Get Mystery Box with random crypto!

'ገንዘብ ለማግኘት ይጫወቱ' (play-to-win)  ጌሞች  መብዛት በማዝናናት እና በገንዘብ ለ | TIKVAH-MAGAZINE

"ገንዘብ ለማግኘት ይጫወቱ" (play-to-win)  ጌሞች  መብዛት

በማዝናናት እና በገንዘብ ለማግኘት መካከል ያለውን መስመር የሚያደበዝዙ አዳዲስ ጌሞች በብዛት እየታዩ ነው።

እንደ Notcoin፣ TapSwap እና Hamster Kombat ያሉ ጌሞች ተጫዋቾች በመጫወት የዲጂታል-ገንዘብ (Cryptocurrency) ሊያገኙ በሚችሉበት በ "ገንዘብ ለማግኘት ይጫወቱ" (play-to-win) ሞዴላቸው በአለም አቀፍ ደረጃ መነጋገሪያ እየሆኑ ነው።

ለምሳሌ ብናነሳው Hamster Kombat 3 ወር ባልሞላ ጊዜ ከ 110 ሚሊዮን በላይ ተጫዋቾች ማግኘት ችሏል።  ነገር ግን ለእዚህ ስኬታቸው ዋናውን ሚና የሚጫወተው ኤርድሮፕ (Airdrop) በመባል የሚታወቀው ፅንሰ-ሀሳብ ነው።

ኤርድሮፕስ (Airdrops) - ነፃ ክሪፕቶ (ገንዘብ) ወይስ አዲስ የማርኬቲንግ ዘዴ?

ከ’ኤርድሮፕስ' (Airdrops) በስተጀርባ ያለው መሰረታዊ ፅንሰ ሃሳብ ሰዎች ጨዋታ በመጫወት ብቻ በቀላሉ ነፃ ክሪፕቶከረንሲ (ዲጂታል ገንዘብ) እንዲቀበሉ የሚያደርግ ነው።

እስካሁን ባለው ይህ ፅንሰ ሃሳብ የክሪፕቶከረንሲ (ዲጂታል ገንዘብ) ባለቤቶች ተደራሽነታቸውን ለማስፋትና ተዓማኒነትን በማግኘት ወደ ገቢያው ለመግባት ይጠቀሙበት የነበረ ነው።

አዲስ የተፈጠሩ ክሪፕቶከረንሲዎች (ዲጂታል ገንዘባቸውን) በቀጥታ በነፃ ለተጠቃሚ በዚህ መንገድ ያሰራጫሉ። ብዙውን ጊዜ ግን ዝም ብለው ሳይሆን የሚያሰራጩት ቀላል ተግባራትን ማለትም፣ ጨዋታዎችን በማጫወት ወይም ኦንላይን ግሩፕ ለመቀላቀል ይሆናል።

አሁን ላይ በቴሌግራም ላይ በመምጣታቸው ስማቸው የገነነው እንደ Notcoin እና Hamster Kombat ያሉ ጨዋታዎች የ ኤርድሮፕን (Airdrops) ፅንሰ ሃሳብ ተጠቅመዋል።

'Notcoin' በይፋ ገበያዎች (Exchanges) ላይ ግብይት ከመጀመሩ በፊት ከ80 ቢሊዮን በላይ ቶከኖችን (ዲጂታል ገንዘብ) በሰፊው አሰራጭቷል።

ይህ ድርጊት ለተጫዋቾች አስደሳች ቢሆንም ይሄ የ ኤርድሮፖ' (Airdrop) ፅንሰ ሃሳብ ግን ለእዚህ ፕሮጀክት የማደግ ዋናውን ሚና ተጫውቷል። በዚህ ፕሮጀክት ዓላማቸውም፡-

መነጋገሪያ መሆን፡ ነፃ crypto (ክሪፕቶ) ትኩረትን ይስባል እና በጨዋታው እና በተጨዋቾች ዙሪያ ደስታን ይፈጥራል።

ማህበረሰብ መገንባት፡  ኤርድሮፕ (Airdrops) ተጫዋቾች የኦንላይን  እና የማህበራዊ ሚዲያ ቡድኖችን (ማለትም እንደ ቴሌግራም ቡድን እና ቻናል) እንዲቀላቀሉ ያበረታታል፣ ይህም ዲጂታል ማኅበረሰብን (Digital Community) ይገነባል።

የዲጂታል ገንዘብ  ምንዛሬ ልውውጥ ገበያ ላይ የመሳተፍ እድልን ማሳደግ፡ ትልቅ የተጠቃሚ እና ጥሩ ሚንቀሳቅስ ማኅበረሰብ (Active Community) የጌሙን ዲጂታል ገንዘብ የመገበያያ ገበያ ላይ የመውጣት እድሉን ይጨምራሉ።

የክሪፕቶ ምንዛሬ ልውውጥ ገበያ ማለት ተጠቃሚዎች cryptocurrency መግዛት፣መሸጥ እና መገበያየት የሚችሉባቸው የኦንላይን መድረኮች ናቸው።

እነዚህ መድረኮች ለነዚህ  "ገንዘብ ለማግኘት ይጫወቱ" (play-to-win) ለሚሉት ጨዋታዎች ዘላቂነት እንዲኖራቸው ወሳኝ ናቸው።

የሚሸልሙትን ዲጂታል ገንዘብ በነዚህ የሽያጭ መድረኮች ላይ እንዲዘረዝሩ በማድረግ፣ ለጌሙ እና ለዚህ ዲጂታል ገንዘብ ፈጣሪ ደርጅት እና ለተጫዋቾቹ ከጌሙ ጋር የተሰራውን ዲጂታል ገንዘብ ወደ እውቅና ወዳላቸው (እንደ ቢትኮይን ያሉ) ዲጂታል ገንዘብ (Cryptocurrency) ወይም ወደ ባህላዊ ገንዘብ (ዶላር፣ ዩሮ እና ብር የመሳሰሉት) እንዲቀይሩ ያስችላቸዋል።

#ጥንቃቄ፡ ሁሉም ኤርድሮፕስ (airdrops) አንድ አይነት አይደሉም!

ኤርድሮፕስ (airdrops) አዳዲስ ጨዋታዎችን እና ሽልማቶችን የሚያገኙበት መንገድ ሊሆን ቢችልም ግን በጥንቃቄ ማስተዋል ግን ያስፈልጋል። ምክንያቱም፤ ትክክለኛ ዋጋ ላይኖራቸው ይችላል፣ ተሳክቶላቸው የዲጂታል ገንዘብ ምንዛሬ ልውውጥ ገበያ ውስጥ ላይገቡ እና የማጭበርበሪያ መንገዶችም ሊሆኑ ይችላሉ።

"ገንዘብ ለማግኘት ይጫወቱ" (play-to-win) ፅንሰ-ሀሳብ በመሠረቱ የሁለቱም የጨዋታዎችን (Games) እና  ዲጂታል ገንዘብ  (Cryptocurrency) ገጽታ እየለወጠ ነው። 

ነገር ግን፣ ጥንቃቄ በተሞላበት አቀራረብ እና ጨዋታ ላይ ትኩረት በማድረግ፣ እና  ተጫዋቾቹ ከኤርድሮፕስ (airdrops) ጋር ተያይዘው ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶችን እያወቁ እና እየተጠነቀቁ  በእነዚህ ጨዋታዎች ሊዝናኑ ይችላሉ።

#TikvahTechTeam   #TechDailly   #Cryptocurrency    #Airdrop

@TikvahethMagazine