Get Mystery Box with random crypto!

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለአቶ ጃዋር መሀመድ አራት የሞባይል ሲም ካርድ ሊያቀብል ሲል በቁጥጥር ስ | YeneTube

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለአቶ ጃዋር መሀመድ አራት የሞባይል ሲም ካርድ ሊያቀብል ሲል በቁጥጥር ስር ውሏል የተባለው ግለሰብ ዋስትና ተፈቀደለት፡፡

ተጠርጣሪ ሀምዛ ጀማል አንድ በOMN ድርጅት ስም እና 3 በግለሰብ ስም የወጡ ሲም ካርዶችን ለአቶ ጃዋር መሀመድ ሊያቀብል ሲል በማረሚያ ቤቱ የጥበቃ አባላት በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሎ ከአንድ ወር በላይ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ሲደረግበትና ለአራት ጊዜ ፍርድ ቤት ሲቀርብ ቆይቷል።

በምርመራው መርማሪ ፖሊስ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ምስክር ቃል መቀበሉን ከኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርዱ በማን ሰም ስለመውጣቱ ማስረጃ መሰብሰቡን ገልጾ ነበር፡፡

ምርመራ መዝገቡን አቃቤ ህግ እየተመለከተው መሆኑን እንዲሁም ተጨማሪ ምስክር ለመቀበል ተጨማሪ የምርመራ ቀናትን ጠይቆ የነበረ ሲሆን የተጠርጣሪ ጠበቃ በቂ ጊዜ ተሰጥቷል ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁ አግባብ አደለም ሲል ተቃውሞ ተከራክሮ ነበር፡፡

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት መርማሪ ያቀረበው የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ተጨማሪ ጊዜ ለመስጠት አሳማኝ ምክንያት አይደለም ሲል አልተቀበለውም፡፡

እስካሁን የተከናወኑ የምርመራ ቀናት በቂ ናቸው ሲል ተጠርጣሪው የ30 ሺህ ብር ዋስ አስይዞ ከእስር እንዲፈታ ዋስትና ፈቅዷል፡፡

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ
@YeneTube @FikerAssefa