Get Mystery Box with random crypto!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ገደብ ዛሬ ያበቃል በአማራ ክልል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ ለስድስት ወራ | Zehabesha

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ገደብ ዛሬ ያበቃል

በአማራ ክልል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ ለስድስት ወራት የታወጀው አስቸኳይ አዋጅ ለአራት ወራት መራዘሙ ይታወሳል። አዋጁ የታቀደለትን ለውጥ ማምጣት ባለመቻሉ ነበር ማራዘም ያስፈለገበት ምክንያት። በአዋጁ የተቋቐመው ኮማንድ ፓስት ለተከሰተው ቀውስ ምን መፍትሄ አስገኘ? የሚለው ጥያቄ ምላሽ ይፈልጋል። ከመፍትሄው ይልቅ ሰብአዊ ቀውስን ማባባሱን በርካቶች ይናገራሉ። በኮማንድ ፖስቱ ስር የሚገኙ የጸጥታ እና ደህንነት አካላት በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተከሰሱ ይገኘሸል። በተለይ ደግሞ ጋዜጠኞች፣ አርቲስቶች እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን ለእስር በመዳረግ እና ከማዋከብ ባሻገር ግጭቱን ሊያስቆሙ አልቻሉም።

ከዚህ ቀደም እንደነበሩት ተመሳሳይ አዋጆች ይኸኛውም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ሊከተል የሚችለውን ቀውስ በውል አላጤነም። በአዋጁ ሳቢያ የተከሰተው ችግር ግጭቱ ካስከተለው ጉዳት የሚተናነስ እንዳልሆነም በስፋት ይነገራል።

አሁንም መፍትሄው ሀገርን በአዋጅ መምራት ሳይሆን ችግርን በንግግር መፍታት ነው። ሁሉም ሐሳቡን ወደ ጠረጴዛ በማምጣት ተነጋግሮ መፍታት የስልጣኔ ማሳያ መሆኑን አንዘንጋ።

ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የላኩልን