Get Mystery Box with random crypto!

'ያለአግባብ ፓምፕ በቆጣሪ ዙሪያ የሚተክሉ ደንበኞች ላይ ውል እስከመሰረዝ እርምጃ ወስዳለሁ' ባለሥ | TIKVAH-MAGAZINE

"ያለአግባብ ፓምፕ በቆጣሪ ዙሪያ የሚተክሉ ደንበኞች ላይ ውል እስከመሰረዝ እርምጃ ወስዳለሁ" ባለሥልጣኑ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ያለ ፍቃድ እና መተከል የሌለበት ቦታ ፓምፕ በሚተክሉ ደንበኞች ላይ ውል እስከመሰረዝ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ፡፡

በቆጣሪ አካባቢ የሚቀጠል ፓምፕ ህገ ወጥ እና ሌሎች ጎረቤቶች ውሃ እንዳያገኙ ምክኒያት ሆኗል ሲልም ነው የገለጸው፡፡

ባለስልጣኑ ከህዝብ በደረሰው ቅሬታ መሰረት በለሚ ኩራ ቅርንጫፍ አማካኝነት በለሚ ኩራ ክ/ከ ወረዳ 10 ሳውዲ ጀርመን አጥር በታች ባሉ ውስን አካባቢ ባደረገው ጥናት 32 ፓምፕ ያለ አግባብ የቀጠሉ ደንበኞች አግኝቷል፡፡

ደንበኞቹም በአስቸኳይ እንዲያስተካክሉ በሰጠው ማስጠንቀቂያ መሰረት 13ቱ ወዲያው ሲያስተካክሉ 19ኙ ማስጠንቀቂያውን ችላ በማለታቸው ቆጣሪያቸው ተነስቶ እና ተቀጥተው ባለስልጣኑ በሚፈቅደው መሰረት መልሰው ቀጥለዋል፡፡

በቀጣይም መሰል ችግር እንዳይፈጠር ክትትል እና ቁጥጥር የሚደረግ በመሆኑ ሁሉም ከዚህ መሰል ድርጊት እንዲቆጠብ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡

@TikvahethMagazine