2024-05-08 22:57:30
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር ከዛሬ ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ፣ ናይሮቢና ጅቡቲ እንደሚያቀኑ ተገለጸ። ወደ ናይሮቢ በማቅናት ከኬንያ ባለስልጣናት ጋር በጋራ ቀጠናዊ ተግዳሮቶች ላይ ይመክራሉ።
ልዩ መልዕክተኛ ሀመር በአዲስ አበባ ከአፍሪካ ህብረት፣ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት እና ከትግራይ ጊዚያዊ መስተዳድር ጋር በፕሪቶሪያ የጦርነት ማቋረጥ ስምምነትን አፈፃፀም እና አስቸኳይ ጉዳዮችን በፖለቲካዊ ውይይት መፍታት እና ወደ ግጭት መመለስን በማስወገድ ዙሪያ እንደሚነጋገሩ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዛሬ አስታውቋል።
ልዩ መልዕክተኛ ሀመር በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለማስቆም በሚደረገው ውይይት እና የሰብአዊ መብት ጥሰት ሪፖርቶችን ማጣራት እንዳለበትም እንደሚወያዩ የገለጸው መስሪያ ቤቱ በጅቡቲም፣ ልዩ መል ዕክተኛው ከጅቡቲ መንግስት ባለስልጣናት ጋር በክልላዊ እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ አስታውቋል።
U.S. Embassy Addis Ababa
12.6K views19:57