2024-06-08 13:10:49
የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ የግዜ ገደብ ከተጠናቀቀ ቀናት እያለፉነው።
በአዋጁ የተቐቐመው ኮማንድ ፖስት ስራውን ስለመቀጠሉም ሆነ ስለመቀጠሉ በመንግስት በኩል ምንም የተባለ ነገር የለም። ሲታወጅ እንደተነገረው፣ ቀኑ ሲያበቃም መግለፁ ሕዝብን ማክበር ይሆን ነበር።
በነገራችን ላይ…. ባለፉት አምስት አመታት ብቻ አምስት የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ እና አምስት ኮማንድ ፓሰት አስተናግደናል። በትግራይ፣ በቤን ሻንጉል፣ በጋምቤላ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ታውጆ የመጣ ለውጥ የለም። የአዋጁ ፋይዳ አልተገመገመገም እንጂ በጥቅል ሲታይ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል። ጥቅሙ ሰብአዊ እና ኢኮኖሚያወዊ ቀውስን ማባባስ ከሆነ ግን የኮማንድ ፓስቱ ስራ በደንብ የተሳካ ነበር ማለት ይቻላል።
አቶ አበጀ በለው
11.1K views10:10