Get Mystery Box with random crypto!

ይህ ወጣት ቲክቶከር በቁጥጥር ስር መዋሉን ታውቋል። አቶ አለሙ ቢጫ ለተባሉ ግለሰብ ህክምና በቲክ | YeneTube

ይህ ወጣት ቲክቶከር በቁጥጥር ስር መዋሉን ታውቋል።

አቶ አለሙ ቢጫ ለተባሉ ግለሰብ ህክምና በቲክቶክ የተሰበሰበ 350 ሽህ ብር "ታማሚው ስለማይድን ብሩን አጥፍቼዋለሁ . . . ቲክቶክ አካውንቴን ሸጬ እከፍላለሁ"በማለት በአደባባይ የተናገረው ወጣት ዛሬ ሚያዚያ 28/2016 በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።

የጉለሌ ፖሊስ መምሪያ የቅን ልቦች ከተባለ ድርጅት አቤቱታ ቀርቦለት ወጣቱን ሲፈልግ መቆየቱ ተሰምቷል።

ወጣቱ ሰሞኑን አጠፋሁት ያለውን 350 ሽህ ብር ለታካሚው አለሙ ቢጫ መመለሱ ታውቋል።ፖሊስ ጉዳዩን አጣርቶ በዋስትና እንደሚለቀ ይጠበቃል።

@Yenetube @Fikerassefa