Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 125.42K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 479

2021-02-15 10:28:17 አዲስ አበባ እና ድሬዳዋን ጨምሮ በአራት ክልሎች የዕጩዎች ምዝገባ ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ኦሮሚያ እና ሐረሪ ክልሎች የዕጩዎች ምዝገባ ዛሬ ይጀመራል።

ምዝገባው የሚከናወነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዕጩዎች ምዝገባ ባወጣው ከየካቲት 08 እስከ የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ነው።

የምርጫ ክልሎቹ በተጠቀሱት ጊዜያት የዕጩዎች ምዝገባ የሚያከናውኑት ለምርጫ ክልል እና ለዞን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሊያገለግሉ የሚችሉ ቢሮዎችን በማዘጋጀታቸው መሆኑን ቦርዱ ገልጿል።

በአፋር፣ አማራ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ እና ሶማሌ ክልሎች ከየካቲት 05 እስከ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ለዕጩዎች ምዝገባ የሚውሉ ቁሳቁሶች እንደሚጓጓዙ እና የዕጩዎች ምዝገባ አስፈጻሚዎች ሥልጠና እንደሚሰጥም ቦርዱ አመልክቷል።

ከየካቲት 15 እስከ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ደግሞ የዕጩዎች ምዝገባ እንደሚከናወን ቦርዱ ባለፈው ሳምንት መወሰኑ ይታወሳል።

Via:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa
13.3K views07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-15 10:15:59 አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ እና ጌትነት ዋለ በፈረንሳይ የተካሄደውን የቤት ውስጥ ሻምፒዮን በበላይነት አጠናቀቁ

በፈረንሳይ ቫል ዴ ሪዩል በተካሄደው የቤት ውስጥ ሻምፒዮና አትሌት ጉዳግፍ በዚያው በፈረንሳይ ክብረ ወሰን ከሰበረች በሳምንት ውስጥ ሁለተኛ ድሏን 800 ሜትር አሸንፋለች።
አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ እ.አ.አ ከ2006 ወዲህ ርቀቱን 1:57.52 በሆነ ጊዜ የአለም ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ነው ለማሸነፍ የቻለችው።
አትሌት ጌትነት ዋለ ደግሞ በ1500 ሜትር የመሰናክል ሩጫ ለሜቻ ግርማን አስከትሎ በመግባት ሌላ አንጸባራቂ ድል አስመዝግቧል።
አትሌት ጌትነት ዋለ 1500 ሜትሩን በ3:35.54 ጊዜ ሲጨርስ ፣ አትሌት ለሜቻ ግርማ ደግሞ 3:35.60 በሆነ ጊዜ ሁለተኛ ሆኖ በማጠናቀቅ የሳምንቱን ድል ለኢትዮጵያ ያማረ እንዲሆን አድርጎታል።

Via: EBC
@Yenetube @Fikerassefa
8.9K viewsedited  07:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-15 10:05:51
ቻይና የለገሰችው የመጀመሪያው ዙር የኮሮና ቫይረስ ክትባት ዛሬ ጠዋት ዚምባብዌ ዋና ከተማ ሐራሬ መግባቱ ተሰምቷል፡፡

የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ኮንስታቲኖ ቺዌንጋ፤ ሮበርት ጋብሬል ሙጋቤ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን በመገኘት ድጋፉን ተቀብለዋል፡፡

ከምክትል ፕሬዚዳንቱ በጨማሪ በዚምባብዌ የቻይና አምባሳደርም ተገኝተዋል፡፡

ቻይና የለገሰችው የኮሮና ቫይረስ ክትባት 200 ሺህ መጠን ያለው ነው ተብሏል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ክትባቱ የበለጸገው ሲኖፋርማ በተባለው የሀገሪቱ ብሔራዊ የመድኃኒት አምራች ኩባንያ መሆኑም ተነግሯል፡፡
 
ምንጭ፡-ሲጂቲኤን
@Yenetube @Fikerassefa
13.3K viewsedited  07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-15 09:57:45
ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል የምርጫ 2013 የብልጽግና ፓርቲ ማኒፌስቶ እና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ይፋዊ የእውቅና መድረክ በሸራተን አዲስ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የዕውቅና መድረኩን በእንኳን ደህና መጣችሁ የከፈቱት የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ብናልፍ አንዷለም ፓርቲያችን ብልጽግና የአገራችንንና አለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን በጥልቀት የገመገመ፣አገራችንን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን በውል ለይቶ ትክክለኛ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ያስቀመጠ፣ሁሉንም የኢትዮጵያ ህዝቦች በእኩል አካቶና አቅፎ የማታገያ ሜዳ ያመቻቸ፣በሚሊዬን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን በአባልነትና በደጋፊነት ከጎኑ ያሰለፈ፣በለውጥ ውስጥ የተወለደ፣ለለውጥ የሚተጋ፣የተስፋ ብርሐን የሰነቀ የዛሬና የነገ ፓርቲ ነው ብለዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ ፓርቲው በምርጫ ወቅት የሚጠቀምበትን ማኒፌስቶና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክትን ይፋ አድርገዋል፡፡

በመድረኩ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ በርካታ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
7.4K views06:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-15 09:21:27 በጊኒ በኢቦላ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ የበሽታው መቀስቀስ ይፋ ተደረገ!

በጊኒ ደቡብ ምስራቃዊ ግዛት በኢቦላ የሶስት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን አራት ሰዎች ደግሞ ክፉኛ ታመዋል፡በላይቤሪያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ ስፍራ የቀብር ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት ሶስት ሰዎች የደም መፍሰስ ፣ ማስመለስና ፣ ተቅማት ምልክቶች ታይቶባቸዋል፡፡

በኢቦላ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ በለይቶ ማቆያ እንዲገቡ መደረጋቸውን የጊኒ የጤና ሚኒስትር አስታውቋል፡፡የጤና ሚኒስትሩ ሪማይ ላማህ በኢቦላ የሰዎች ህለፈት መመዝገቡ ስጋት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡ጊ ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር በመሆን በኢቦላ የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ የኢቦላ ክትባት እንደምትሰጥ አስታውቃለች፡፡እ.ኤ.አ ከ 2013 እስከ 2016 ባሉት ዓመታት በጊኒ ፣ ላይቤሪያ ፣ ሴራሊዮን ፤ በኢቦላ የተነሳ የ11,300 ሰዎች ህልፈት መመዝገቡ ይታወቃል፡፡

Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
8.6K views06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-15 09:19:34
ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ

@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com

0953707070
8.9K views06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-14 21:10:33
ሱዳን የቀድሞው ገዢ ፓርቲ አባላት ተይዘው እንዲከሰሱ ወሰነች!

የአልበሽር ደጋፊዎች ከያሉበት እንዲታደኑ እና ክስ እንዲመሰረትባቸው ውሳኔ ተላልፏል፡፡የቀድሞውን ም/ፕሬዝዳንት ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት ባለፈው ሳምንት መያዛቸው ይታወሳል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
19.1K views18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-14 15:45:02
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሻምቡ ባኮን የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ በይፋ መርቀው ስራ አስጀመሩ።

መንገዱ ከ60 ኪሎሜትር በላይ ርዝመት ያለው ነው።በተጨማሪም የሻምቡ ሀገምሳ የ95 ኪሎሜትር መንገድ ፕሮጀክት የማስጀመር ስነስርአትም ተካሂዷል።ከኦቢኤን የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው ግንባታውን የማስጀመር እና የምረቃ ስነስርአቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፥ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፥ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰመስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በሆሮ ጉዱሩ ዞን ሻምቡ ከተማ ተካሂዷል።

[OBN/Walta]
@YeneTube @FikerAssefa
20.9K views12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-14 10:15:01
ሦስት መቶ አርባ ሦስት ዜጎች ከሳዑዲ አረብያ ወደ አገራቸው ተመለሱ!

ሦስት መቶ አርባ ሦስት ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረብያ ጂዳ ከተማ ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይረክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
20.2K views07:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-14 05:13:56
ዶናልድ ትራምፕ የቀረበባቸው ክስ በሴኔቱ ውድቅ ተደረገ!

በፈረንጆቹ ጃንዋሪ 6 አመፅን አነሳስተዋል በሚል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ክስ የቀረበባቸው የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይከሰሱ አይከሰሱ የሚለውን ለመወሰን ዛሬ የተሰበሰበው ሴኔት 57 ለ 43 በሆነ አብላጫ ድምፅ እንዳይከሰሱ ወስኗል። ክሱ ተፈፃሚ እንዲሆን የሴኔቱ ሁለት ሶስተኛ ወይም 67 ድምፅ ያስፈልግ ነበር። ሁሉም የዴሞክራት ፓርቲ ተወካዮች ትራምፕ እንዲከሰሱ ድምፅ የሰጡ ሲሆን 7 ሪፐብሊካኖችም ተባብረዋቸዋል። ዶናልድ ትራምፕ በተመሳሳይ ሂደት ውስጥ ሲያልፉ ይሄኛው ለሁለተኛ ጊዜያቸው ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
20.5K views02:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ