Get Mystery Box with random crypto!

የአፋር ክልል ህዝብና መንግስት ግምቱ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ በትግራ | YeneTube

የአፋር ክልል ህዝብና መንግስት ግምቱ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ በትግራይ ክልል በመገኘት አስረከበ።

ድጋፉን የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኤለማ አቡበከርን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች በመቀሌ ተገኝተው ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አስረክበዋል።

የምግብ ቁሳቁሱ ሩዝ፣ የፉርኖ ዱቄት፣ ስኳርና ቴምር ሲሆን አጠቃላይ ብዛቱ 2ሺህ700 ኩንታል መሆኑ ተገልጿል።

የአፋር ክልል ላደረገው ድጋፍ በትግራይ ህዝብ ስም ምስጋና ያቀረቡት የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ፤ “የአፋር ህዝብ የትግራይ ህዝብ ወንድም መሆኑን አሳይቷል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አቶ ኤለማ አቡበከር በበኩላቸው ክልላቸው ለትግራይ ያለውን አጋርነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል በማረጋገጥ ድጋፉ ቀጣይነት እንደሚኖረው ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa