በ13ተኛው "ለዛ ሽልማት" እነማን አሸናፊዎች ሆኑ?
13ኛው የ "ለዛ ሽልማት" ስነ ሥርዓት ትናንት ግንቦት 16 2016 ዓ/ም በሂልተን ተካሄዷል።
በዚህም መሰረት በፊልም እና ትወና ዘርፍ ፦
- የዓመቱ ምርጥ ተዋናይ፦ አርቲስት ግሩም ዘነበ (በዶቃ ፊልም)
- የዓመቱ ምርጥ ፊልም፦ ዶቃ ፊልም
- የዓመቱ ምርጥ ተዋናይት፦ አርቲስት መስከረም አበራ (በ የሱፍ አበባ ፊልም)
- የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፊልም፦ በስንቱ
- የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፊልም ተዋናይ፦ አርቲስት አለማየሁ ታደሰ (በስንቱ)
- የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፊልም ተዋናይት፦ አርቲስት መስከረም አበራ (በስንቱ ) አሸናፊ መሆን ችለዋል።
በሙዚቃ ዘርፍ የዓመቱ የለዛ አሸናፊዎች እነማን ናቸው ?
- የዓመቱ ምርጥ አልበም፦ የግርማ ተፈራ ካሣ " ግን የት ሀገር ?" አልበም
- የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ፦ የድምጻዊት ራሔል ጌቱ "ኢትዮጵያዬ"
- የዓመቱ ምርጥ ነጠላ ዘፈን፦ የድምጻዊ ቴዲ አፍሮ "ናዕት"
- የአልያስ መልካ ሽልማት (ምርጥ አዲስ ድምጻዊ)፦ ወግዳይት (አሳላፊ አልበም)
- የዓመቱ ምርጥ ዘፈን፦ የድምጻዊት ሔዋን ገ/ወልድ "ሼሙና"
የህይወት ዘመን ተሸላሚው ደግሞ አንጋፋው ድምጻዊ ንዋይ ደበበ መሆን ችለዋል።
#LezaAward #Award
@TikvahethMagazine