Get Mystery Box with random crypto!

በየአካባቢው የቁም እንስሳት ቅርጫ ማረድ አለመከልከሉ ተገለጸ! በአዲስ አበባ ከተማ የትንሳኤ በ | YeneTube

በየአካባቢው የቁም እንስሳት ቅርጫ ማረድ አለመከልከሉ ተገለጸ!

በአዲስ አበባ ከተማ የትንሳኤ በዓል ህብረተሰቡ በየቤቱ እና በየአካባቢው የቁም እንስሳትን ቅርጫ ማረድ አለመከልከሉን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው ለትንሳኤ በዓል ህብረተሰቡ በየቤቱ እና በየአካባቢው የቁም እንስሳትን ቅርጫ ማረድ ተከልክሏል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን አስታውቋል።

በየአካባቢው በህገ ወጥ መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የሚገኙ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የከተማውን ነዋሪ ጤንነት ላይ ጉዳት ስለሚያደርስ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግም ቢሮው ባወጣው መረጃ አመላክቷል።

የከተማው ነዋሪ በዓላትን ሽፋን በማድረግ ጤንነቱ ያልተረጋገጠ እንስሳት አርዶ ማከፋፈል በጤና ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ግምት ውስጥ በማስገባት በህገወጥ እርድ የሚሰማሩ አካላት በሚደረገው ቁጥጥር ተባባሪ እንዲሆን አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa