ ቅርንጫፎች የሰልጣኞች ምዝገባ ከሰኔ 18 እስከ ሰኔ 29-2016 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።

ለተመዘገቡ ሰልጣኞች ስልጠና በነዚህ ከተሞች ተሰጥቶ የፈጠራ መነሻ ሃሳባቸውን በፅሁፍ በባንኩ ቅርንጫፎች በኩል እንዲያቀርቡ ይደረጋል። በኋላም የተመረጡ ተወዳዳሪች ወደ አዲስ አበባ መጥተው ለውድድር ዝግጁ እንደሚሆኑ ተነግሯል።

ባንኩ ውድድሩን ለማካሄድ ከአጋር አካላት ጋር ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን የውድድሩ አሸናፊዎች ከዕውቅና እና ሽልማት በተጨማሪ የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያገኙ እንደሚደረግም ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine