Get Mystery Box with random crypto!

በመቀለ ከተማ በነበረ ተቃውሞ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ! በመቀለ ከተማ በነበረው ተቃውሞ አንድ | YeneTube

በመቀለ ከተማ በነበረ ተቃውሞ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ!

በመቀለ ከተማ በነበረው ተቃውሞ አንድ ግለሰብ በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ ማለፉን አጃንስን ፍራንስ ፕሬስ የህክምና ምንጮች ጠቅሶ ዘግቧል።በትላንትናው እለት በመቀሌ ከተማ በርካታ የንግድ ተቋማት ዝግ በማድረግ ነዋሪዎች ቁጣቸውን ገልፀዋል። መንግስት በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ ሰላማዊ በማስመሰል ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማጋራት እየጣረ ነው ይህ ግን የሀሰት ነው ሲል ነዋሪዎች አነጋግሬአለው ያለው ዘገባው አመላክቷል።

መንግስት ተገዶ በገባበት በዚህ ግጭት በወርሃ ጥቅምት ማብቂያ የህወሃት ቡድን በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መሰንዘሩ አይዘነጋም።ከትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚቀርቡ ወቀሳዎች በመረጃ ያልተደገፉ ናቸው ሲሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ አቶ ለማ ተሰማ መናገራቸው ይታወሳል።

ዳጉ ጆርናል
@YeneTube @FikerAssefa