Get Mystery Box with random crypto!

በኪነ-ጥበብ ሥራዎችና ባለሙያዎች ላይ የሚደረጉ ጫናዎች እንዲቆሙ ተጠየቀ። በኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች | TIKVAH-MAGAZINE

በኪነ-ጥበብ ሥራዎችና ባለሙያዎች ላይ የሚደረጉ ጫናዎች እንዲቆሙ ተጠየቀ።

በኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና የኪነ-ጥበብ መድረኮች ላይ እየደረሱ ያሉ ጫናዎች ከዕለት ዕለት እየበረቱ መምጣታቸው አሳስቦኛል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ያሬድ ሃይለማሪያም “ኪነ-ጥበብን ማፈን የሃሳብ ነፃነትን መጋፋት ስለሆነ ተገቢ ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል" ሲሉ ተናግረዋል።

የኪነ-ጥበብ ዘርፉ ሰፊ የሕግ ጥበቃ ያለው መሆኑን ያነሳው መግለጫው፥ በተለይም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 29 ላይ በግልጽ እንደተደነገገው ጥበብ እንደ አንድ ሃሳብን በነፃነት የመግለጫ መንገድ የህግ ከለላና እውቅና ማግኘቱን ጠቅሷል።

ማዕከሉ በጥር ወር “ቧለቲካ" የተሰኘው የቴአትር መድረክ መከልከሉ፤ በሚያዚያ ወር "እብደት በህብረት" የተሰኘው የመድረክ ተውኔት አዘጋጅና ተዋናይ ባለሙያዎች መታሰራቸውን አንስቷል።

በተጨማሪም፥ "የተለያዩ እንደ ስነ-ፅሁፍ፣ ተውኔት እና የመሳሰሉት ስራዎች የሚቀርቡባቸው የጥበብ መድረኮች የስብሰባ ፍቃድ ያስፈልጋችኋል በሚል መስተጓጎጎላቸውን ተረድተናል" ሲል አንስቷል።

መግለጫው ባስቀመጠው ምክረ ኃሳብም፥ መንግስት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እንድያከብር፤ በዘፈቀደ እንዳይጣስ ጥበቃ እንድያደርግ፤ በሥራቸው ምክንያት የታሰሩ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች እንዲፈቱ ወይም የተፋጠነ ፍትህ እንዲያገኙና የተከለከሉ የኪነ-ጥበብ መድረኮችም በነጻነት እንዲሰሩ ሲል ጠይቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@TikvahethMagazine