Get Mystery Box with random crypto!

'ህጋዊውን የኢትዮጆብስ ድረ-ገጽ የሚያስመስል የውሸት ድረ-ገጽ እየተሰራጨ ነው' ኢትዮ ጆብስ የሐ | TIKVAH-MAGAZINE

"ህጋዊውን የኢትዮጆብስ ድረ-ገጽ የሚያስመስል የውሸት ድረ-ገጽ እየተሰራጨ ነው" ኢትዮ ጆብስ

የሐሰተኛ መረጃ አይነቶች ተብለው ከተለዩት ውስጥ አንዱ የውሸት ማንነት(Imposter Content) ነው። ይህም የታዋቂ ሰዎችን ወይም ድርጅቶችን ስም ወይም አርማ በመውሰድ፥ አጭበርብረው በዛ ምንጭ እንደተዘጋጀ ተደርጎ የሚቀርብበት መንገድ ነው።

ይህ አይነቱ ሐሰተኛ መረጃ የሚቀርብበት መንገድ በሀገራችን በብዛት የሚታየው ሀሰተኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች በመክፈት ቢሆንም የተቋማትን ስም እና አገልግሎት በመጠቀም የተከፈቱ ሐሰተኛ ድረገጾችም አሉ።

በዚህ መንገድ ከተከፈቱ ድረገጾች አንዱ የሥራ ማስታወቂያዎችን በማድረስ በሚታወቀው የኢትዮ-ጆብስ ስም እና አገልግሎት የተከፈተው ድረ-ገጽ ይገኝበታል።

ትክክለኛው የኢትዮ ጆብስ ድረ-ገጽ አድራሻ ethiojobs.net ሲሆን ስሙን ተጠቅሞ የተከፈተው ሀሰተኛ ገጽ ደግሞ #ethio_jobs.net.et የሚል የዶሜን ስም ይዟል።

ባለፉት ወራት የዚህ ዌብሳይት የእይታ መጠን #ከ4 አጥፍ በላይ ማደግ ችሏል። ይህም ሰዎች በዚህ ስም (Ethio jobs) ብለው ሲፈልጉ ቀጥታ በፍለጋቸው ወቅት ከሚመጡላቸው ድረገጾች ከትክክለኛው ድረ ገጽ ቀጥሎ በሁለተኛ ላይ ይገኛል።

ከዚህ በተጨማሪም በድረ-ገጹ ላይ በሚለቀቁት ማስታወቂያዎች ይዘታቸው ከትክክለኛው ድረ-ገጽ የሚወሰድ ሲሆን የሥራ ማስታወቂያዎቹን ከፍታችሁ #ApplyNow የሚለው የመጫኛ ምልክት (Button) ሥራውን እንድታመለክቱ አይረዳችሁም።

ይህ ድረ-ገጽ በዋነኝነት በማስታወቂያ የሚገኝ ገቢ ለማግኘት ሲባል የተከፈተ ለመሆኑ በድረ ገጹ ከሚታዩት ማስታወቂያዎች መረዳት ይቻላል።

ኢትዮ ጆብስ ባወጣው የ #FraudAlert "ህጋዊውን የኢትዮጆብስ ድረ-ገጽ የሚያስመስል የውሸት ድረ-ገጽ እየተሰራጨ ነው" ሲል የገለጸ ሲሆን ተጠቃሚዎች ይፋዊ ድረ-ገጹን እና የተረጋገጠ ሊንክ ብቻ እንዲጠቀሙ አሳስቧል።

@TikvahethMagazine