2024-05-30 16:52:04
በሚዛን አማን ከተማ ሙዝ ሰርቃ በላች በማለት የሶስት ዓመት ህፃን ማንኪያ በእሳት አግላ ያቃጠለቻት አክስት በቁጥጥር ስር ዋለች
።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሚዛን አማን ከተማ ግንቦት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ላይ የሶስት አመት ህፃን ማንኪያ በእሳት አግላ ጉዳት ያደረሰች አክስት በቁጥጥር ስር መዋሏን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በሚዛን አማን ከተማ አዲስ ከተማ ቀበሌ ኮሰኮል መንደር ቄጪ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ በአደራነት የተቀበለቻትን የሶስት አመት ከስድስት ወር ህፃን ልጅ ሙዝ ስርቃ በላች በማለት የሾርባ ማንኪያ በእሳት አግላ እጇ ላይ ጉዳት ማድረሷን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት እና ኮምኒኬሽን ዳይሬክተር ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ተናግረዋል ።
ፖሊስ የወንጀል ድርጊቱን ለምን እንደፈፀመች ባደረገዉ ማጣራት ሙዝ እየሰረቀች ስላስቸገረች ስርቆቷን ትተዋለች በሚል መሆኑን ለመርማሪ ፖሊስ ቃሏን የሰጠች ሲሆን ጉዳት የደረሰባት ህፃን ህክምና እንድታገኝ ተደርጎ በአሁኑ ሰዓት በፖሊስ እጅ እንደምትገኝ ተገልፆል።
ወንጀሉ በተፈፀመ በ24 ሰዓታት ውስጥ ፖሊስ በደረሰው ማስረጃ ተከሳሿን በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን በአንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ግለሰቧ እንዳልተያዘች የሚሰራጨው መረጃ የተሳሳተ መሆኑ ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ተናግረዋል ።
(ብስራት ሬዲዬና ቴሌቪዥን)
11.4K views13:52