Get Mystery Box with random crypto!

#ጥቆማ 'በጎ ስጦታ' የበጎ አድራጎት ድርጅት የተባለ አገር በቀል ድርጅት ከውጪ ካሉ ለጋሽ አካላ | TIKVAH-MAGAZINE

#ጥቆማ

"በጎ ስጦታ" የበጎ አድራጎት ድርጅት የተባለ አገር በቀል ድርጅት ከውጪ ካሉ ለጋሽ አካላት ጋር በመተባበር በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት ያላቸው ግን በአቅም ማነስ ምክንያት ትምህርታቸውን ለመከታተለ የከበዳቸውን ተማሪዎች ድጋፍ ለማረግ ማቀዱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ተቋሙ አሁን ላይ በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በኪያሜድ ኮሌጅ በነርሲንግ ዲፓርትመንት በዲፕሎማ መርሀ ግብር 20 ሴት ተማሪዎችን ተቀብሎ ከትምህርት ጋር የተያያዙ ሙሉ ወጪያቸውን በመሸፈን ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እድሉን ማመቻቸቱን ገልጿል።

የዚህ እድል ተሳታፊ የሆኑ ልጆች ምን ማሟላት አለባቸው?

- ከ 2014 እስከ 2015 የ 12 ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈትነው ለዲፕሎማ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ያመጡ፤

- በዲፕሎማ በቀን መርሀ ግብር ነርሲንግ መማር ፍላጎት ያላቸው።

- አቅም እንደ ሌላቸው ከቀበሌ ማስመስከር የሚችሉ፤

- ትምህርቱን ከጀመሩ በኋላ ውጤታቸውን አስጠብቀው መጓዝ የሚችሉ፤

- ተቋሙ ከትምህርት ውጪ ያሉ ወጪዎችን ስለማይሸፍን በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

ይህንን የምታሟሉ / በአከባቢያችሁ በትምህርታቸው ጎበዝ የሆኑ የምታቋቸው ካሉ በዚህ እድል እንዲጠቀሙ ይህንን መልዕክት አድርሷቸው።

ለበለጠ መረጃ በቴሌግራም @elzabet18/@Dr_Daniel_D ወይም በስልክ ቁጥር +251912671410 /+251938327771/ +251953146834 ላይ ያግኙ።

BegoSitota.com

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine