Get Mystery Box with random crypto!

ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ዳውሮ ዞን ዛሬ ጠዋት የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ነዋሪዎች ገለጹ ፡፡ | YeneTube

ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ዳውሮ ዞን ዛሬ ጠዋት የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ነዋሪዎች ገለጹ ፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ ዛሬ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ተኩል አካባቢ የተከሰተው የዞኑ ዋና ከተማ ተርጫን ጨምሮ በዋካ ከተሞና በአጎራባች የጌና ወረዳ ውስጥ ነው ፡፡ጠዋት በግምት አንድ ሰዓት ተኩል አካባቢ ከሁለት እስከ ሦስት ሰከንድ የሚደርስ እርግብግቢት መከሰቱን የተናገሩት ሁለት የከተማዋ ነዋሪዎች “ በንዝረቱ የመኖሪያ ቤት ግድግዳዎችና የቤት ዕቃዎች ተንቀጥቅጠዋል ፡፡ አንዳንድ ነዋሪዎችም በደንጋጤ ከቤት በመውጣት ለመሮጥ ሲሞክር ተስተውለዋል “ ብለዋል ፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ መከሰቱን ለዶቼ ቬለ የተናገሩት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ለማ መሠለ “ ያም ሆኖ ንዝረቱ በነዋሪው ላይ ካስከተለው ጊዜያዊ መደናገጥ ውጭ በሰው ሕይወትም ሆነ ንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት አልተመዘገበም “ ብለዋል፡፡

ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና አስትሮኖሚ ተቋም የመሬት መንቀጥቀጥ ባለሙያና ተመራማሪ ዶክተር አታላይ አየለ ዛሬ ጠዋት አንድ ሰዓት ከሃያ አራት ደቂቃ ላይ በዳውሮ ዞን በሬክተር እስኬል 3 ነጥብ 0 የተመዘገብ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ተናግረዋል ሲል ዶቼ ቬለ ዘግቧል ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa