Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 127.33K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 482

2021-02-10 22:41:03
300 ዜጎች ከሳዑዲ ዓረቢያ ተመለሱ!

300 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ጂዳ ከተማ ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ከሰሞኑ ከሳዑዲ ዓረቢያና ከሌሎች ሃገራት ኢትዮጵያውያን ዜጎች መመለሳቸው ይታወሳል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
16.4K views19:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-10 20:56:38
ምርጫ ቦርዱ ለ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ የ49 ሺህ 407 የምርጫ ጣቢያዎችን ዝርዝር ይፋ አደረገ!

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው 6ኛው አገር አቀፍ የምርጫ ሰሌዳ ላይ በተገለጸው መሰረት የካቲት 03 ቀን የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር ይፋ ማድረጊያ ቀን ነው። በዚህም መሰረት በዛሬው እለት ቦርዱ የምርጫ ምልክት በመውሰድ ለምርጫ ለመወዳደር ዝግጅት እያደረጉ ያሉ ሁሉም ፓርቲዎች የምርጫ ጣቢያዎቹን ዝርዝር በፍላሽ እንዲደርሳቸው ማድረጕን አስታወቋል።

የምርጫ ጣቢያዎቹን ዝርዝር በምርጫ ቦርዱ ድረ-ገፅ ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።

በዚህ መሰረት:

በአዲስ አበባ ከተማ - 1,848
በሲዳማ ክልል - 2,247
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል - 699
አፋር ክልል- 1,432
አማራ ክልል- 12,199
ድሬዳዋ ክልል- 305
ጋምቤላ ክልል- 431
ሃረሪ ክልል- 285
ኦሮሚያ ክልል- 17,623
ደ/ብ/ብ/ህ ክልል- 8,281
ሶማሌ ክልል- 4,057

በአጠቃላይ 49 ሺህ 407 የምርጫ ጣቢያዎች ለ6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን የምርጫ ጣቢያዎቹን ዝርዝር ከስር ከሚገኘው ሊንክ ላይ ማግኘት ይቻላል።

https://nebe.org.et/am/polling-stations

@YeneTube @FikerAssefa
16.7K views17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-10 20:54:40
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚቀርቡለትን ቅሬታዎች በአግባቡ ምልሽ እንዲሰጥ በአንዳንድ ተቃዋሚዎች ተጠየቀ።

ቦርዱ ዛሬ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ባደረገው የምክክር መድረክ እስካሁን የተከናወኑ የዝግጅት ተግባራትን ዘርዝሯል። ተቃዋሚዎች በበኩላቸው እስካሁን የተከናወኑ ተግባራትን በማድነቅ በየጊዜው ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ፈጣን እና በደብዳቤ ምላሽ አለመስጠቱን ወቅሰዋል። በጽሑፍ ለሚቀርቡ አቤቱታዎች በጽሑፍ ምላሽ አለመሰጠቱን በተመለከተ፦ ቅሬታውን የተቀበሉት የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፦ «ለተፈጠረው ክፍተት ይቅርታ» በመጠየቅ የሚቀርቡ አቤቱታዎች እጅግ መብዛታቸውን ጠቊመዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
15.2K views17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-10 20:47:24 የትግራይ ክልል 80 በመቶው ለዕርዳታ ተደራሽ አይደለም በማለት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ፕሬዝዳንት አበራ ቶላ ዛሬ ለጋዜጠኞች መናገራቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ 10 ሺዎች በርሃብ ሊሞቱ እንደሚችሉ ያስጠነቀቀው ማኅበሩ፣ እስካሁን ዕርዳታ እየደረሰ ያለው ከመቀሌ በስተሰሜን እና ደቡብ በዋና ዋና መንገዶች አቅራቢያ ብቻ ነው ብሏል፡፡ በክልሉ 3.8 ሚሊዮን ሰዎች ዕርዳታ ፈላጊዎች አሉ የሚል ግምት እንዳለውም አስታውቋል፡፡

Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
14.7K views17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-10 19:49:57
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ መስተዳድሮች የዕጩዎች ምዝገባ ቀንን ይፋ አደረገ፡፡

ቦርዱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በኦሮሚያ እና በሃረሪ ክልላዊ መንግስታት የሚወዳደሩ እጩዎች የሚመዘገቡበትን ቀንም ይፋ አድርጓል፡፡

በመሆኑም በሁለቱ ከተማ መስተዳድሮች እና ቀደም ሲል በተጠቀሱት ክልሎች የሚገኙ እጩዎች ምዝገባ ከየካቲት 8 እስከ የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 እንደሚከናወን ቦርዱ አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
15.3K views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-10 19:32:51
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አፈ ጉባኤና የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ታደለ ተረፈ ከኃላፊነት ተነሱ!

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብልፅግና ፓርቲ የክልሉን ዋና አፈ ጉባኤና የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ታደለ ተረፈ ከኃላፊነት አነሳ።ፓርቲው የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት “ብልፅግና አሀዳዊ ነው በሚል የሀሰት ትርክት ሁለት ቦታ በመርገጥ” ህዝብን ሲበድሉ የነበሩ አመራሮች መኖራቸውን ገምግሟል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የብልጽግና ፓርቲ በመተከል ዞን ለተፈጸመው ግድያ እና ሌሎች ጉዳቶች ይቅርታ መጠየቁ ይታወሳል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
15.4K views16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-10 16:42:23
የአፋር ክልል ህዝብና መንግስት ግምቱ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ በትግራይ ክልል በመገኘት አስረከበ።

ድጋፉን የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኤለማ አቡበከርን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች በመቀሌ ተገኝተው ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አስረክበዋል።

የምግብ ቁሳቁሱ ሩዝ፣ የፉርኖ ዱቄት፣ ስኳርና ቴምር ሲሆን አጠቃላይ ብዛቱ 2ሺህ700 ኩንታል መሆኑ ተገልጿል።

የአፋር ክልል ላደረገው ድጋፍ በትግራይ ህዝብ ስም ምስጋና ያቀረቡት የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ፤ “የአፋር ህዝብ የትግራይ ህዝብ ወንድም መሆኑን አሳይቷል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አቶ ኤለማ አቡበከር በበኩላቸው ክልላቸው ለትግራይ ያለውን አጋርነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል በማረጋገጥ ድጋፉ ቀጣይነት እንደሚኖረው ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
15.5K views13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-10 16:08:23
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በመተከል ዞን ለደረሰው ግድያና ውድመት ይቅርታ ጠየቀ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ጉባኤ ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።ጉባኤው በአሶሳ ከተማ በክልሉ ወቅታዊ የፖለቲካና የሠላም ሁኔታ ላይ ለሶስት ቀናት ሲካሄድ ቆይቷል፡፡በዚህም በክልሉ መተከል ዞን በደረሰው አሳዛኝና ዘግናኝ ማንነት ተኮር ግድያና ውድመት ፓርቲው ይቅርታ ጠይቋል፡፡

የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት ‘ብልፅግና አሀዳዊ ነው’ በሚል የሀሰት ትርክት ከሁለት ቦታ በመርገጥ ህዝብን ሲበድሉ የነበሩ አመራሮች መኖራቸውም ተገምግሟል፡፡በቀጣይ የህግ የበላይነትን በማስከበር በወንጀል የተሳተፉ የስራ ኃላፊዎችም ተጠያቂ እንደሚሆኑም ተጠቁሟል።የፓርቲውን እሴትና መርህ በማክበር የዜጎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራም በአቋም መግለጫው ማሳወቁን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
15.3K views13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-10 15:10:05 የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን በአንድ ሳምንት ዉስጥ የትራንሰፖርት ታሪፍ ማሰተካከያ አጥንቶ እንደሚገልጽ አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ ህጋዉ የታሪፍ ማስተካከያ አስከሚያሳዉቅም ዋጋ የሚጨምሩ አሽከርካሪዎች ላይ ህጋዊ እርማጃ እወስዳለዉ ብሏል፡፡ባለፉት ሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የትራንስፖርት እጥረት ተስተዉሏል፡፡እንዳንድ አሽከርካሪዎችም በራሳቸዉ ፍቃድ የነዳጅ ጭማሪ ስላለ በማለትም ዋጋ እየጨመሩም ናቸዉ፡፡የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን በሁለት ቀናት የተፈጠረዉን የትራንስፖርት እጥረት መስተዋሉንም የባለስልጣኑ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ በድሉ ሌሊሳ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
15.0K views12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-10 14:30:12 ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያዩ አገራት የሚገኙ ዲፕሎማቶች ስለ አገራቸዉ ጥቅም የተሻለ ስራ የሰሩትን እና ያልሰሩትን ሊገመግም ነው፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ እየገጠማት ያለዉን የተዛባ አመለካከት ለማስረዳት ሁሉም ድፕሎማቶች ስለ አገራቸዉ ብሄራዊ ጥቅም በትኩረት እንዲሰሩም አሳስቧል፡፡

የተወሰኑ ድፕሎማቶች በአለም አቀፍ መገናኛዎች ጭምር በመቅርብ በኢትዮጵያ ስላለዉ ሁኔታ እንዲሁም ስለ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እያስረዱ ቢሆንም አብዛኞቹ ግን ብዙ የቤት ሥራ ይጠብቃቸዋልም ተብሏል፡፡

የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለ አገራቸዉ ብሄራዊ ጥቅም የተሸለ አፈፃፀም የሰሩና ያልሰሩ ዲፕሎማቶችን በቁጥር ጭምር በመያዝ እንደሚገመግምም ኢትዮ ኤፍ ኤም ከሚኒስቴሩ ያገኘዉ መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን ወክለዉ በተለያዩ አገራት የሚገኙ የዲፕሎማት ማህበረሰቦች ባገኙት አጋጣሚ በአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እና በማህበራዊ ሚዲያዎችም ጭምር የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ስለ ኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ግንዛቤ እንዲኖረዉ በትኩረት እንዲሰሩም ጥሪ ተደርጓል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ አገራት የሚኖሩ የዲያስፖራ ማህበረሰብ እና ምሁራን የአገሪቱን ብሄራዊ ጥቅም በማስጠበቅ ረገድ ብዙ ስራዎችን ሊሰሩ ይገባል ተብሏል፡፡

በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በነበረዉ የህግ ማስከበር ሂደት ጋር ተያይዞ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ የተዛቡ መረጃዎችን እንደያዘ ያስታወቀዉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እዉነታዉን ለማስረዳት ሁሉም ዜጋ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

ከህዳሴ ግድብ እና ከኢትዮ ሱዳን የድንበር ዉዝግብ ጋር ተያይዞም ዲፕሎማቶች፤ ምሁራን፤ ዲስፖራዎች፤ እና የአገር ዉስጥ ሚዲያዎች ጭምር ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ስለ አገራቸዉ ተጨባጭ ሁኔታ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ማስረዳት አለባቸዉ ተብሏል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
15.8K views11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ