Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 125.42K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 480

2021-02-13 21:43:07 የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ክልል ጾታዊ ጥቃትን ጨምሮ ተፈጽመዋል ላላቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መንግሥት ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ እና ወንጀለኞችንም ለፍርድ እንደሚያቀርብ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡ መንግሥት የሰብዓዊ መብት ጥበቃን ለማሻሻል ቁርጠኛ እንደሆነም ሚንስቴሩ ገልጧል፡፡ ኮሚሽኑ እየሰራ ያለው ሥራ የሀገሪቱ ፖለቲካዊ ለውጥ ፍሬ እያፈራ መሆኑን ያሳያል በማለትም አክሏል ሚንስቴሩ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
19.6K views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 19:47:30
በርሀብ አድማ ላይ የሚገኙት የእነ አቶ ጃዋር መሃመድ እና አቶ በቀለ ገርባን የሚከታተል የግል ሃኪሞቻቸው ቡድን ሲያደርግላቸው የቆየውን የህክምና ክትትል ማቆሙን አስታውቋል።

የህክምና ቡድኑ አስተባባሪ ዶ/ር ኢሊሊ ጀማል ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት የህክምና ክትትሉን ከትናንት ምሽት ጀምሮ ለማቆም የተገደዱት በማረሚያ ቤት እና በታካሚዎች በኩል ያለው ፍላጎት ባለመጣጣሙ ነው ብለዋል፡፡ ማረሚያ ቤቱ ወደ መንግስት ህክምና ማዕከል እንዲወሰዱ ፍላጎት ሲያሳይ ታካሚዎች ደግሞ በግል ሆስፒታል ለመታየት በመፈለጋቸው ቡድኑ ህክምናውን መስጠት አለመቻሉም ተገልጿል። 

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
16.0K views16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 19:19:29
ድራጊ አዲሱ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሃላ ፈጸሙ!

ማሪዮ ድራጊ አዲሱ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሃላ ፈጸሙ፡፡የቀድሞው የአውሮፓ ማዕከላዊ ባንክ ፕሬዝዳንት ጁሴፔ ኮንቴን ተክተው ጣሊያንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ለመምራት ቃለ መሃላ የፈጸሙት በፕሬዝዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ ጥሪ ነው፡ማታሬላ የህግ ፕሮፌሰሩ ኮንቴ በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣን ለመልቀቅ መጠየቃቸውን ተከትሎ ነው ድራጊን መንግስት እንዲያዋቅሩ የጠሩት፡፡ድራጊም መንግስት ለማዋቀር የሚያስችል የካቢኔ አባላት ምርጫ ማድረጋቸውንም ገልጸዋል፡፡በፋይቭ ስታር ሙቭመንት እና በሊግ ኋላ ላይ ደግሞ በፋይቭ ስታር ሙቭመንት እና በዴሞክራቲክ ፓርቲ ጥምረት በሁለት የተለያዩ ጊዜያት የተመሰረቱ መንግስታትን በገለልተኛነት ተመርጠው የመሩት ኮንቴ ጣሊያንን ላለፉት 4 ዓመታት መርተዋል፡፡ሆኖም በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የገቡበት ፖለቲካዊ ቅርቃር በስልጣን ሳያስቀጥላቸው ቀርቷል፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
18.5K views16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 18:54:36
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በቀጣዩ ሃገር አቀፍ ምርጫ እንደሚወዳደር አስታወቀ፡፡

ምርጫውን በተመለከተ ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ቆታ ያደረጉት የፓርቲው ሊቀመንበር መረራ ጉዲና (ፕ/ር) በመጪው ሃገራዊ ምርጫ እንደሚወዳደሩ አስታውቀዋል፡፡

ሆኖም በምርጫው የመወዳደራቸው ሁኔታ በመንግስት የሚወሰን ነው እንደ ሊቀመንበሩ ገለጻ፡፡ ሊወዳደሩ የሚችሉባቸውን ቅድመ ሁኔታዎችንም አስቀምጠዋል፡፡

ምርጫው ነጻና ፍትሃዊ እንዲሆን “የምናነሳቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች አሉን” የሚሉት መረራ “መንግስት ካላስወጣን በስተቀር ከምርጫው አንወጣም” ሲሉ ይናገራሉ፡፡

መሰረታዊ የሚሏቸውን ጥያቄዎች ምንነት በተመለከተ ሲያብራሩም በሺዎች የሚቆጠሩ አባልና ደጋፊዎቻችን እንዲሁም ከፍተኛ አመራሮቻችን ታስረዋል ይላሉ፡፡

ዘገባው የአልዐይን ነው፣ ዝርዝሩን ለማንበብ

https://am.al-ain.com/article/we-won-t-miss-the-election-unless-gov-t-compel-us-prof-merera-gudina

@YeneTube @FikerAssefa
14.0K views15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 17:13:58 መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በመቀበል የመማር ማስተማሩን ሥራ መጀመሩን አስታወቀ።

የዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር ከሰተ ለገሰ፣ የመማር ማስተማሩን ሥራ የጀመሩት ከሚጠበቁት 13ሺህ ተማሪዎች ውስጥ አብዛኛዎቹን በመቀበል ላይ መሆኑንና የቀሩትንም እየገቡ ይገኛሉ ብለዋል።

ተማሪዎቹ በመቀሌ ማኅበረሰብ እና ተማሪዎች ኅብረት አቀባበል እየተደረገላቸው ከየካቲት 1 ቀን 2013 ዓ.ም አንሥቶ ትምህርታቸውን መከታተል መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

የተማሪዎች መማሪያ ክፍሎች፣ መኝታ ቤቶች፣ ምግብ ማብሰያ እና መመገቢያ አዳራሾችን የኮሮና ወረረሽኝን ለመከላከል ታሳቢ ባደረገ መልኩ ቀድመው መሰናዳታቸውን ዶ/ር ከሰተ አስረድተዋል።

ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ዓመት ድረስ የሚማሩት እነዚህ ተማሪዎቹ የተቋሙን ሕግ እና ሥርዓት አክብረው ትምህርታቸውን መከታታል እንደሚጠበቅባቸውም ገልጸዋል።

ትምህርታቸው መከታተል ከጀመሩት መካከል ከደቡብ ክልል የመጣው የአዲሀቂ ካምፓሰ የሶሾሎጂ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ ቸርነት ሺፈራው ትምህርት በመጀመሩ መደሰቱን ገልጾ፣ በንጹሕ መጠጥ ውኃ አቅርቦት በኩል ግን እጥረት ስላለ እንዲስተካከል አስተያየቱን ሰጥቷል።

የእኛ ተማሪዎች ሕልም በሰላም እና ፍቅር ትምህርታችንን መከታተል እና ተመርቀን ራሳችንና ሀገራችን መጥቀም ነው ያለው ደግሞ የሁለተኛ ዓመት ሶሾሎጂ ተማሪ እንድሪስ አብዱ ነው።

ከኦሮሚያ ክልል የመጣው ተማሪ ጫላ ሳፋይ በበኩሉ ዩኒቨርሲቲው ለመማር ማስተማር የሚያስችል የግቢው መሠረተ ልማት ማሟላቱን ገልጿል።

በምግብ ሰዓት ግን በወረፋ ብዛት ምክንያት ለብዙ ሰዓታት እየጠበቅን መሆኑን ታውቆ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል ማለቱን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
17.3K views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 16:29:32
በአዲስ አበባ በሕገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ ከ2 ሚሊየን ጄሪካን በላይ ፓልም የምግብ ዘይት ተያዘ!

በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ጀሞ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በልዩ ስሙ አንበሳ ጋራዥ በሚባለው ቦታ በሕገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ ከ2 ሚሊየን ጄሪካን በላይ ፓልም የምግብ ዘይት ዛሬ ተይዟል፡፡

በሕገ ወጥ መንገድ የተከማቸው ዘይት ሊያዝ የቻለው ፌዴራል ፖሊስ እና የላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከህብረተሰቡ የደረሳቸውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ለ2 ሳምንታት ባደረጉት ጥብቅ ክትትል መሆኑን ኢብኮ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
16.9K views13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 15:10:32
በሶማሊያ በፕሬዘዳንታዊ ቤተመንግስት አካባቢ አጥፍቶ ጠፊ ጉዳት አደረሰ!

በሶማሊያ ሞቃዲሹ በፕሬዘዳንታዊ ቤተመንግስት አካባቢ አንድ አጥፍቶ ጠፊ ባፈነዳው ቦንብ ራሱ ሲሞት ሌሎች ሰባት ንጹሃን መቁሰላቸውን ፖሊስ ገልጿል፡፡ የፖሊስ ቃል አቀባይ ሳዲቅ አሊ አሽከርካሪው እንዲቆም ሲጠየቅ ተባባሪ ባለመሆኑ ፖሊስ ተኩስ መክፈቱን ተናግረዋል፡፡በፍንዳታው ከ10 በላይ የሚሆኑ ተሽከርካሪዎች በፍንዳታው መውደማቸውን ፖሊስ አስታውቋል፡፡በሶማሊያ ለመጨረሻ ጊዜ ቦንብ የፈነዳው የሶማሊያ ፖለቲከኞች እንዴት ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ እንናካሂድ የሚል ክርክር ባሰሙበት ወቅት ነው፡፡ምርጫው በፈረንጆቹ የካቲት 8 ቀነ ቀጠሮ ተይዞለታል፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
13.2K views12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 13:31:42 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የዕጩዎች ምዝገባ ማከናወን የተራዘመባቸው ክልሎችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት ለ6ተኛው ሀገር ዐቀፍ ምርጫ የተለያዩ ተግባራትን እየፈጸመ እንደሆነ ይታወቃል።

ቦርዱ በማቋቋሚያ ዐዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ (1) እና የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 37 ንዑስ አንቀጽ (7) እና አንቀፅ 163 ንዑስ አንቀፅ (2) ላይ በተሰጠው ሥልጣን ባወጣው የዕጩዎች ምዝገባ መመሪያ መሠረት፤ የዕጩዎችን ምዝገባ ለማከናወን የሚያስችሉትን ከክልል መስተዳድሮች እና ከከተማ መስተዳድሮች የሚጠበቁ የትብብር ግዴታዎችን ለሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ገልፆ ዝግጅቶችን እያደረገ እንደነበር ይታወቃል።

በዚህም መሰረት የክልሎች ዝግጁነት ምን እንደሚመስል ሰኞ የካቲት 01 ቀን 2013 ዓ.ም ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

በመግለጫውም
• አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር
• ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
• ድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር
• ጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
• ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና
• ሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስፈላጊ የሆኑትን ለምርጫ ክልል እና ለዞን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሊያገለግሉ የሚችሉ ቢሮዎችን አዘጋጅተው ለቦርዱ እንዳስታወቁ በመግለጽ፤ በጊዜ ሠሌዳው በተቀመጠው ቀን መሠረት ከየካቲት 08 እስከ የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም. የዕጩ ምዝገባ የሚከናወነው ከላይ በተጠቀሱት ክልልሎች በሚገኙ የምርጫ ክልል ቢሮዎች መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን በቀሪዎቹ ክልሎች የክልል መስተዳድሮቹ ደግሞ አስፈላጊውን ትብብር ሲያደርጉ ምዝገባው የሚጀመርበትን ቀን ቦርዱ የሚያሳውቅ ገልፆ ነበር።

መሆኑን በዚሁ መሠረት እጩ ምዝገባ በማይጀመርባቸው ቀሪ ክልሎቹ የሚካሄዱት የዕጩዎች ምዝገባ ሂደት እንደሚከተለው ይሆናል፤
• አፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
• አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
• ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
• ደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት እና
• ሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከየካቲት 05 እስከ የካቲት 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ለዕጩዎች ምዝገባ የሚውሉ ቁሳቁሶች የሚጓጓዙበትና የዕጩዎች ምዝገባ አስፈጻሚዎች ሥልጠና የሚሰጥበት ጊዜ ሲሆን፤ ከየካቲት 15 እስከ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ደግሞ የዕጩዎች ምዝገባ የሚከናወንበት ጊዜ እንዲሆን ቦርዱ ወስኗል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የካቲት 06 ቀን 2013 ዓ.ም
@YeneTube @FikerAssefa
16.7K views10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 12:59:54
ፕሬዘዳንት ባይደን የ“ጓንታናሞ” እስርቤትን ለመዝጋት ማቀዳቸውን ኋይት ኃውስ አስታወቀ!

የቀድሞው ፕሬዘዳንት ትራምፕ በ2016 የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የጓንታናሞ ባይ እስርቤትን በስራ ላይ እንደሚቆይና በ “መጥፎ ሰዎች” እንደሚሞላ ገልጸው ነበር።

ኋይት ኃውስ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን የስልጣን ዘመናቸው ከማብቃቱ በፊት በሽብር የተጠረጠሩ ግለሰቦች የሚታሰሩበትን የጓንታናሞ ባይ እስርቤትን የመዝጋት አላማ እንዳላቸው አስታውቋል፡፡

 መቼ ይዘጋል ተብሎው በጋዜጠኞች የተጠየቁት የኋይት ኃውስ ፕሬስ ሴክሬታሪ“ያ እርግጠኛ ግብ ነው፤ ፍላጎታችን ነው” የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡ፕሬስ ሴክሬታሪዋ እንዳሉት አስተዳደሩ የባይደን አስተዳደር ያለበት መጫውቻ ምን እንደሚመስልና ከበፊቱ አስተዳደር ምን ወርሷል የሚለውን ለማወቅ ዳሰሳ እየተካሄደ ነው ብለዋል፡፡

[አል ዐይን]
@YeneTube @FikerAssefa
16.4K views09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 10:11:13
የጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ቀብሪ ደሀር ፣ ወለጋ እና አርሲ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቻቸውን አስመረቁ፡፡

ጅማ ዩኒቨርስቲ እና ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል፡፡

ጅማ ዩኒቨርስቲ በሁለተኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ያሠለጠናቸውን 4ሺህ 311 ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 3ሺህ 950 በመጀመሪያ ዲግሪ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 1ሺህ 530 ሴቶች ናቸው።

በሁለተኛ ዲግሪ ደግሞ 45 ሴቶች የሚገኙበት 354 ተማሪዎች ተመርቀዋል፡፡

በተጨማሪም ሶሰት ተማሪዎች በሶስተኛ ዲግሪ እና አራት ተማሪዎች ደግሞ የ “ሰብ ስፔሻሊቲ” ተመራቂ ይገኙበታል፡፡

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ጥቅምት ወር 1ሺህ 409 ተማሪዎችን ማስመረቁ ይታወሳል፡፡

ወለጋ ዩኒቨርሲቲም በተመሳሳይ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 3ሺህ 398 ተማሪዎችን ዛሬ በወለጋ ስታዲየም አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል የመጀመሪያ ዲግሪ 3 ሺህ 13፣ በሁለተኛ ዲግሪ 344፣ በህክምና ዶክትሪት 40 እና የአካዳሚክ ዶክተር በአጠቃላይ 3 ሺህ 398 ናቸው።

ቀብሪ ደሀር ዩኒቨርሲቲም የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ እና ሌሎች የክልልል እና የፌዴራል የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 612 ተማሪዎቹን አስመርቋል፡፡

አርሲ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ በህክምና ስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 23 ሰልጣኞቹን በመጀመሪያ ዙር አስመርቋል፡፡

በተመሳሳይም የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸው 2 ሺህ 39 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
16.6K views07:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ