Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ሰራተኞች እየተከፈላቸው ባለዉ ደመወዝ ክፍያ ኑሮን መቋቋም ባለመቻላቸው ለችግር መጋለጣቸ | YeneTube

የኢትዮጵያ ሰራተኞች እየተከፈላቸው ባለዉ ደመወዝ ክፍያ ኑሮን መቋቋም ባለመቻላቸው ለችግር መጋለጣቸውን ኢሰማኮ አስታወቀ!

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ሰራተኞች እየተከፈላቸው ባለዉ ደመወዝ ክፍያ ኑሮን መቋቋም ባለመቻላቸው ለችግር መጋለጣቸውን በመግለፅ ይህን አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ ያቀረብኩት ጥያቄ ትኩረት ሳይሰጠዉ ቀርቷል ብለዋል።

ማህበሩ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበው ምላሽ አላገኙም ካሏቸዉ ጥያቄዎች ዉስጥ "ሠራተኞች አሁን እየተከፈላቸው ባለው የደመወዝ ክፍያ የኑሮ ዉድነቱን በፍጹም መቋቋም ያልቻሉ በመሆኑ ደመወዝ የገቢ የሥራ ግብር እንዲቀነስ ላቀረብነዉ ጥያቄ መንግሥት ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ብሏል።

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚወስን የደመወዝ ቦርድ እንዲቋቋም በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ የተደነገገ ቢሆንም የደመወዝ ቦርድ ማቋቋሚያ ደንብ በሚንስትሮች ምክር ቤት ባለመውጣቱ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያልተገባ መሆኑን ነዉ ማህበሩ ያስታወቀው።

በጦርነት ዘላቂ መፍትሒ ስለማይመጣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ግጭትና ጦርነት ቆሞ በዉይይት ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ሁሉም ወገኖች በድርድር እንዲፈቱ የጠየቀው ኢሰማኮ ለጉዳዩ አፅንኦት ይሰጠዉ ብሏል በመግለጫው።

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa