Get Mystery Box with random crypto!

እስራኤል አልጀዚራን ዘጋች፤ ጣቢያው ድንገተኛ ብርበራ ተደርጎበታል! እስራኤል የአልጀዚራ ቴሌቪዥን | YeneTube

እስራኤል አልጀዚራን ዘጋች፤ ጣቢያው ድንገተኛ ብርበራ ተደርጎበታል!

እስራኤል የአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጣቢያን ዘጋች። ጣቢያውን የዘጋችው ''የሐማስ አፈ ቀላጤ ሆኗል'' በሚል ክስ ነው።ጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁ “የእስራኤል ካቢኔ ጣቢያው እንዲዘጋ ወስኗል” ብለዋል።

ይህን ተከትሎ ፖሊስ በጣቢያው ቢሮ ኢየሩሳሌም፣ አምባሳደር ሆቴል ድንገተኛ ወረራ በመፈጸም ብርበራ አድርጓል።እስራኤል “አልጀዚራ ለብሔራዊ ደኅንነቴ ሥጋት ነው” ማለቷን ጣቢያው፣ “ቀሽም ነገር ግን አደገኛ ዉሸት” ሲል አጣጥሎታል።ጣቢያው በሕግ መብቱን እንደሚያስከብር ዝቷል።

የእስራኤል የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ሽሎሞ ካርሂ በድንገተኛ ወረራው አንዳንድ ቁሳቁሶች ተወስደዋል ብለዋል።በዚሁ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የኤክስ ገጽ በተለጠፈ ተንቀሳቃሽ ምሥል ፖሊሶች ወደ ሆቴሉ ገብተው ሲበረብሩ ያሳያል።የቢቢሲ ጋዜጠኞች ወደ ሥፍራው አቅንተው የነበረ ቢሆንም ወደ ውስጥ እንዳይገቡ፣ ክስተቱንም እንዳይቀርጹ ተከልክለዋል።

ሮይተርስ እንደዘገበው የእስራኤል ሳተላይት አገልግሎት አልጀዚራ ይታይበት በነበረ ምሥል አሁን የጽሑፍ መልእክት ብቻ እየታየ ይገኛል፤ መልእክቱም “መንግሥት በወሰነው መሠረት በእስራኤል የአልጀዚራ ሥርጭት እንዲቆም ተደርጓል” የሚል ነው።አልጀዚራ በሳተላይት ይታገድ እንጂ አሁንም በእስራኤል በፌስቡክ እየታየ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa