Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ የ2017 የትምህርት ዘመን የትምህርት ካላንደር ይፋ ሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተ | TIKVAH-MAGAZINE

በአዲስ አበባ የ2017 የትምህርት ዘመን የትምህርት ካላንደር ይፋ ሆነ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2017 የትምህርት ዘመን በከተማ አስተዳደሩ ስር ባሉ የመንግስት፣ የግልና በሌሎች የተያዙ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛ ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ወጥነት ያለው የትምህርት የጊዜ ሰሌዳ /የትምህርት ካላንደር/ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

በዚህም፦

- ከሰኔ 24 እስከ 30/2016 ዓ.ም ድረስ የነባር ተማሪዎች ምዝገባ እና የመጽሐፍት ስርጭት

- ነሃሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም  ድረስ መምህራን በትምህርት ቤታቸው ተገኝተው ሪፖርት በማድረግ አጠቃላይ የመምህራን ጉባኤ ይደረጋል

- ከነሃሴ 21-30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የ7ተኛ እና የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ምዝገባ ይከናወናል

- ጳጉሜ 1 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን ድረስ አስፈላጊውን መረጃ አሟልተው የሚመጡ አዲስ የተማሪዎች ምዝገባ ይከናወናል

- መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም  ለተማሪዎች ስለ ት/ቤቱ ህገደንብና ተያያዥ ጉዳይ ላይ ገለጻ ይሰጣል

- መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም   መደበኛ ትምህርት ይጀምራል

- መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም ትምህርት በሬዲዮ ስርጭት ይጀምራል

- ህዳር 16-18 ቀን 2017 ዓ.ም አንደኛ ወሰነ ትምህርት አጋማሽ ፈተና ይሰጣል

- ከጥር 7-9 ቀን 2017 ዓ.ም ለ6ኛ ፣ ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ይሰጣል

- ከጥር 19-23 ቀን 2017 ዓ.ም አንደኛ ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና ይሰጣል

- ከጥር 26-29 ቀን 2017 ዓ.ም መምህራን ፈተና የሚያርሙበት እና ውጤት ማጠናቀሪያ ሳምንት

- ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም መምህራን የተማሪዎችን የፈተና ውጤት የሚያሳውቁበት ይሆናል

- የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም  የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት ይጀምራል

- ሚያዚያ 6-8 ቀን 2017 ዓ.ም  የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት አጋማሽ ፈተና ይሰጣል

- ግንቦት 19-22 ቀን 2017 ለ6ኛ፣ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ይሰጣል

- ከሰኔ 3-4 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ይሰጣል

- ከሰኔ 9-11 ቀን 2017 ዓ.ም  ድረስ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ይሰጣል

- ከሰኔ 16-20 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ሁለተኛ  ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና ይሰጣል

- ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ መምህራን የተማሪዎችን የፈተና ውጤት የሚያሳውቁበት ይሆናል

- ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም  የውጤት መግለጫ ካርድ በመስጠት የዓመቱ ትምህርት ይጠናቀቃል።

ቢሮው በ1ኛ ወሰነ ትምህርት 103 የትምህርት ቀናት ሲኖሩ በ2ኛ ወሰነ ትምህርት 101 ቀናት በጠቅላላው በዓመቱ 204 የትምህርት ቀናት መኖራቸውን ጠቅሷል።

በተጨማሪም ትምህርት ቢሮ የትምህርት ካላንደሩና ካላሻሻለ በስተቀር ማንኛውም ትምህርት ቤት ከካላንደሩ ውጪ የትምህርትን ስራ ማከናወን የተከለከለ መሆኑን አሳስቧል።

@TikvahethMagazine