Get Mystery Box with random crypto!

የ ‘ገበታ ለሀገር’ ሎጆችን የማስተዳደር ኃላፊነት ለስካላይት ኢትዮጵያ ሆቴል ተሰጠ! በጠቅላይ ሚ | YeneTube

የ ‘ገበታ ለሀገር’ ሎጆችን የማስተዳደር ኃላፊነት ለስካላይት ኢትዮጵያ ሆቴል ተሰጠ!

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለተከናወኑት የ'ገበታ ለሀገር' ፕሮጀክቶች ከዛሬ ጀምሮ ለክልል መንግስታት ተላልፈው መሰጠታቸው ተገለጸ።የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ይፋ ካደረገው መረጃ አዲስ ማለዳ እንደተመለከተችው ፕሮጀክቶቹ ለአማራ፣ ለኦሮሚያ እና ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት ተሰጥተዋል።

እንዲሁም በ'ገበታ ለሀገር' የተገነቡ ሎጆችን ስራ የማስኬድ ኃላፊነት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ስር ለሚገኘው ስካይ ላይት ሆቴል እንዲወስድ ስምምነት መፈረሙ ተመላክቷል።

በዚህም እስካሁን የተጠናቀቁት ሃላላ ኬላ ሎጅ፣ ጨበራ ጩርጩራ የዝሆን ዳና ሎጅ እና ወንጪ ኢኮ ሎጅ በስካይላይት ሆቴል የሚተዳደሩ ይሆናል። የጎርጎራ ፕሮጀክት ስራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ተብሏል።ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሰጠው ኃላፊነት የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ እና ለዓለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻነት ትውውቅ ከፍ ያለ ዕድል ስለሚፈጥር እንደሆነ ተመላክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa