Get Mystery Box with random crypto!

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

የሰርጥ አድራሻ: @abiyahmedaliofficial
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 115.42K
የሰርጥ መግለጫ

ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!
Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!
Freedom to our People – Prosperity to our Nation!

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-06-15 14:02:58
እንኳን ለ2016 የዒድ አል አድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

የኢድ አል አድሃ በዓል የፈተናና የመሥዋዕትነት በዓል ነው፡፡ ነቢዩ ኢብራሂም በአላህ ትእዛዝ ልጃቸውን ለመሥዋዕትነት ያዘጋጁበት፤ ጽናታቸው ተፈትኖ ያሸነፉበት በዓል ነው፡፡ ለዚህ ጽናታቸውም ከአላህ ዘንድ ምትክ በግ ያገኙበት በዓል ነው፡፡
ከዚህ በዓል የምንማራቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ማንኛውም ፈተና በጽናት ካለፉት ዋጋው ከፈተናው በላይ መሆኑን እንማርበታለን፡፡ ልጅን ያህል ነገር እንዲሠዉ መጠየቅ ከባድ ፈተና ነው፡፡ ልጅን ለመሥዋዕትነት ማዘጋጀት ደግሞ ከባድ ጽናት ነው፡፡ ከባድ ፈተና ከባድ ቆራጥነት ይፈልጋል፡፡ ከባድ ቆራጥነት ከባድ ውሳኔን ይጠይቃል፤ ከባድ ውሳኔም ታላቅ ዋጋን ያስገኛል፡፡
ኢትዮጵያን ታላቅና የበለጸገች ሀገር ለማድረግ ስንነሣ ፈተናው ከባድ እንደሚሆን እናምን ነበር፡፡ ሳይፈቱ የተከማቹ ሀገራዊ ችግሮች አሉ፡፡ በዘመናችን የተፈጠሩ አሁናዊ ችግሮችም አሉ፡፡ እነዚህ ሁለቱን በአንድ ጊዜ መጋፈጥ ይጠይቀን ነበር፡፡ ተራራውን መጋፈጥ ሳይሆን ተራራውን ማንሣት ይጠይቀን ነበር፡፡ ይሄንን ፈተና ለመጋፈጥ ከባባድ ውሳኔዎችን መወሰን ይገባን ነበር፡፡ እንደ ልጅ የምንወዳቸውን ሰዎች፣ ነገሮች፣ ቡድኖች፣ ወዳጆችና አካሄዶች ለመሠዋት መወሰን ነበረብን፡፡ መወሰን ብቻ ሳይሆን ማድረግም ነበረብን፡፡
ነቢዩ ኢብራሂም ልጃቸው ኢስማኤልን ሳይሆን በምትኩ ከአላህ የተሰጣቸውን በግ ሠዉተዋል፡፡ የእኛ ፈተና ከዚህም የባሰ ነበር፡፡ ሀገራችን ባከማቸቻቸው ዕዳዎችና ስብራቶች የተነሣ፣ ያለን አማራጭ የራሳችንን ነገር መሠዋት ብቻ ነበር፡፡ ሀገራችንን ለማዳን፣ የሕዝባችንን ዘላቂ ጥቅሞች ለማስከበር እና ከዛሬው የተሻለ ነገን ለመፍጠር ስንል፣ ብዙ ነገሮችን ሠዉተናል፡፡
ችግሮቻችን ቀስ ብለን እንድንሄድ አይፈቅዱልንም፡፡ በጥንቃቄ እንድንሮጥ እንጂ፡፡ የልማት ጥያቄዎቻችንን ለመመለስ እንደ ሕዝብ ሁላችንም የምንወዳቸውን ነገሮች ሠዉተናል፡፡ ከምንወደው አካባቢ ወደ ሌላ ሄደናል፡፡ ትዝታዎቻችንን ሠዉተናል፡፡ የባንዳውን ጩኸት ችለናል፤ ሀገርን ለመለወጥ ስንል ቤቶቻችንና ሕንጻዎቻችን እንዲፈርሱ ፈቅደናል፡፡ የመብራትና የውኃ መጥፋትን ታገሠናል፤ የመንገድ መዘጋትንና የአካባቢ መፈራረስን ተቀብለናል፡፡ ያለ መሥዋዕትነት የሚያድግ ሕዝብ፣ ያለ መሥዋዕትነት የሚበለጽግ ሀገር የለም፡፡ የኮሪደር ልማቱን በዚህ መልኩ በመሥዋዕትነት ነው የሠራነው፡፡ ፍሬው ግን እጅግ ጣፋጭ መሆኑን አይተናል፡፡
ሰላማችንን ለማስፈን በዚሁ መንገድ ነው መቀጠል ያለብን፡፡ ነፍጥን መጣል፤ ከጫካ መውጣትና የራስን ዋሻ ትቶ ወደ መስኩ መውጣትን ይፈልጋል፡፡ የራስን ኢጎ መሠዋትን ይጠይቃል፡፡ ምቾትንና ፍላጎትን መተዉን ይፈልጋል፡፡ ከመቀበል በላይ መስጠትን ይሻል፡፡ እንደ ኢብራሂም በጣም የምንሳሳለትን ነገር ለመሠዋት መቁረጥ ይፈልጋል፡፡ ሁላችንም ለመሥዋዕትነት ከተዘጋጀን የማይሳካ የሰላም መንገድ የለም፡፡ እንደ ልጅ ያሳደግናቸው ብዙ ልማዶች፣ ጠባዮች፣ አመለካከቶች፣ ርእዮተ ዓለሞችና አካሄዶች አሉን፡፡ እነርሱን ለሀገርና ለሕዝብ ጥቅም ስንል ለመሠዋት ዝግጁ ከሆንን፣ ውጤቱ ከሰላም በላይ ነው፡፡
ምክክር የሚሳካው የተሻለ ሐሳብና የላቀ ዕውቀት በማዋጣት ብቻ አይደለም፡፡ የተሻለ ሐሳብና የላቀ ዕውቀት ስላለን ብቻ የሠመረ ውጤት አናገኝም፡፡ ሌላ ወሳኝ ነገር ይፈልጋል፡፡ እርሱም መሥዋዕትነት ነው፡፡ የራስን ፍላጎት ለመሠዋት መቻል አለብን፡፡ ለትልቅ ግብ ሲባል ይቅርብኝ ማለት አለብን፡፡ ከእኔ የተሻለ ሐሳብና ልምድ፣ ዕውቀትና ጥበብ ሊኖር ይችላል ብለን ማመንና መቀበል አለብን፡፡ ለተሻለው ሐሳብ መገዛት አለብን፡፡ ልክ ልኩን ከመንገር፤ ነጥብ ከማስቆጠር፤ ጀግና ጀግና ከመጨዋት የወጣ ትኁት ሰብእና መያዝ አለብን፡፡ ይሄ ሁሉ መሥዋዕትነትን ይጠይቃል፡፡ እንደ ነቢዩ ኢብራሂም ያሳደግናቸውን ብቻ ሳይሆን አብረውን ያደጉትን ብዙ ጠባዮች ለመሠዋት መዘጋጀትን ይጠይቃል፡፡ መሥዋዕትነት የሚከፍሉ ዜጎች በበዙ ቁጥር፣ ምክክር የላቀ ውጤት ያስገኛል፡፡
የኮሪደር ልማታችን በየከተሞቻችን እንዲስፋፋ፤ ሰላማችን የጸና እና የማይደፈርስ እንዲሆን፤ ሀገራዊ ምክክሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ተካሂዶ እንዲሳካ - ያሳደግናቸውንና ያደጉብንን አንዳንድ ነገሮች መሥዋዕት ለማድረግ እንዘጋጅ፡፡ ሐሳቦቻችን ትጥቅ ይፍቱ፡፡ ከመተኮሻ ወደ ማረሻ እንመለስ፡፡ ከጠመንጃ ወደ ማጨጃ እንዛወር፡፡ ከዲሞትፈር ወደ ምክክር እንምጣ፡፡ ከብሔር ግጭት ወደ ሐሳብ ፍጭት እንሻገር፡፡ የምንወደውን፣ የምንፈልገውንና ያሳደግነውን እንኳን ቢሆን - ለሀገር ስንል ለመሠዋት እንዘጋጅ፡፡
መልካም በዓል ይሁን፡፡

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ስኔ 8 ቀን 2016 ዓ.ም
17.4K views11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-13 11:47:50
ዛሬ ጠዋት የጂቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሃሙድ አሊ ዩሱፍ መልዕክት ከፕሬዚዳንት እስማኤል ዑማር ጉሌ ይዘው መጥተዋል በጽሕፈት ቤታችን ተቀብያለሁ። እንዲህ ያሉት ግንኙነቶች በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ለንግግር እና ትብብር አውታር በመሆን የጋራ መግባባትን ያሳድጋሉ።

I welcomed this morning Mahamoud Ali Youssouf, the Foreign Minister of Djibouti, to my office this morning. Minister Youssouf came bearing a message from President Ismail Omar Guelleh. Such exchanges serve as vital channels for dialogue and cooperation, fostering mutual understanding and collaboration on bilateral and regional matters of shared interest.
8.1K views08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-11 10:47:10
ዛሬ ጠዋት የዘንድሮው የበጀት አመት ከመጠናቀቁ በፊት የመጨረሻ የሆነውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት የመቶ ቀናት ግምገማ ጀምረናል። እንደሁልጊዜው የየሴክተሮችን አፈፃፀም እንገመግማለን። ክፍተቶችን እናጤናለን፤ በጥንካሬዎች ላይ ለቀጣይ ስራዎች እንነሳለን።
We convened this morning for the 100-day Council of Ministers evaluation, the last one before the end of the current budget year. As always, we will review sectoral performance to assess gaps and build on strengths.
21.0K views07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-10 19:55:52
መዲናችንን ቃል በገባነው መሰረት እንደስሟ አበባ እያደረግን ነው ፤ በዚህ ስራ ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋና አቀርባለሁ
22.9K views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-10 18:55:13
ውብ አዲስ አራዳ፣
አዲስ ጽጌሬዳ::

እሪ ሰሚ ሲያገኝ
22.7K views15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-10 18:07:36
ውብ አዲስ አራዳ፣
አዲስ ጽጌሬዳ::

አራት ኪሎ ተኳኩሎ፣ ሰባ ደረጃ ተሻሽሎ
23.4K views15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-10 14:31:49
ውብ አዲስ አራዳ፣
አዲስ ጽጌሬዳ::

ግምቦች ጌጠኛ...ጎዳናው ጤነኛ
23.4K views11:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-10 08:29:12
24.2K views05:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-08 21:29:02
በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት በአሸናፊ ከበደ የክዋኔ ጥበባት ማዕከል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በመታደሜ ደስ ብሎኛል። አሸናፊ ከበደ ከያኒ ብቻ ሳይሆን የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት የመጀመሪያው ዳይሬክተር ነበር። የአዲሱ ማዕከል ዳይሬክተር ግርማ ይፍራሸዋ ደግሞ በቀደመው እና በአሁኑ የኢትዮጵያ ሙዚቃ መካከል ድልድይ በመሆን ያገለግላል። ይህን መሰል ድልድይነት እና ቀጣይነት በሁሉም ተቋሞቻችን አስፈላጊ ነው። ሙዚቃ ኃይል አለው። ይህን ኃይል ለወጣቶቻችን አብርሆት ልንጠቀምበት ይገባል። ጥበባት መጪውን ትውልድ ቅርጽ በማስያዝ እና የከተማችንን የቱሪዝም መስሕብ በማላቅ ከፍ ያለ ሚና ይጫወታሉ። ይህን ዐቅም በምሉዕነት መጠቀም ይገባናል።

I am pleased to witness the inauguration of the Ashenafi Kebede Performing Arts Center at the Yared School of Music. Ashenafi Kebede was not only an artist but also the first director of the Yared Music School. The new center’s director, Girma Yifrashewa, serves as a bridge between the past and the future of music in Ethiopia. Such continuity and linkage are essential in all our institutions. Music is powerful, and we must use this power to enlighten our youth. The arts play a vital role in shaping future generations and enhancing our city’s capacity to attract tourism. We must fully utilize this potential.
11.2K views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-07 18:51:26
Singapore ቆይታ
20.9K views15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ