2024-06-12 17:06:37
የማይካድራ ሰማዕታት መቼውንምአንረሳቸውም!ጊዜው የሥራም፣የትግልም ነው!!ሀገራችን ኢትዮጵያ በየጊዜው የገጠሟትን ብሔራዊ ፈተናዎችበቀደሙት አርበኞች የከበረ መስዋዕትነት በድልተሻግራቸዋለች፡፡ በረዥሙ የነፃነት ታሪኳ የተለያዩ ወራሪዎች
ፈትነዋታል እንጂ አላንበረከኳትም፡፡ በብርቱ መስዋዕትነትሀገራዊ ህልውናዋን ማስቀጠል ችላለች፡፡ በየዘመናቱ የታሪክ
መታጠፊያ የሆኑ ክስተቶች አጋጥመዋታል፡፡
ለታሪካዊ ጠላቶቿተንበርክካ የማታውቀው ኢትዮጵያ፣ በዘመናት መካከልየሚያጋጥሟትን
የታሪክ መታጠፊያዎች፣ ራሷን እንደንሥርአድሳ፤ ትንሳዔዋን አብስራ አልፋቸዋለች፡፡ ጥቅምት 24ለኢትዮጵያ የታሪክ መታጠፊያ ማዕዘን ነው የምንልበት ዋነኛምክንያት በአንድ በኩል ጠላት ኢትዮጵያን ወደ
ድንጋይ ዘመንለመቀየር ወጥኖት የነበረውን
እኩይ ዓላማ ከሽፎሊያስተባብለው የማይቻለው
የማይካድራ ጥቅምት 30/2013ሰይጣናዊ ማንነቱ ለዓለም የተገለጠበት ሲሆን በሌላ በኩልደግሞ
የሀገረ-መንግሥቱ የመጨረሻ ምሽግ የሆነውመከላከያ ሠራዊታችን በእናት ጡት ነካሽ ባንዳዎችከጀርባው ተወግቶ፣ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት አደጋ ላይበወደቀበት ሁኔታ የሰራዊቱ አባላት በመስዋዕትነታቸው ታሪክየማይሽረው አዲስ የድል ምዕራፍ የከፈቱልን፤ በህልፈታቸውየኢትዮጵያን ህልውና ያፀኑልን በመሆኑ
ጥቅምት 30የማይካድራ ሰማዕታት፣ በጥንተ-ጠላት ሕወሓትየተፈፀመው የሀገር ክህደት፣የክፋቱ ጥግ ማሳያ ናት፡፡ ይሁንእንጂ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር/ትህነግ-ወያኔ/ ከፍጥረቱ ጀምሮ ፀረ-አማራ እና ፀረ-ኢትዮጵያ ሆኖ የተነሳአረመኔ ድርጅት ነው፡፡
ወያኔ፣ በአማራ ደምና ሀብት
‹ታላቋ ትግራይ›ን የመመሥረትዕቅዱን ለማሳካት ሲል፤ አማራን ገድሏል፤ አኮላሽቷል፤ ሀብቱንዘርፏል፤ መሬቱንም ወርሯል፡፡ ለዚህ ምስክር የወልቃይት-ጠገዴየሦስት ዐሥርት ዓመታት መዋቅራዊ ግፍና መከራ ቀዳሚተጠቃሽ ነው፡፡
ባለፉት ሠላሳ ዓመታት ዓለም ጆሮ የነፈገው የዘር ማጥፋትወንጀል በወልቃይት ጠገዴ የአማራ ሕዝብ ላይ ተፈጽሟል፡፡ ምናልባትም በብዙሃኑ ኢትዮጵያውያንና በተወሰኑ የዓለማቀፉማኅበረሰብ አባላት ዘንድ የተሰማው ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የሕግ ማስከበር ዘመቻው ከተጀመረ በኋላ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በማይካድራ የተፈፀመውን የዘር ማጥፋትወንጀል ብቻ ነው፡፡ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ግን ባለፉት ሦስትዐሥርት ዓመታት በርካታ ማይካድራዎችን አይቷል፡፡ በየትኛውምየዓለም ክፍል የተፈጸሙ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች አንዴተጀምረው በተወሰነ የጊዜ ገደብ የተጠናቀቁ ቢሆንም፣ ወልቃይት ጠገዴ ላይ የተፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ግንበዓይነትም ሆነ በድርጊት የተለየ ነው፡፡
የማይካድራን ጭፍጨፋ ስናስብ ጭፍጨፋው የፀረ-አማራትርክት ውጤት ስለመሆኑ ልብ ልንለው ይገባል፡፡ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በማይካድራ ከተማ የተፈፀመው የጅምላጭፍጨፋ በ1968 ዓ.ም ወያኔ ያዘጋጀው አማራን የማጥፋትፍኖተ መርሁ አካል ነው።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ የጥናት ባለሙያዎች ለወራትባደረጉት ጥናት መሠረት በዚህ የጅምላ ጭፍጨፋ 1,644 አማራዎች የጉዳት ሰለባ ሆነዋል። የተገደሉ1,563 ሲሆኑ፤ የአካልጉዳት የደረሰባቸው ደግሞ 81 ናቸው፡፡ በዚህ ጭፍጨፋ የተነሳበርካታ ሕፃናት ያለ ወላጅ ቀርተዋል። የደረሰውን ግፍለማስረዳት ገና ብዙ መጻሕፍት፣ ፊልሞች፣ ዘገባዎችናዶክመንተሪዎች እንደሚያስፈልጉ አያከራክርም፡፡ በዚህ በኩልከፍትሕ ወዳድ ኢትዮጵያዊያንና ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ብዙእንጠብቃለን፡፡ እኛም ለመተባበር ሁልጊዜም በራችን ክፍትነው፡፡
የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የማንነት እና ወሰን ጥያቄ ቀንጠብቆ፤ ሒሳብ ሰርቶ ብቅ ያደረገው የዘር ካርድ ሳይሆን በመራርየፈተና እና የመከራ ወቅት ሳይቀር እስከ ኢያሪኮ ጎልቶ የተሰማእውነተኛ የሕዝብ ድምጽ ነው፡፡ የወልቃይት ጠገዴ አማራሕዝብ ግፈኞች ቀን ሰጣቸው ብሎ ሳይፈራ፤ በጀምላ ተገደልኩብሎ ለነፍሱ እና ለቤተሰቡ ሳይራራ ከሦስት አስርት ዓመታትበላይ በጽናት እና በብርታት ፊት ለፊት እንደተጋፈጣቸው ታሪክህያው ምስክር ነው፡፡ የወልቃይት-ጠገዴ አማራ ሕዝብ ይህንሁሉ ግፍና መከራ ተቀብሎ በከበረ መሥዋዕትነቱ ዛሬ ነጻነቱንአስከብሮ ከአብራኩ በወጡ ልጆቹ እየተመራ ይገኛል፡፡
ስለሆነም
ጊዜው የሥራም፤የትግልም በመሆኑ በዛሬው ዕለትሰኔ
5/2016ዓ.ም የማይካድራ ሰማዕታት መቼውንምአንረሳቸውም!! በሚል መሪ ሃሳብ የሰማዕታቱ ማስታወሻየሚሆን ሃወልት በማይካድራ ከተማ በ3136 ካ.ሜና በ30ሜ ከፍታ ላይ የሚያርፍ ሲሆን የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ሰውምጎንደሬ፤ መሬቱም የአማራ፣ ወሰኑም ተከዜ መሆኑን በታሪክም፣በጂኦግራፊም፣ በሥነ-ህንፃም፣ በወግ፣ በባህሉ፣ በሥነ-ልቦናየተሳሰረ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በግፈኛው ወያኔቡድን ሲደርስበት የነበረውን ግፍና በደል ከወንድም የአማራህዝብና ፍትህ ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጋር በጽናትና በአይበገሬነትየታገለበትን እና የተጎናጸፈውን ነፃነት ትግል በዘላቂነትለትውልዱ ለማስተላለፍ ይረዳ ዘንድ ከታገለበት ዓላማ ጋርየተሳሰረ፣የተሰናሰለና ዘመኑን የዋጀ የአርቴክት ሙያ ተላብሶእንሆ በዛረው ዕለት በይፋ የሰማዕታት የትግል አደራ ሃወልትለማቆም የሚሰራበትን ቦታ ለይተን አስቀምጠናል፡፡
ስለሆነም
የማይካድራ ሰማዕታት መታሰቢያ ሃውልት ሰሪዎችእኛው፣መሀንዲሶቹ ከአብራኩ የወጡ ልጆቹ ፣የፋይናንስ ምንጩእኛውና ፍትህ ወዳድ ኢትዮጵያውያን ነን፡፡ ይህ ሃወልት ሲያልቅየወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ትግል አማራ ነን እንጂ አማራ እንሁንአላልንም የሚለውን ጉልህ ምልክት ሁኖ እንደማሳያየሚያገለግል፣የማይካድራ ሰማዕታት በሰው ልጅ አእምሮና ልብማህተም ሁኖ እንዲኖር ከታገለበት ዓላማ ጋር ተሰናስሎ ከዘመኑየዋጀ የኪነ-ህንፃ ሙያ ተገናዝቦ አምሳል የሆነውን የዳግማዊአያናዝጊ ቤት-ሞሎ ከተማ የሚገኘውን ከታሪካዊ የጎንደር-የፋሲል አብያተ መንግስታት ጋር በታሪክ ተጣጥሞ የሚሰራሃወልት መሆኑን ትልቅ የትግሉ ድልና ስኬት ነው፡፡ ስለሆነም ይህሃወልት ተሰርቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ አስተባባሪዎቹ የወልቃይትጠገዴ አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽና አስጨራሽ ኮሚቴዎችይሆናሉ፡፡
8.5K views14:06