Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ የዲጂታል ምንዛሬ (Digital Currency) እንቅስቃሴ ጅማሮ የሚኒስትሮች ምክር ቤ | TIKVAH-MAGAZINE

ኢትዮጵያ የዲጂታል ምንዛሬ (Digital Currency) እንቅስቃሴ ጅማሮ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትላንት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በኢትዮጵያ የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ምንዛሪ (ሲ.ቢ.ዲ.ሲ) (Central Bank Digital Currency (CBDC) ) ማስተዋወቅ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ የሚያወጣውን ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል።

ይህ አሰራር ማለትም የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ምንዛሪ (CBDC) ከባህላዊ ገንዘብ ጎን ለጎን እየተዘዋወረ ለዲጂታል የኢትዮጵያ ገንዘብ መንገድ ይከፍታል ተብሏል።

  የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ምንዛሪ (ሲ.ቢ.ዲ.ሲ) - Central Bank Digital Currency (CBDC) ምንድነው?

የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ምንዛሪ  (CBDC) በአንድ ሀገር ማዕከላዊ ባንክ የሚሰጥ የዲጂታል ምንዛሪ አይነት ነው። በኢትዮጵያ ስናየው ደግሞ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚሰጥ የዲጂታል ምንዛሪ ማለት ነው።

ይህም እንደ ቢትኮይን ያሉ ክሪፕቶከረንሲዎች (Cryptocurrencies) አይነት ሆኖ ከእነሱ የሚለየው ፣ የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ምንዛሪ (CBDC)ን የሚያዘጋጀው ፣ ሚያወጣው እና የሚቆጣጠረው የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ መሆኑ ነው።

ይህ ማለት የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ የምንዛሬ ዋጋውን እና የተረጋጋ እንቅስቃሴ መኖሩን ያረጋግጣል። የመግዛት አቅሙም በማዕከላዊ ባንክ የተስተካከለ እና ከአገሪቱ የባህላዊ ገንዘብ (የ ኢትዮጵያ ብር) ምንዛሪ ጋር ተመጣጣኝ እንዲሆን ይደረጋል።

በጠቅላላ አገላለጽ የአንድ ሀገር CBDC በዲጂታል መልክ ሆነ እንጂ በመሠረቱ ከ ሀገሪቱ በማዕከላዊ ባንክ የተደገፈ ባህላዊ ገንዘብ (Fiat Currency) ምንዛሬ ጋር እኩል ነው ማለት ይቻላል።

በ ማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ምንዛሪ (CBDC) ዙሪያ የሌሎች ሃገራት ልምድ ምን ይመስላል?

ኢትዮጵያ ይህንን አይነት ሥርዓት ለመሞከር የመጀመሪያዋ ሀገር አይደለችም።  የስኬት ደረጃዎቻቸው ይለያይ እንጂ በተለያዩ ሀገራት ተግባራዊ ሆኗል።

የሌሎች ሀገራት ተሞክሮን በተመለከተ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።

Credit : Shega Media

#TikvahTechTeam #CBDC #Cryptocurrencies

@TikvahethMagazine