Get Mystery Box with random crypto!

በመጨረሻም ጊዜው የሥራም፣የትግልም መሆኑንላስታውሳችሁ እወዳለሁ፡፡ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ትግል ላ | Zehabesha

በመጨረሻም ጊዜው የሥራም፣የትግልም መሆኑንላስታውሳችሁ እወዳለሁ፡፡ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ትግል ላይነው፡፡ ትግሉ ደግሞ ራስን የመሆን ክቡር የጎንደር-አማራማንነቱን የማጽናት ትግል ነው፡- የራስን ዕድል በራስ የመወሰንትግል፡፡ ወልቃይት ጠገዴ ጎንደር-አማራ ነው! የትግሉ ዓላማ ግንከዚህም ከፍ ያለ ነው፡፡ ትግሉ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራንኮሪደር አስከብሮ የኢትዮጵያን ህልውና የመጠበቅ ሀገራዊትግልም ነው፡፡ ወልቃይት ጠገዴ ለእኛ መሬት ብቻ ሳይሆንማንነታችንም ነው፡፡ ቀየው፣ ወንዙ-ሸንተረሩ፣ ጋራው፣ ዛፉ፣ የእምነት ቦታው፣ መንደሩ፣ ገበያው ወዘተ…ሁሉ ለእኛ ልዩትርጉም አለው፡፡ ልዩ ስሜት ይፈጥርብናል፡፡ ብዙ የትውልዶችትዝታ፣ወግ፣ትውፊትና ልማድ ያቀፈ ባድማችን ነውና በምንምአይለወጥም! የተከዜ አዳኝ ትውልድ ተቀዳሚ ተልዕኮ ይህንንበምንም የማይለወጥ ክቡር የወልቃይት ጠገዴ አማራዊ ማንነትለማስከበር በነጋ-በጠባ በወያኔ ፕሪፖጋንዳ ሳንደናገርና ሳንዘናጋ፣ዛሬ የማይመች ቢሆን ነገ የተመቸ እንዲሆን በጽናትና በትጋትመሥራት፤መታገልና ወደፊት መግፋት እንጂ መሸነፍ፣ተስፋመቁረጥና ደክሞ መቆም አይገባም፣አያስፈልግም፡፡ ከባሕሩ ማዶያለውን ብርቱኳን የምንፈልገው ከሆነ ባሕሩን ዋኝቶ መሻገርያስፈልጋል እንጂ ሌላ ሰው ዋኝቶ እንዲሰጠን ከጠበቅን ከእሱየተረፈውን እና የማይፈልገውን እንደሚወረውርልን ማወቅይገባል፡፡ የምንፈልገው ጉዳይ በራሳችን ዐቅም ለማሳካትእየተጋን የጎደለብንን እየሞላን፣የጎበጠውን እያቃናን መጓዝበእጅጉ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለጥንካሬ የሚበጁ ሁሉንምነገሮች እንደ ስፖንጅ በመምጠጥ ዐቅም አድርጎ በመጠቀም እናአንድነትን ከሚያላሉ ፣ ጽናትን ከሚያዳክሙ ነገሮች በመራቅሕልማችን እውን በማድረግ ባለታሪክ ለመሆን መረባረብያስፈልጋል፡፡ ትግሉ በውስን ጀግኖች ትግልና መስዋዕትነት ብዙርቀት የመጣ ቢሆንም፤ ገና በጣም ብዙ እንደሚቀረው ተገንዝቦበፅናት መታገልና መቆም ይገባል፡፡ ሁሌም ዝግጁ እንሁን!!ለነፃነት የተከፈለውን መስዋዕትነት በላይ የተገኘውን ነፃነትበዘላቂነትና በአስተማማኝ ማጽናት ያክል ከባድ የለምና እንትጋ!እንበርታ! በወጀብና በንፋስ አንወሰድ!ችግሮችን በምክክርእንፍታ!!
አመሰግናለሁ
ማይካድራ ከተማ
ሰኔ 5/2016ዓ.ም
አሸተ ደምለው ተድላ
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ዋና አስተዳዳሪ