Get Mystery Box with random crypto!

በወጣት ቃልኪዳን ባህሩ ዙሪያ የወጡ መረጃዎች እንዲጣሩ ተጠየቀ በወጣት ቃልኪዳን ባህሩ ላይ በተፈ | TIKVAH-MAGAZINE

በወጣት ቃልኪዳን ባህሩ ዙሪያ የወጡ መረጃዎች እንዲጣሩ ተጠየቀ

በወጣት ቃልኪዳን ባህሩ ላይ በተፈጸመው አስገድዶ መድፈር፣ ዕገታና ጥቃት ዙሪያ የወጡ መረጃዎች እንዲጣሩ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበርና 4 አጋር ድርጅቶች ጠይቀዋል።

ወጣት ቃልኪዳን ባህሩን በተመለከተ በማኅበራዊ ሚዲያዎች መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በፌስቡክ ገጹ ላይ "አንዲት ወጣት እንደተደፈረች ተደርጎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ ነው" ሲል ግንቦት 10 ቀን ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

ፖሊስ በመግለጫው ምን አለ?

- ወጣቷ ሚያዚያ 16 ቀን 2016 ዓ/ም ወጣቷ  በግለሰቦች ከቤት ተወስጄ ተደፈርኩ በማለት ለጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አመልክታለች፤

- ፖሊስ በወቅቱ በፍጥነት በዳግማዊ ምንሊክ ሆስፒታል ምርመራ እንድታገኝ ቢያደርግም ውጤቱ  ምንም አይነት ፆታዊ መደፈር እንዳልደረሰባት የሚያሳይ ነው፤

- ወጣቷ ከዚህ ቀደምም በ2014 ዓ/ም ተመሳሳይ ወንጀል ተፈፅሞብኛል ብላ አራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አመልክታ የነበር ቢሆንም የተደረገው የጤና ምርመራ ምንም አይነት ፆታዊ መደፈር  እንዳልደረሰባት ያሳያል፤

- ወጣቷ ሳትደፈር ተደፈርኩ በማለት ሀሰተኛ ክስ ከማስዝገብ ባሻገር ጉዳዩን በማህበራዊ ሚዲያ እንዲናፈስ ማድረጓ የህግ ተጠያቂነት የሚያከትል ድርጊት ነው ሲል ጠቅሷል።

ማኅበሩ ይህ መረጃ እንደደረሰው ቃልኪዳንን ጠርቶ ከቤተሰቦቿ ጋር ስለጉዳዩ ማውራቱንና በቅድሚያ ከቤተሰቦቿ ጋር ካሉበት የሸራ ቤት ጊዜያዊ መጠለያ እንዲመቻችላቸው ቅድሚያ ሰጥቶ መስራቱን ገልጿል።

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር በመግለጫቸው ምን አለ ?

- የቴሌግራም መልዕክቶችን እንዲሁም ለተጠቂ እናት በስልክ ሲደርሳቸው የነበረው ዛቻና ማስፈራሪያ አስመልክቶ ፖሊስ በምን መንገድ አስፈላጊውን ምርመራ እንዳደረገ ከምርመራው ያገኘውን ውጤት በግልፅ እንዲያሳውቀን፤

- ይህ አይነት የተወሳሰበ ወንጀል በቴክኖሎጂ፣ በፎረንሲክ እንዲሁም በልዩ ልዩ የፕሮፌሽናል ማስረጃ በማረጋገጥ የሚፈታ ወንጀል በመሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ይህን አድርጎ ከሆነም ውጤቱን በግልፅ እንዲያሳውቀን፤

- የሚኒሊክና የጴጥሮስ ሆስፒታሎች የህክምና ማስረጃውን የምርመራውን ሂደት በግልፅ የሚያሳይ ውጤት እንዲገለፅልን ሲል ጠይቋል።

ለተባባሪ አካላት ባቀረበው ጥሪም "ስለተጠቂ ቃልኪዳን ባህሩ እየተሰራጨ ያለውን መረጃ ትክክለኛነት በማጣራትና በነበሩ ሂደቶች ዙሪያ የተደረገላት የህክምና ሂደቶች ትክክለኛነት ተጣርቶ ፍትህ እስክታገኝ ድረስ ከተቋማችን ጋር ተባብረው እንዲሰሩ" ሲሉ አንስተዋል።

( የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

#ጾታዊጥቃት #ሐሰተኛመረጃ #ሴቶች

@tikvahethmagazine