Get Mystery Box with random crypto!

በቅርቡ በራሱ ሰራተኞች ጉዳት የደረሰበት የአይደር ሆስፒታል የላብራቶሪ ክፍል አገልግሎት መ | YeneTube

በቅርቡ በራሱ ሰራተኞች ጉዳት የደረሰበት የአይደር ሆስፒታል የላብራቶሪ ክፍል አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተነገረ!

የሆስፒታሉ ዳይሬክተር ዶ/ር አብርሃ ገ/እግዚአብሔር እንደተናገሩት ማሽኑ በተለያዮ አቅጣጫዎች ውድመት ደርሶበት ለሁለት ሳምንት ያህል ከአገልግሎት ውጪ እንደነበር ተናግረዋል።ድርጊቱን ፈፅመዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች 4 ግለሰቦች መሆናቸውን እና በቁጥጥር ስር ዉለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ብለዋል።

ተጠርጣሪዎቹም ማሽኑ በነበረበት የስራ ክፍል ላይ ተመሳሳይ የስራ ድርሻ የነበራቸው መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።እስካሁንም ድርጊቱ ለምን እንደተፈፀመ የተደረሰበት ነገር አለመኖሩን እና አሁንም በምርመራ ላይ እንደሆነ አንስተዋል።ድርጊቱ የተፈፀመው መጋቢት 21 ለሊት ሲሆን በሚሊዮኖች የሚገመት ዋጋ ያለው የህክምና መሳሪያ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር የሚታወስ ነው።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa