Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 127.33K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 483

2021-02-10 11:27:26
የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል እርዳታ ለመስጠት የሚያስችለውን አንድ እርምጃ ወደፊት ተራምዷል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጀት አደነቀ፡፡

ላለፉት ተከታታይ ሳምንታት የድርጅቱ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲን ጨምሮ የተለያዩ አካላት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ አስቻይ መንገዶች አልተመቻቹም፤ የእርዳታ ሰጪ ተቋማትና ሰራተኞቻቸው ወደስፍራው እንዳያቀኑ ተከልከለዋል በሚል መንግስትን ሲወቅሱ ሰንበተዋል፡፡ምንም እንኳን መንግስት ወቀሳውን ውድቅ እንዳደረገው ቢቀጥልም የመንግስታቱ ድርጅት ግን ለመጀመሪያ ጊዜ 25 የበጎ አድራጊ ሰራተኞችን ያቀፈ ቡድን ድጋፍ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ መንግስት የይለፍ አረንጓዴ መብራት እንዳሳየ አስታውቋል፡፡

[አሐዱ ራዲዮ 94.3]
@YeneTube @FikerAssefa
15.6K views08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-10 11:24:13 በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለአቶ ጃዋር መሀመድ አራት የሞባይል ሲም ካርድ ሊያቀብል ሲል በቁጥጥር ስር ውሏል የተባለው ግለሰብ ዋስትና ተፈቀደለት፡፡

ተጠርጣሪ ሀምዛ ጀማል አንድ በOMN ድርጅት ስም እና 3 በግለሰብ ስም የወጡ ሲም ካርዶችን ለአቶ ጃዋር መሀመድ ሊያቀብል ሲል በማረሚያ ቤቱ የጥበቃ አባላት በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሎ ከአንድ ወር በላይ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ሲደረግበትና ለአራት ጊዜ ፍርድ ቤት ሲቀርብ ቆይቷል።

በምርመራው መርማሪ ፖሊስ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ምስክር ቃል መቀበሉን ከኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርዱ በማን ሰም ስለመውጣቱ ማስረጃ መሰብሰቡን ገልጾ ነበር፡፡

ምርመራ መዝገቡን አቃቤ ህግ እየተመለከተው መሆኑን እንዲሁም ተጨማሪ ምስክር ለመቀበል ተጨማሪ የምርመራ ቀናትን ጠይቆ የነበረ ሲሆን የተጠርጣሪ ጠበቃ በቂ ጊዜ ተሰጥቷል ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁ አግባብ አደለም ሲል ተቃውሞ ተከራክሮ ነበር፡፡

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት መርማሪ ያቀረበው የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ተጨማሪ ጊዜ ለመስጠት አሳማኝ ምክንያት አይደለም ሲል አልተቀበለውም፡፡

እስካሁን የተከናወኑ የምርመራ ቀናት በቂ ናቸው ሲል ተጠርጣሪው የ30 ሺህ ብር ዋስ አስይዞ ከእስር እንዲፈታ ዋስትና ፈቅዷል፡፡

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ
@YeneTube @FikerAssefa
15.1K views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-10 10:33:47 በመቀለ ከተማ በነበረ ተቃውሞ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ!

በመቀለ ከተማ በነበረው ተቃውሞ አንድ ግለሰብ በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ ማለፉን አጃንስን ፍራንስ ፕሬስ የህክምና ምንጮች ጠቅሶ ዘግቧል።በትላንትናው እለት በመቀሌ ከተማ በርካታ የንግድ ተቋማት ዝግ በማድረግ ነዋሪዎች ቁጣቸውን ገልፀዋል። መንግስት በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ ሰላማዊ በማስመሰል ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማጋራት እየጣረ ነው ይህ ግን የሀሰት ነው ሲል ነዋሪዎች አነጋግሬአለው ያለው ዘገባው አመላክቷል።

መንግስት ተገዶ በገባበት በዚህ ግጭት በወርሃ ጥቅምት ማብቂያ የህወሃት ቡድን በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መሰንዘሩ አይዘነጋም።ከትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚቀርቡ ወቀሳዎች በመረጃ ያልተደገፉ ናቸው ሲሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ አቶ ለማ ተሰማ መናገራቸው ይታወሳል።

ዳጉ ጆርናል
@YeneTube @FikerAssefa
10.8K views07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-10 10:31:18
ለ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ የሚያስፈልጉ የመራጮች እና እጩ ምዝገባ ቅፆች እና ቁሳቁሳችን ከዛሬ ጀምሮ ማጓጓዝ እንደሚጀምር ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ለቀጣዩ ሃገራዊ ምርጫ የሚደረጉ ዝግጅቶች በአብዛኛው መጠናቀቃቸውንም ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ በመግለጫው እንደገለፁት፣ በሀገራችን የትግራይ ክልልን ሳይጨምር 673 የምርጫ ክልሎች መቋቋማቸውን ገልዋል።በአዲስ አበባ እንዲሁም በዞን ከተማዎችና ወረዳዎችን ጨምሮ የምርጫ ቢሮዎችና ፅህፈት ቤቶች በመከፈት ላይ እንደሚገኙም አውስተዋል።

ለምርጫ አስፈጻሚዎችም ስልጠና ተሰቷል፣ ቁሳቁሶችም ተሟልተዋል ብለዋል።ለእጩዎችና ለመራጮች ምዝገባ የሚያገለግሉ ቅፆችና ቁሳቁሶች የተዘጋጁ መሆናቸውን የገለጹት ምክትል ሰብሳቢው፣ ቅፆቹና ቁሳቁሶቹ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ተዘጋጁት የምርጫ ክልሎች የማሰራጨትና የማጓጓዝ ስራው ይጀመራል ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
14.5K viewsedited  07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-10 10:09:48
ጉዳፍ ፀጋይ በሌቪን ፈረንሳይ በተካሄደ የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አዲስ የአለም ክብረወሰን አስመዘገበች።

አትሌቷ በፈረንጆቹ 2014 አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በካርልስሩህ ያስመዘገበችውን ክብረወሰን በ2 ሰከንድ በማሻሻል ርቀቱን በ3:53.09 ማጠናቀቅ ችላለች።

አትሌት ለምለም ሀይሉም በዚሁ የፈረንሳይ የቤት ውስጥ ሻንፒዮና ውድድር በ3000 ሜትር 8:32,55 በመሮጥ ስታሸንፍ፣ አትሌት ሀብታም አለሙ በ800 ሜትር 2:00;86 በመሮጥ 2ኛ ሆናለች።

በዚሁ የቤት ውስጥ ውድድር በ3,000 ሜትር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1-4ኛ መውጣት ችለዋል፡፡

በዚሁ መሰረት አትሌት ጌትነት ዋለ 1ኛ፣ ሰለሞን ባረጋ 2ኛ፣ ለሜቻ ግርማ 3ኛ ፣ በሪሁ አረጋዊ 4ኛ፣ ታደሰ ወርቁ 6ኛ በመሆን ጨርሰዋል፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
14.4K views07:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-10 09:46:30
ግብፅ በኤርትራ የባህር ግዛት ላይ ፈቃድ ሳይኖራቸው በመገኘታቸው የተያዙት ግብፃውያን ዓሳ አጥማጆች እንደሆኑ በመጥቀስ ዜጎቿ እንዲለቀቁ የኤርትራን መንግሥት ጠየቀች።

በአምስት ጀልባዎች በመሆን በኤርትራ የባህር ክልል ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የተገኙትን ግብፃዊያን የኤርትራ የባህር ኃይል በቁጥጥር ሥር ያዋለው ባለፈው ወር መሆኑን መረጃዎች የሚያመለክቱ ሲሆን፣ ‹‹ዓሳ አጥማጆች ናቸው›› የተባሉትን ግብፃዊያን ለማስለቀቅም የግብፅ መንግሥት ኦፊሳላዊ ጥያቄ ለኤርትራ መንግሥት ማቅረቡ ተሰምቷል።

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
15.6K views06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-10 09:43:53
ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ

@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com

0953707070
6.2K views06:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-09 22:01:46
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገነባው በሀገራችን የመጀመሪያው ትልቁና ዘመናዊ የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታል ተጠናቀቀ ።

በ20,000 ካሬ ላይ ያረፈው ፣ 400 በላይ ተኝቶ መታከሚያ አልጋዎች ያሉት፣100 የልህቀት ማዕከል አገልግሎት መስጫ ክፍሎች፣በተመሳሳይ ሰአት ለ7 እናቶች የኦፕራሲዮን አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው ዘመናዊና ወረቀት አልባ መስተንግዶ የሚሰጠው ይህ ሆስፒታል ዘመናዊ የህክምና ቁሳቁሶች ተሟልተውለታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤናው ዘርፍ በተለይ በወሊድ እና ተያያዥ ጉዳዮች በእናቶች እና ህጻናት የሚደርሰውን የሞት ምጣኔ ለመቀነስ በአይነቱ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነና ደረጃውን የጠበቀ የእናቶች እና ህጻናት ሆስፒታል ግንባታ ያጠናቀቀ ሲሆን በክብርት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የካቲት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ተመርቆ ስራ የሚጀምር ይሆናል።

ግንባታው ቀድሞ ለመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ተብሎ የተጀመረ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩም ካቢኔ በከተማችን ትልቅ የአገልግሎት ችግር ያለበትን የእናቶችና ህጻናት ጤና ቅድሚያ በመስጠት ሰባት መቶ ሚሊየን ብር በመመደብ ተጨማሪ ግንባታ በማድረግ እና ነባሩን ግንባታ በማሻሻል ወደ ሆስፒታልነት እንዲቀየር አድርጓል።

[Addis Ababa city PS]
@YeneTube @FikerAssefa
17.3K views19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-09 21:08:50
ጀርመን ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን ወደ ሃገራቸዉ መጠረዝዋን ቀጥላለች። በጀርመን ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እና የሰብዓዊ ጉዳይ አቀንቃኞች ይህን የጀርመን መንግሥትን ርምጃ እያወገዙ ነዉ። የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭት እጅግ ባየለበት እና ኢትዮጵያ ዉስጥ በትግራይ እና በተለያዩ ክልሎች የተለያዩ ተግዳሮት ባለበት በአሁኑ ወቅት በጀርመን የጥገኝነት ጥያቄ ያቀረቡ ኢትዮጵያዉያን ወደ ሃገራቸዉ እንዲመለሱ መደረጉ ስህተት ነዉ ሲሉ የሰብዓዊ ጉዳይ አቀንቃኞች ተናግረዋል።በጎርጎረሳዉያኑ 2020 ዓመት ብቻ ከጀርመን 20 ኢትዮጵያዉያን ወደ ሃገራቸዉ እንዲመለሱ ተደርጎአል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
17.1K views18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-09 19:11:13
በትግራይ ክልል ሕፃፅና ሽመልባ በተባሉ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የነበሩ 20,000 የሚጠጉ ኤርትራውያን ስደተኞች፣ መንግሥት ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ሲያከናውን በነበረው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ የመጠለያ ጣቢያዎቹን ለቀው እንደወጡ ተገለጿል፡፡

ዘገባው የሪፖርተር ነው ተጨማሪ ለማንበብ: http://bit.ly/3tFIX9B

@YeneTube @FikerAssefa
17.1K views16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ