Get Mystery Box with random crypto!

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ተጨማሪ የ350 ሚሊዮን ዶላር ብድር ማግኘቱ ተገለጸ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባን | TIKVAH-MAGAZINE

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ተጨማሪ የ350 ሚሊዮን ዶላር ብድር ማግኘቱ ተገለጸ

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ የቴሌኮም መሰረተ ልማትን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ከዓለማቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) የ350 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሊያገኝ እንደሆነ ኢስት አፍሪካ ጋዜጣ ዘግቧል።

ብድሩን ኢትዮጵያ ውስጥ የቴሌኮምንኬሽን ኔትዎርክ እና የሞባይል ገንዘብ የሆነውን የኤምፔሳን አገልግሎት ለማስፋፋት እንደሚጠቀመው ሲገለፅ ይህም በሀገሪቱ የሀገር ውስጥ የቴሌኮም ገበያውን ፉክክር እንደሚያሳድገው ተጠቁሟል።

የግሉን ዘርፍ በፋይናንስ በመደገፍ የሚታወቀው ዓለማቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ከዚህ ቀደም ለሣፋሪኮም ኢትዮጵያ 157.4 ሚሊዮን ዶላር ብድር የሰጠ ሲሆን የኩባንያውን 7.25 በመቶ ድርሻ በ100 ሚሊዮን ዶላር መግዛቱም ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine