Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 127.33K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2024-04-29 11:01:41 አሜሪካ የራፋህን ጥቃት እንድታስቆም የፍልስጤሙ መሪ ተማጸኑ!

የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ እስራኤል ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች በተጠለሉባት ደቡባዊ የጋዛ ከተማ ራፋህ ላይ ጥቃት ከማድረስ የምታስቆማት ብቸኛዋ አገር አሜሪካ ናት ብለዋል።ከፊል ዌስት ባንክን የሚያስተዳድሩት አባስ ማንኛውም የእስራኤል ጥቃት ፍልስጤማውያን ከጋዛ እንዲሸሹ ሊያደርግ ይችላል ብለዋል።እስራኤል በራፋህ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ደጋግማ እየዛተች ትገኛለች።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እሑድ ዕለት ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት “በራፋህ ላይ ያላቸውን ግልፅ አቋም” በድጋሚ አስታውቀዋል።ሰላማዊ ዜጎችን ከጉዳት ለማዳን የሚያስችል አስተማማኝ ዕቅድ ካላየች በስተቀር አሜሪካ በራፋህ የሚካሄድን መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ መደገፍ እንደማትችል ደጋግማ ተናግራለች።በሳዑዲ ርዕሰ መዲና ሪያድ በተካሄደው የዓለም ኢኮኖሚ ጉባዔ (ደብሊውኢኤፍ) ላይ ንግግር ያደረጉት አባስ አሜሪካ ጣልቃ እንድትገባ አሳስበዋል።

"እስራኤል ይህን ወንጀል እንዳትፈጽም ማድረግ የምትችለው አሜሪካ ብቻ ስለሆነች እስራኤል የራፋህ ዘመቻዋን እንድታቆም እንድትጠይቅ አሜሪካን እንማጸናለን። ራፋህ ላይ የሚደረግ "ትንሽ የሚባል ጥቃት" ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ለመሸሽ እንደሚያስገድድ ተናግረዋል።"በፍልስጤም ህዝብ ታሪክ ውስጥ ትልቁ ጥፋትም ያኔ ይከሰታል።" ብለዋል።ከግማሽ በላይ የሚሆነው የጋዛ ህዝብ በራፋ የሚገኝ ሲሆን በከተማዋ ያለው ሁኔታም የከፋ የሚባል ነው። የተፈናቀሉ ሰዎች የምግብ፣ የውሃ እና የመድሃኒት እጥረት እንዳለባቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ዋይት ሃውስ በራፋህ የሚካሄደውን ዘመቻ በተመለከተ ባይደን ለኔታንያሁ የሰጡትን አስተያየት በተመለከተ በዝርዝር አልገለጸም። የብሔራዊ ደህንነት ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ ለኤቢሲ እንደተናገሩት እስራኤል ወደ አካባቢው ከመግባቷ በፊት የአሜሪካን ስጋቶች እና ሃሳቦችን ለማዳመጥ ተስማምታለች።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ወደ ሪያድ አቅንተው ከአባስ ጋር ሊነጋገሩ መሆኑም ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አዲስ ተስፋ እየፈነጠቀ የመጣው በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የሚደረገው ቀጥተኛ ያልሆነ የተኩስ አቁም ድርድር እና በጋዛ የቀሩትን ታጋቾች የማስለቀቅ ሂደት በእስራኤል ጥምር መንግሥት ውስጥ ያለውን መከፋፈል ይበልጥ እያጋለጠው ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
13.8K views08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-28 18:40:29
የቦንዳ አልባሳት የሀገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያ 53 በመቶ ድርሻ መያዙ ጥናት አመላከተ!

የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ አምራቾች ማህበር በተጠናቀቀው ዓመት አደረኩት ባለዉ ጥናት ለሁለተኛ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚዉሉ ልብሶች በሀገሪቱ ለሚገኙ የጨርቃጨርቅ አምራች ኢንዱስትሪ ገበያውን ይበልጥ ፈታኝ" እንዲሆን እያደረገው እንደሚገኝ ገልጿል።ማህበሩ በዚሁ ጥናቱ በተለምዶ ቦንዳ በሚል መጠሪያ የሚታወቁት አልባሳት የሃገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያን 53 በመቶ ድርሻ መያዛቸዉን አስታዉቀዋል።

እነዚሁ ልብሶች ዋጋቸዉ ዝቅተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በማህበረሰቡ ዘንድ በጥራት የተሻለ ወይም ተቀባይነት ባላቸው አምራቾች የተመረቱ ናቸዉ በሚል አመለካከት ፍላጎቱ ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል።እንደ ጥናቱ ከሆነ በአለም አቀፍ ደረዳ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋሉት አልባሳት ገበያ 71.22 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ እንዳለው እና እኤአ በ2030 ደግሞ ወደ 282.7 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ የአልባሳት ገበያ በአሁኑ ወቅት ከአዉሮፓ እና አሜሪካ በመጡ ርካሽ ልብሶች መሞላታቸዉን በጥናቱ ተመላክቷል።የቦንዳ ልብሶች ወደ ሀገር ዉስጥ በተለያዩ መንገዶች የሚገብ ሲሆን ከእነዚህ ዉስጥ ዋነኛውን ድርሻ የሚይዘው በሞያሌ ፣ በድሬዳዋና በሌሎች የድንበር ከተሞች ከሚባሉት በተጨማሪ በኢትዮጵያ አየር መንግድ በኩል በተለያዩ ሁኔታዎች ሲገቡ ይስተዋላል።

@YeneTube @FikerAssefa
15.6K views15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-28 14:21:37 አየርላንድ ድንበር ተሻግረው የሚመጡ ስደተኞችን ወደ ዩኬ እመልሳለሁ አለች!

የአየርላንድ መንግሥት ከዩናይትድ ኪንግደም የሚመጡ ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችለውን ሕጋዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ጀመረ።የአየርላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ሲሞን ሃሪስ የአገሪቱ ፍትሕ ሚኒስቴር ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችል ሕግ አርቅቆ ለአገሪቱ ካቢኔ እንዲያቀርብ አዘዋል።

ዩናይትድ ኪንግደም በሕገ-ወጥ መልኩ ወደ አገሯ የሚገቡ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እልካለሁ ማለቷን ተከትሎ ዩኬ የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሩዋንዳ ላለመመለስ ሲሉ እንደ አየርላንድ ያሉ አገራትን አማራጭ መዳረሻቸው እያደረጉ ነው።የአየርላንድ የፍትሕ ሚኒስትር ሄለን ማክኤንቲ በቅርቡ ወደ አየርላንድ ከተሻገሩ ስደተኞች መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት መነሻቸው ዩኬ ነው ብለዋል።

የአገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማይክል ማርቲን የዩኬ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ እቅድ ገና ከአሁኑ በአየርላንድ ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ነው ብለዋል።ከቀጥቂት ቀናት በፊት ለበርካታ ወራት ብዙ ሲያወዛግብ የቆየው ወደ ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) በሕገ-ወጥ መንገድ የገቡ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ የሚያስችለውን ሕግ የአገሪቱ ፓርላማ ጸድቆ ሕግ ሆኗል።

ይህ ሕግ ኢንግሊሽ ቻናል ተብሎ በሚጠራው የውሃ አካል በኩል በጀልባ በሕገ-ወጥ መንገድ ዩኬ የደረሱ ስደተኞችን በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ ሩዋንዳ የሚልክ ነው።ስደተኞቹ በዩኬ የሚያቀርቡት የጥገኝነት ጥያቄ የሚታየው ሩዋንዳ ተወስደው ሲሆን፣ የጥገኝነት ጥያቄያቸው አዎንታዊ መልስ የሚያገኝ ከሆነ ስደተኞቹ እዚያው እንዲቆዩ ይፈቀድላቸዋል።

ነገር ግን የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ ከሆነ ደግሞ ስደተኞቹ ሌላ ምክንያት በማቅረብ በሩዋንዳ አልያም በሌላ ሦስተኛ አገር የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ፈጽሞ ወደ ዩኬ መመለስ ግን አይችሉም።ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ሕጉ ተግባራዊ ሆኖ ሐምሌ 2016 ዓ.ም. ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንደሚጀር አስታውቀዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
15.7K views11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-28 14:21:25
ለድርጅትዎ የGOOGLE ማስታወቂያ ማሰራት ይፈልጋሉ?

ማስታወቂያዎት ደንበኛ ሊሆንዎት ከፍተኛ እድል ወዳላቸው ሰዎች(Potential
Customers) እንዲደርስስ?

-ጉግል ሰርች ላይ ለሚመጡ ማስታወቂያዎች፤
-በዩቲውብና ጂሜይል ለሚታዩ ማስታወቂያዎች፤
-በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ላይ የሚታዩ ማስታወቂያዎችን በማሰራት ምርትና አገልግሎትዎን ለማሳደግ ከፈለጉ ያናግሩን።

ከዚህም በተጨማሪ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ኤክስን በመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያ ማሰራትም ይችላሉ።

ቴሌግራም፡ @adsommar
ስልክ፡ 0954260423
14.8K views11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-27 20:05:27
የ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑ ተነገረ!

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተገልጿል።የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ምክክር መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ እንደሆነ ተሰምቷል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ በኦን ላይን ለመስጠት ባይቻልም በሁሉም ክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።በዚህም በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን የሚወስዱ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን ይወስዳሉ ብለዋል።

የሀገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፈተናውን በኦን ላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል። ተማሪዎች የሙከራ ፈተና የሚለቀቅላቸው ሲሆን ደጋግመው እንዲሞክሩና እንዲለማመዱ ይደረጋልም ብለዋል።

ለዚህም እንዲረዳ የአሰልጣኛች ስልጠና በመሥጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሠጣቸውም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮም የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት እንደሚጀምርም በመድረኩ ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
16.2K views17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-27 14:00:15
Ready to empower the next generation of learners? Join us on Edtech Mondays for an eye-opening discussion on Financing EdTech Startups in Ethiopia! Discover how investors are igniting innovation and driving change in the education landscape, overcoming unique challenges to support promising ventures. From bridging the digital divide to enhancing learning outcomes, explore the transformative potential of investing in EdTech startups. Tune in and be part of the movement to revolutionize education in Ethiopia!
Monday, April 29th at 8:10 pm on Fana FM 98.1 for insights that matter.
#EdTechEthiopia #EducationInnovation #JoinTheConversation #Ethiopia
#DigitalLiteracy #TechnologyInEducation #EdTechMondaysEthiopia
#EquityInEducation #Ethiopia #DigitalLiteracy #ShegaMedia #MastercardFoundation
12.7K views11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 13:43:01 በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ቦይንግ በወንጀል እንዲከሰስ ጠየቁ!

በኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ከአምስት ዓመት በፊት ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ለአደጋው መንስዔ የሆነው የአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ላይ የወንጀል ክስ እንዲመሠረት የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤትን ጠየቁ።የመንገደኞቹ ቤተሰቦች በዋሽንግተን ከአሜሪካ የፍትህ ባለሥልጣናት ጋር ሚያዝያ 16/ 2016 ዓ.ም በተነጋገሩበት ወቅት የአሜሪካው ኩባንያ ቦይንግ ለፍርድ እንዲቀርብ ጠይቀዋል።

የተጎጂዎች ቤተሰቦች እና ተወካይ ጠበቆቻቸው ኩባንያው የሚያመርታቸውን አውሮፕላን ምርቶች ደኅንነት እና ጥራት ለማስጠበቅ ከሦስት ዓመት በፊት ከአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ጋር የገባውን የቁጥጥር መርሃ ግብር ጥሷል ብለዋል።

የ157 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈው ከኢትዮጵያው አደጋ በተጨማሪ ለ189 ሰዎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት በሆነው የኢንዶኔዥያ አየር መንገድ አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ቦይንግ በወንጀል እንዲጠየቅ ለፍትህ መሥሪያ ቤቱ ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል።

በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው አሰቃቂ በተባለው በቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን አደጋዎች የ346 ሰዎች ሕይወት አልፏል።በሁለቱ አውሮፕላን አደጋዎች ሕይወታቸውን ያጡ ቤተሰቦች በቅርቡ ንብረትነቱ የአሜሪካ አላስካ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በበረራ ላይ ሳለ መስኮቱ መገንጠሉ ጋር ተያይዞ አሁንም የደኅንነት እና የጥራት ችግር እንዳለበት የሚያሳይ ነው ብለዋል።

የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤት በአውሮፕላንን አምራቹ ላይ ካደረገው የረዥም ጊዜ ምርመራ በኋላ ቦይንግ ለ737 ማክስ አውሮፕላኑ ፍቃድ ለማግኘት ሲል ሆን ብሎ የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ተቆጣጣሪዎችን እንዳሳሰተ ደርሸበታለሁ በሚል “አሜሪካን ለማጭበርበር በማሴር” በሚል ከሦስት ዓመት በፊት ክስ መስርቶበት ነበር።

ቦይንግ ቺካጎ በነበረው የፍርድ ሂደት በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ካሳ ለመክፈል ተስማምቶ በምላሹም የአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት ለአውሮፕላን አምራቹ ከ737 ማክስ ዲዛይን ጉድለት ጋር በተያያዘ በማጭበርበር ሴራ በወንጀል እንዳይከሰስ ከለላ ሰጥቶት ነበር።

የአውሮፕላን አምራቹ በአደጋው ለሞቱት ሰዎች ኃላፊነቱን እንደሚወስድ እና ተጠያቂነቱን ተቀብሎ ለአሜሪካ መንግሥት፣ አደጋ ለደረሰባቸው አየር መንገዶች እና ለተጎጂዎች የሚሆን 2.5 ቢሊዮን ዶላር የቅጣት ካሳ ለመክፈል ተስማምቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
15.4K views10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 12:49:13
በቅርቡ በራሱ ሰራተኞች ጉዳት የደረሰበት የአይደር ሆስፒታል የላብራቶሪ ክፍል አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተነገረ!

የሆስፒታሉ ዳይሬክተር ዶ/ር አብርሃ ገ/እግዚአብሔር እንደተናገሩት ማሽኑ በተለያዮ አቅጣጫዎች ውድመት ደርሶበት ለሁለት ሳምንት ያህል ከአገልግሎት ውጪ እንደነበር ተናግረዋል።ድርጊቱን ፈፅመዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች 4 ግለሰቦች መሆናቸውን እና በቁጥጥር ስር ዉለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ብለዋል።

ተጠርጣሪዎቹም ማሽኑ በነበረበት የስራ ክፍል ላይ ተመሳሳይ የስራ ድርሻ የነበራቸው መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።እስካሁንም ድርጊቱ ለምን እንደተፈፀመ የተደረሰበት ነገር አለመኖሩን እና አሁንም በምርመራ ላይ እንደሆነ አንስተዋል።ድርጊቱ የተፈፀመው መጋቢት 21 ለሊት ሲሆን በሚሊዮኖች የሚገመት ዋጋ ያለው የህክምና መሳሪያ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር የሚታወስ ነው።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
14.8K views09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 09:30:01 ዐቃቤ ሕግ የሽብር ተከሳሾችን ክስ እንዲያሻሽል በተሰጠው ብይን ላይ አቤቱታ አቀረበ!

ዐቃቤ ሕግ፣ በሽብር ወንጀል የተከሰሱትን የእነዶር. ወንድወሰን አሰፋን ክስ አሻሽሎ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤት ዛሬ ኀሙስ በሰጠው ብይን ላይ፣ “ምስክሮቼን ያጋልጥብኛል” በማለት አቤቱታ አቅርቧል፤ የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው ክሱ ካልተሸሻለ እንዲቋረጥ ጠይቀዋል፡፡በተከሳሶቹ የወንጀል ድርጊት “ተገድለዋል” የተባሉ ሰዎች፣ በክሱ ላይ በስም እንዲጠቀሱ ብይን ሰጥቶ የነበረው ፍርድ ቤቱ፣ በዛሬው ክርክር ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን፣ ከተከሳሾች ጠበቆች አንዱ ሰሎሞን ገዛኸኝ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

በእነዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ፣ ሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በዐቃቤ ሕግ የሽብር ክስ የተመሠረተባቸው ተከሳሾች፣ ዛሬ ሚያዝያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ችሎት ቀርበዋል፡፡የዛሬው ችሎት የተቀጠረው፣ ዐቃቤ ሕግ በፍርድ ቤት በታዘዘው መሠረት ክሱን አሻሽሎ ማቅረቡን ለመመልከት ነበር፡፡

የዐቃቤ ሕግ ክስ፣ ተከሳሾቹ በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈጸሙት የሽብር ወንጀል፣ የ217 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ ብዙዎች መጎዳታቸውንና ከፍተኛ ንብረትም መውደሙን ሲያስረዳ፣ በተከሳሽ ጠበቆች ጥያቄ መሠረት፣ ሟቾቹ በስም ተጠቅሰው፣ ሌሎች ጉዳቶችም በዝርዝር ተገልጸው ክሱ እንዲሻሻል፣ ፍርድ ቤቱ ባለፈው ኅዳር 12 ቀን በይኖ ነበር፡፡

ኾኖም፣ ዐቃቤ ሕግ፣ ክሱ እንዲሻሻል የተሰጠው ብይን እንዲሻር በደብዳቤ አቤቱታ አቅርቧል፡፡ ለዚኽም በምክንያትነት ያቀረበው፣ እንደ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ የሟቾቹን ስም መጥቀስ “ምስክሮቹን ለጉዳት የሚዳርግ ነው፤” የሚል እንደኾነ፣ ከተከሳሽ ጠበቆች አንዱ ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ሰሎሞን ገዛኸኝ አስረድተዋል፡፡ጠበቆች በበኩላቸው፣ ዐቃቤ ሕግ የፍርድ ቤቱን ብያኔ አክብሮ ክሱን የማያሻሽል ከኾነ ክሱ እንዲነሣ መጠየቃቸውንም ተናግረዋል፡፡የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው ችሎቱ፣ በጉዳዩ ላይ ትእዛዝ ለመስጠት ለግንቦት 12 ቀን መቅጠሩን፣ ጠበቃ ሰሎሞን ገዛኸኝ አመልክተዋል፡፡

በክስ መዝገቡ ላይ ከተጠቀሱ 51 የሽብር ወንጀል ተከሳሾች መካከል አራት የመገናኛ ብዙኀን ባለሞያዎችን ጨምሮ 23ቱ በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸውን በመከታተል ላይ የነበሩ ናቸው፡፡ ከመካከላቸው አንዱ ለሕክምና እንደወጡ ማምለጣቸውን፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ተወካዮች ከዚኽ ቀደም ለፍርድ ቤት ማሳወቃቸውን ጠበቆቹ ገልጸዋል፡፡ጉዳያቸው በሌሉበት እየታየ የሚገኙ ተከሳሾችን፣ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ውጤቱ ለቀጣዩ ችሎት እንዲቀርብም ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
14.5K views06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 09:25:29
ለድርጅትዎ የGOOGLE ማስታወቂያ ማሰራት ይፈልጋሉ?

ማስታወቂያዎት ደንበኛ ሊሆንዎት ከፍተኛ እድል ወዳላቸው ሰዎች(Potential
Customers) እንዲደርስስ?

-ጉግል ሰርች ላይ ለሚመጡ ማስታወቂያዎች፤
-በዩቲውብና ጂሜይል ለሚታዩ ማስታወቂያዎች፤
-በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ላይ የሚታዩ ማስታወቂያዎችን በማሰራት ምርትና አገልግሎትዎን ለማሳደግ ከፈለጉ ያናግሩን።

ከዚህም በተጨማሪ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ኤክስን በመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያ ማሰራትም ይችላሉ።

ቴሌግራም፡ @adsommar
ስልክ፡ 0954260423
14.0K views06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ