Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 127.33K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-05-06 22:05:05
ይህ ወጣት ቲክቶከር በቁጥጥር ስር መዋሉን ታውቋል።

አቶ አለሙ ቢጫ ለተባሉ ግለሰብ ህክምና በቲክቶክ የተሰበሰበ 350 ሽህ ብር "ታማሚው ስለማይድን ብሩን አጥፍቼዋለሁ . . . ቲክቶክ አካውንቴን ሸጬ እከፍላለሁ"በማለት በአደባባይ የተናገረው ወጣት ዛሬ ሚያዚያ 28/2016 በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።

የጉለሌ ፖሊስ መምሪያ የቅን ልቦች ከተባለ ድርጅት አቤቱታ ቀርቦለት ወጣቱን ሲፈልግ መቆየቱ ተሰምቷል።

ወጣቱ ሰሞኑን አጠፋሁት ያለውን 350 ሽህ ብር ለታካሚው አለሙ ቢጫ መመለሱ ታውቋል።ፖሊስ ጉዳዩን አጣርቶ በዋስትና እንደሚለቀ ይጠበቃል።

@Yenetube @Fikerassefa
13.5K views19:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-06 15:35:56
የኢትዮጵያ ሰራተኞች እየተከፈላቸው ባለዉ ደመወዝ ክፍያ ኑሮን መቋቋም ባለመቻላቸው ለችግር መጋለጣቸውን ኢሰማኮ አስታወቀ!

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ሰራተኞች እየተከፈላቸው ባለዉ ደመወዝ ክፍያ ኑሮን መቋቋም ባለመቻላቸው ለችግር መጋለጣቸውን በመግለፅ ይህን አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ ያቀረብኩት ጥያቄ ትኩረት ሳይሰጠዉ ቀርቷል ብለዋል።

ማህበሩ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበው ምላሽ አላገኙም ካሏቸዉ ጥያቄዎች ዉስጥ "ሠራተኞች አሁን እየተከፈላቸው ባለው የደመወዝ ክፍያ የኑሮ ዉድነቱን በፍጹም መቋቋም ያልቻሉ በመሆኑ ደመወዝ የገቢ የሥራ ግብር እንዲቀነስ ላቀረብነዉ ጥያቄ መንግሥት ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ብሏል።

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚወስን የደመወዝ ቦርድ እንዲቋቋም በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ የተደነገገ ቢሆንም የደመወዝ ቦርድ ማቋቋሚያ ደንብ በሚንስትሮች ምክር ቤት ባለመውጣቱ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያልተገባ መሆኑን ነዉ ማህበሩ ያስታወቀው።

በጦርነት ዘላቂ መፍትሒ ስለማይመጣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ግጭትና ጦርነት ቆሞ በዉይይት ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ሁሉም ወገኖች በድርድር እንዲፈቱ የጠየቀው ኢሰማኮ ለጉዳዩ አፅንኦት ይሰጠዉ ብሏል በመግለጫው።

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
15.2K views12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-06 11:42:29
እስራኤል አልጀዚራን ዘጋች፤ ጣቢያው ድንገተኛ ብርበራ ተደርጎበታል!

እስራኤል የአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጣቢያን ዘጋች። ጣቢያውን የዘጋችው ''የሐማስ አፈ ቀላጤ ሆኗል'' በሚል ክስ ነው።ጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁ “የእስራኤል ካቢኔ ጣቢያው እንዲዘጋ ወስኗል” ብለዋል።

ይህን ተከትሎ ፖሊስ በጣቢያው ቢሮ ኢየሩሳሌም፣ አምባሳደር ሆቴል ድንገተኛ ወረራ በመፈጸም ብርበራ አድርጓል።እስራኤል “አልጀዚራ ለብሔራዊ ደኅንነቴ ሥጋት ነው” ማለቷን ጣቢያው፣ “ቀሽም ነገር ግን አደገኛ ዉሸት” ሲል አጣጥሎታል።ጣቢያው በሕግ መብቱን እንደሚያስከብር ዝቷል።

የእስራኤል የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ሽሎሞ ካርሂ በድንገተኛ ወረራው አንዳንድ ቁሳቁሶች ተወስደዋል ብለዋል።በዚሁ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የኤክስ ገጽ በተለጠፈ ተንቀሳቃሽ ምሥል ፖሊሶች ወደ ሆቴሉ ገብተው ሲበረብሩ ያሳያል።የቢቢሲ ጋዜጠኞች ወደ ሥፍራው አቅንተው የነበረ ቢሆንም ወደ ውስጥ እንዳይገቡ፣ ክስተቱንም እንዳይቀርጹ ተከልክለዋል።

ሮይተርስ እንደዘገበው የእስራኤል ሳተላይት አገልግሎት አልጀዚራ ይታይበት በነበረ ምሥል አሁን የጽሑፍ መልእክት ብቻ እየታየ ይገኛል፤ መልእክቱም “መንግሥት በወሰነው መሠረት በእስራኤል የአልጀዚራ ሥርጭት እንዲቆም ተደርጓል” የሚል ነው።አልጀዚራ በሳተላይት ይታገድ እንጂ አሁንም በእስራኤል በፌስቡክ እየታየ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
14.8K views08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-05 16:37:06
በሀላባ ዞን በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን በተከሰተ ከባድ የጎርፍ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡በዞኑ ዌራ ዲጆ ወረዳ ትናንትና የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ የአምስት ሰዎች ማለፉን የዞኑ አስተዳደር ገልጿል፡፡

በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ህይወታቸው ካለፉት ውስጥ የሶስቱ አስክሬን ሲገኝ፤ የሁለቱ አስክሬስ እስካሁን እንዳልተገኘ ተጠቁሟል፡፡የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን ሁሴን÷ በቀጣይም ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

በተለይም ሕብረተሰቡ የጎርፍ ማፋሰሻ ቦታዎችን ማዘጋጀትን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ቅድመ ጥንቃቄዎችን እንዲያደርግ አስገንዝበዋል፡፡በጎርፍ አደጋው ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖችም የተሰማቸውን ሀዘን እንደገለጹም የክልሉ ኮሙኒኬሽ መረጃን ያመላክታል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
15.2K views13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-03 18:04:09
በየአካባቢው የቁም እንስሳት ቅርጫ ማረድ አለመከልከሉ ተገለጸ!

በአዲስ አበባ ከተማ የትንሳኤ በዓል ህብረተሰቡ በየቤቱ እና በየአካባቢው የቁም እንስሳትን ቅርጫ ማረድ አለመከልከሉን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው ለትንሳኤ በዓል ህብረተሰቡ በየቤቱ እና በየአካባቢው የቁም እንስሳትን ቅርጫ ማረድ ተከልክሏል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን አስታውቋል።

በየአካባቢው በህገ ወጥ መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የሚገኙ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የከተማውን ነዋሪ ጤንነት ላይ ጉዳት ስለሚያደርስ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግም ቢሮው ባወጣው መረጃ አመላክቷል።

የከተማው ነዋሪ በዓላትን ሽፋን በማድረግ ጤንነቱ ያልተረጋገጠ እንስሳት አርዶ ማከፋፈል በጤና ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ግምት ውስጥ በማስገባት በህገወጥ እርድ የሚሰማሩ አካላት በሚደረገው ቁጥጥር ተባባሪ እንዲሆን አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
19.2K views15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-03 12:23:47 ትላንት ማታ በአቃቂ የገበያ ማዕከል በደረሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋ 16 ሱቆች ሙሉ በሙሉ ተቃጥለዋል።

ሚያዚያ 24 ቀን2016 ዓ.ም ምሽት 3:10 ሰዓት ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 03 አቃቂ የገበያ መዕከል በተነሳ የእሳት አደጋ 16 ንግድ ሱቆች ሙሉ በሙሉና በከፊል ተቃጥለዋል።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር አምስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ሁለት የዉሀ ቦቴ ከ44 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማራ ሲሆን እሳቱ ወደገበያ ማዕከሉ ተስፋፍቶ በሰዉና በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን አደጋዉን ለመቆጣጠር ሁለት ሰዓት ፈጅቷአል።

በአደጋ መቆጣጠሩ ሂደት የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ከፍተኛ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።አቃቂ የገበያ ማዕከል ትንሹ መርካቶ እየተባለ የሚጠራ የገበያ ማዕከል ሲሆን ገበያ ማዕከሉ በከተማ ደረጃ ለእሳት አደጋ ተጋላጭ ተብለዉ ከተለዩ አንዱ ሲሆን በገበያ ማዕከሉ በተደጋጋሚ የእሳት አደጋ እያጋጠመ በንብረት ላይ ጉዳት ሲደርስ ቆይቷል።

ኮሚሽን መ/ቤቱ ገበያ ማዕከሉ ለአደጋ የተጋለጠባቸዉን ዝርዝር ጉዳዮችን የመፍትሄ ሀሳቦችን አካቶ ለገበያ ማዕከሉ ማህበራትና ለሚመለከታቸዉ አካላት ያቀረበ ቢሆንም የማስተካከያ ዕርምጃዎች አልተወሰዱም።በመሆኑም በቀጣይ መሰል አደጋዎች እንዳያጋጥሙ መፍትሄ እንዲሰጥ ኮሚሽኑ ያሳስባል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
13.2K views09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-02 13:18:31
የ ‘ገበታ ለሀገር’ ሎጆችን የማስተዳደር ኃላፊነት ለስካላይት ኢትዮጵያ ሆቴል ተሰጠ!

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለተከናወኑት የ'ገበታ ለሀገር' ፕሮጀክቶች ከዛሬ ጀምሮ ለክልል መንግስታት ተላልፈው መሰጠታቸው ተገለጸ።የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ይፋ ካደረገው መረጃ አዲስ ማለዳ እንደተመለከተችው ፕሮጀክቶቹ ለአማራ፣ ለኦሮሚያ እና ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት ተሰጥተዋል።

እንዲሁም በ'ገበታ ለሀገር' የተገነቡ ሎጆችን ስራ የማስኬድ ኃላፊነት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ስር ለሚገኘው ስካይ ላይት ሆቴል እንዲወስድ ስምምነት መፈረሙ ተመላክቷል።

በዚህም እስካሁን የተጠናቀቁት ሃላላ ኬላ ሎጅ፣ ጨበራ ጩርጩራ የዝሆን ዳና ሎጅ እና ወንጪ ኢኮ ሎጅ በስካይላይት ሆቴል የሚተዳደሩ ይሆናል። የጎርጎራ ፕሮጀክት ስራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ተብሏል።ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሰጠው ኃላፊነት የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ እና ለዓለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻነት ትውውቅ ከፍ ያለ ዕድል ስለሚፈጥር እንደሆነ ተመላክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
14.8K views10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-02 12:59:36 ‘’ የፕሬስ ነጻነት ቀን ስናከበር ጋዜጠኞች ለአካባቢ ደህንነት ጥበቃ ተግባራዊ ምላሽ በመስጠት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል‘’ ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ምክር ቤት የ2016 የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀንን ምክንያት በማድረግ በዛሬው ዕለት መግለጫ አውጥቷል፡፡ምክር ቤቱ በላከው መግለጫ የዘንድሮው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ‘’ጋዜጠኝነት በአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ውስጥ” ወይም “Journalism in the face of the Environmental Crisis” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተገፃል፡፡


በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ አማካይነት በየዓመቱ ሚያዝያ 25 ወይም ሜይ 3 የሚከበረው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን በአለም ዙሪያ ያለውን የፕሬስ ነፃነት ሁኔታ ለመገምገም፣ መገናኛ ብዙሃን በነጻነታቸው ላይ ከሚሰነዘረው ጥቃት ለመከላከል እና ህይወታቸውን ላጡ ጋዜጠኞች ክብር ለመስጠት የሚከበር በመሆኑ የመገናኛ ብዙኃንና የፕሬስ ነፃነት አቀንቃኞች ዕለቱን በተለየ ሁኔታ ይመለከቱታል ተብሏል፡፡

የአየር ንብረት እና የብዝሃ ህይወት ቀውስ በአካባቢ እና ስነ–ምህዳር ላይ ብቻ ሳይሆን በአለም ዙሪያ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት እየጎዳ ነው፤ በዚህም በዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ውስጥ ሃገራችን የጉዳቱ ገፈት ቀማሽ ከመሆንዋም ሌላ ችግሩን ለመቅረፍ እልህ አስጨራሽ ትግል ውስጥ ትገኛለች የሚለው መግለጫው፡፡

በዚህ ረገድ ባለፉት በርካታ አመታት በሃገራችን ቀላል የማይባሉ ጥረቶች ሲደረጉ የቆዩ ሲሆን በተለይ ባለፉት 5 አመታት የተከናወኑ የአካባቢ ጥበቃ ጥረቶች ቀላል አይደሉም፡፡በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች የሚተከሉበት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርና በየአካባቢው የሚካሄደው የአፈርና ውሃ እቀባ ስራ በሀገራችን ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር እየተከናወኑ ካሉ ተግባራት መካከል ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በዚህ ውስጥ የሃገራችን መገናኛ ብዙኃን ተቋማትና ጋዜጠኞች ቀላል የማይባል ሚና ተጫውተዋል፡፡የሀገራችን መገናኛ ብዙሃን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻሉ የመጡ አካባቢያዊ ለውጦችን በማጠናከር፣ ሊሻሻሉ የሚገባቸው ህጐች፣ አሰራሮችና ለአካባቢ ደህንነት ጠንቅ የሆኑ አመለካከቶች ላይ በመወያየት ትኩረት እንዲያገኙ ሲጥሩ ጋዜጠኞች ሥራቸውን ከስጋትና ፍርሃት ነፃ ሆነው በኃላፊነት ስሜት የሚሰሩበት ሁኔታ ትኩረት ሊስጠው እንደሚገባ ምክር ቤታችን ያምናል ሲል በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
13.8K views09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-01 12:56:40
የትግራይ ክልል ክለቦች ከ2017 ጀምሮ ከጦርነቱ በፊት ወደነበሩበት ሊግ ተመልሰው እንዲወዳደሩ ውሳኔ ተላለፈ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ፥ የትግራይ ክልል ክለቦች ከ2017 ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ከጦርነቱ በፊት ሲወዳደሩበት ወደነበረው ሊግ ተመልሰው እንዲወዳደሩ ውሳኔ አሳልፏል።

@Yenetube @Fikerassefa
14.4K views09:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-01 10:45:32 የአውሮፓ ህብረት የጣለውን ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ውሳኔ እንዲያጤነው ኢትዮጵያ ጠየቀች!

የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ መንግሥት በህገወጥ መንገድ በአውሮፓ የሚኖሩ ዜጎቹን ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ ነው በሚል በኢትዮጵያውያን ላይ የጣለው ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ እንዳሳዘናት ኢትዮጵያ አስታወቀች።የአውሮፓ ህብረት ይህንን አቋሙን እንዲያጤነው በቤልጂየም፣ ብራስልስ ተቀማጭነቱን ያደረገው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ትናንት ሚያዝያ 22/ 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት (ካውንስል) ያስተላለፈው የእግድ ውሳኔ በህብረቱ አባል አገራት ለመኖር ህጋዊ ፍቃድ የተነፈጋቸው ኢትዮጵያዊ ዜጎችን በክብር፣ በስርዓት እና ዘላቂነት ባለው ሁኔታ እንዲመለሱ ለማድረግ ሁለቱ ወገኖች በቅርበት እየሰሩ ባለበት ወቅት ነው ሲልም መግለጫው አስፍሯል።የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ከሰሞኑ በኅብረቱ ሕግ ሥር ያሉና ለኢትዮጵያውያን ቪዛ ለመስጠት ይውሉ የነበሩ አሠራሮች ላይ ገደብ መደረጉን አስታውቋል።

በዚህ ዕገዳ መሠረት፣ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ኢትዮጵያውያን በሚያቀርቧቸው ማስረጃዎች መሠረት ቪዛ ሲጠይቁ የሚያስፈልጓቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማንሳት (waiving requirements) አይችሉም።ኢትዮጵያውያን ከአንድ ጊዜ በላይ ወደ አውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ገብተው መውጣት የሚችሉበት ቪዛ (multiple entry) ማግኘት አይችሉየዲፕሎማት እና አገልግሎት ፓስፖርት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ያለ ክፍያ ቪዛ እንዲሰጣቸው አይደረግም።

በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን ቪዛ ለማግኘት የሚጠብቁት ጊዜ ከ15 የሥራ ቀናት ወደ 45 የሥራ ቀናት ከፍ እንዲል ውሳኔ መተላለፉ ተገልጿል።ለዚህም ውሳኔው የኢትዮጵያ መንግሥት ዜጎቹን ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ መሆኑን ገልጾ “የኢትዮጵያ ባለሥልጣኖች ዜጎችን መልሶ ለመውሰድ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡም” ብሏል።ኢትዮጵያ በበኩሏ በሰጠችው ምላሽ ጊዜያዊ የቪዛ እግዱ ዜጎቿን ወደ አገራቸው ለመመለስ እና ከማህበረሰቡም ጋር መልሶ ለማዋሃድ በኢትዮጵያ እና በህብረቱ መካከል ያለውን ጠንካራ ትብብር ያላገናዘበ ነው ብላለች።

በተጨማሪም ውሳኔው ማንነትን ለማረጋጋጥ የሚደረገውን አድካሚ ሂደት ከግምት ውስጥ ማስገባት አልቻለም ሲል ኤምባሲው ተችቶታል።የምክር ቤቱ እርምጃ "ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ከህብረቱ አባላት አገራት ወደ አገራቸው የሚመለሱበትን የቅበላ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራዊ እርምጃዎች ላይ እንቅፋት የሚፈጥር ነው ብሏል ከቤልጂየም በተጨማሪ ለሉክሰምበርግ ፣ ኔዘርላንድስ እና የአውሮፓ ህብረት የሚያገለግለው ኤምባሲው።

የአውሮፓ ህብረት አቋሙን እንደገና እንዲያጤን የጠየቀው ኤምባሲው ኢትዮጵያውያን ዜጎች ከአውሮፓ ወደ አገራቸው የሚመለሱበትን አሰራር በተመለከተ ከተሰጠው ውሳኔ ጋር በሚጣጣሙ እርምጃዎች ላይ ይመክራል ብሏል።ህብረቱ ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ የጉዞ ሰነዶች በመስጠት እንዲሁም በፍቃድ እና ያለ ፈቃድም የሚደረግ ስደተኞችን የመመለስ ሂደትን በተመለከተም ኢትዮጵያ “በቂ ትብብር አላደረገችም” ብሎ ነበር።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
12.6K views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ