Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 131.53K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 485

2021-02-06 16:59:38
አኗር መስጅድ አካባቢ ባለ ስፍራ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ከ20 በላይ መኖሪያ ቤቶች ተቃጠሉ!

በአዲስ አበባ ልዩ ስፍራው ልዩ ስሙ ስሜ ሜዳ (ንጉስ ሚካኤል ሆቴል አካባቢ ) ባለ አኗር መስጅድ አካባቢ በሚገኝ ስፍራ ዛሬ ጥር 29,2013 ቀን ስድስት ሰአት ምክንያቱ ባልታወቀ የእሳት አደጋ ከ20 በላይ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን ፊደል ፖስት ከስፍራው የደረሰ መረጃ ያሳያል።የከተማው እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ስለተፈጠረው የአደጋ ውድመትና መንስኤ ዝርርዝር መረጃ ባይሰጥም እሳቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን ለፊደል ፖሰት ገልፇል።

Via Fidelpost
@YeneTube @FikerAssefa
18.9K views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-06 15:03:09
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንዳንድ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች ባጋጠመው አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት በረራዎች መስተጓጎላቸውን ገለጸ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንዳንድ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች ባጋጠመው አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት ዛሬ ወደ ላልይበላ፣ ጎንደር እና ባህር ዳር ይደረጉ የነበሩ በረራዎች መስተጓጎላቸውን ገለጸ፡፡አየር መንገዱ ለተፈጠረው መጉላላትም ደንበኞቹን ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን የአየር ሁኔታው መሻሻሉን የሚገልጽ መረጃ ከብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት እንደደረሰው በረራውን የሚቀጥል መሆኑን ገልጿል፡፡ከብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት መስሪያ ቤት መረጃ እንደደረሰውም በጥሪ ማዕከሉ በኩል ለደንበኞቹ የሚያሳውቅ መሆኑንም በፌስቡክ ገጹ ጠቅሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
14.3K viewsedited  12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-06 13:03:20
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከምስራቅ አፍሪካ ባንኮች መካከል የመጀመሪያውን ደረጃ አገኘ፡፡

የኢትጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀው የአውሮፓውያን 2020 በጀት አመት አፍሪካ ውስጥ ከሚገኙ 100 ባንኮች መካከል የ 17ኛ፣ ከምስራቅ አፍሪካ ደግሞ 1ኛ ደረጃ በመያዝ አመቱን ማጠናቀቁን አፍሪካ ቢዝነስ እና ዘ አፍሪካ ሪፖርት በጥናታቸው ይፋ አደረጉ፡፡የአፍሪካ ባንኮች በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት በተከሰተው የኢኮኖሚና የንግድ መቀዛቀዝ ሳይበገሩ ከባለፉት 10 ዓመታት የተሻለ የካፒታል መጠን በማስመዝገብ አመቱን አጠናቀዋል፡፡ ባንኮች አማራጭ አገልግሎቶችን በማስተዋወቅና በዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች አማካኝነት ተደራሽነትን ለማስፋት ያደረጉት ጥረት የኮቪድ ተጽዕኖን በመቋቋም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንዳስቻላቸው የጥናት ሪፖርቶቹ አስነብበዋል፡፡

https://african.business/2020/11/finance-services/are-banks-strong-enough-to-weather-the-storm/
https://www.gfmag.com/magazine/may-2020/worlds-best-banks-2020-africa

Via CBE
@YeneTube @FikerAssefa
14.2K viewsedited  10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-06 12:50:53 በሰላም ሚኒስትር የተመራ ልዑክ በትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ ስርጭት ያለበትን ሁኔታ ለመመልከት መቐለ ገባ!

በሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እና በዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሊ የተመራ የልዑካን ቡድን በትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ ስርጭት ያለበትን ሁኔታ ለመመልከት መቐለ ገብቷል።

እንደ ኢዘአ ዘገባ የልዑክ ቡድኑ አባላት በትግራይ ክልል በሚኖራቸው ቆይታ በመቐለ እና በአካባቢው እንዲሁም በኩሃ ያለውን የሰብአዊ ድጋፍ ስርጭት ሁኔታን ተዘዋውረው ይጎበኛሉ።

በተጨማሪም በትግራይ ክልል እየተሰጠ ባለው የሰብአዊ ድጋፍ ዙሪያ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እና ከብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩም ይጠበቃል።

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
12.8K viewsedited  09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-06 12:15:43
በ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ በ30 ሄክታር መሬት የተገነባው ፊቤላ እንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ በነገው ዕለት ይመረቃል፡፡

ሰባት ከፋብሪካዎች የያዘ ፊቤላ እንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ በቀን 1ሺህ 500 ቶን የምግብ ዘይት የሚያመርት ሲሆን፣ የሀገሪቱን 60 በመቶ የዘይት ፍላጎት የሚሸፍንና ለዘይት ይወጣ ከነበረው 30 በመቶ ወጪውን የሚያስቀር እንደሆነ ባለሃብቱና የቢኬጂ ቦርድ ሊቀመንበሩ አቶ በላይነህ ክንዴ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ፊቤላ እንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ ከዘይት ፍብሪካው በተጨማሪ በቀን 200 ቶን ሰሊጥ ማቀነባበር የሚችል ፋብሪካ፣ በቀን 96 ቶን ሳሙና የሚያመርት ፋብሪካ፣ የአትክልትና ማርጋሪት ማምረቻ፣ የፕላስቲክና ጠርሙስ እንዲሁም የካርቶን ፍብሪካዎችን በውስጡ እንደሚያመርት ተናግረዋል።የዘይት ፍብሪካው ምርት የጥራት ደረጃው ተፈትሾ ለገበያ እንዲቀርብ ፍቃድ በማግኘቱ ከሰኞ ጀምሮ ለሸማቹ እንደሚደርስም ተገልጿል።

[Walta]
@YeneTube @FikerAssefa
12.8K viewsedited  09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-06 11:39:44
336 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ ዓረብያ ሪያድ ከተማ በትናንትናው ዕለት ወደ አገራቸው መመለሳቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይረክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ለተመላሾቹ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
14.9K views08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-06 11:38:01
ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ 2‚785 ተማሪዎችን አስመረቀ!

ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 785 ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡

በምረቃ ስነ ስርአት ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ጨምሮ ሌሎች የክልል እና የፌዴራል ከፍተና የስራ ሀላፊዎች እና የኃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
14.7K views08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-06 10:11:41
የዲ.አር.ኮንጎ ፕሬዝደንት ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል!

የዲሞክራቲክ ሪፓሊክ ኮንጎ ፕሬዝደንት ፌሊክስ አንቶየን ትሺስኬዲ ትናንት ጥር 28 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ላይ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ፕሬዝደንቱ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ፕሬዝደንት ትሺስኬዲ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበርነትን ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ ይቀበላሉ፡፡የሕዳሴ ግድቡ ድርድርም በእርሳቸው መሪነት የሚቀጥል ይሆናል፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
11.8K views07:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-06 09:45:15
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው!

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ እና በተከታታይ ፕሮግራም ያስተማራቸውን 5 ሺህ 310 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው፡፡

በመጀመሪያ ዲግሪ 2ሺህ 963 ወንድ እና 2ሺህ 115 ሴት ተማሪዎችን እነዲሁም 214 ወንድ እና 18 ሴት ተማሪዎችን በድህረ ምረቃ ፕሮግራም ነው እያስመቀ ያለው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
11.8K views06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-06 09:43:32
‹‹ኤርትራ ወታደሮቿን ከትግራይ በአስቸኳይ ታስወጣ›› በሚል የወጣውን የዩናይትድ ስቴትስ መግለጫ አስመራ አግባብነት የሌለው ስትል ውድቅ አደረገች፡፡

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገብረመስቀል በቲውተር ገፃቸው ባሰፈሩት አጭር ምላሽ በኤርትራ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ያወጣውን መግለጫ ሀሰተኛና ተንሳፋፊ ወይም ማስረጃ ያልቀረበበት ክስ ብለውታል፡፡በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን በቲውተር ገፃቸው ያሰፈሩት በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ‹‹የተወሰኑ አገራት መንግሥት ስለመኖራቸው ማረጋገጫ ሳይሰጥ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል እንዲወጡ ሲጠይቁ እየተመለከትን ነው›› ብለዋል፡፡‹‹ግን ለምን ወረራ የፈፀመውና የኢትዮጵያን ሉኣላዊ ድንበር የያዘውን የሱዳን ኃይል እንዲወጣ ጥያቄ አያቀርቡም?›› ሲሉም አገራቱን ተችዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ አርብ ባወጣችው መግለጫ ‹‹በትግራይ ክልል የኤርትራ ወታደሮች እንዳሉ የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ አለኝ›› በማለት በአስቸኳይ እንዲወጡ መጠየቋ ይታወሳል፡፡‹‹ወታደሮቹ የሰብኣዊ መብት ጥሰትንም እየፈፀሙ ነው›› በማለት በአስቸኳይ እንዲወጡ መጠየቋን በኤርትራ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ማሳወቁም አይዘነጋም።የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት ግን በትግራይ ክልል የኤርትራ ወታደሮች ተሳትፎ አለ የሚለውን ሪፖርት አይቀበሉትም።

አሐዱ
@YeneTube @FikerAssefa
11.2K views06:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ