Get Mystery Box with random crypto!

ለ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ የሚያስፈልጉ የመራጮች እና እጩ ምዝገባ ቅፆች እና ቁሳቁሳችን ከዛሬ ጀም | YeneTube

ለ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ የሚያስፈልጉ የመራጮች እና እጩ ምዝገባ ቅፆች እና ቁሳቁሳችን ከዛሬ ጀምሮ ማጓጓዝ እንደሚጀምር ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ለቀጣዩ ሃገራዊ ምርጫ የሚደረጉ ዝግጅቶች በአብዛኛው መጠናቀቃቸውንም ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ በመግለጫው እንደገለፁት፣ በሀገራችን የትግራይ ክልልን ሳይጨምር 673 የምርጫ ክልሎች መቋቋማቸውን ገልዋል።በአዲስ አበባ እንዲሁም በዞን ከተማዎችና ወረዳዎችን ጨምሮ የምርጫ ቢሮዎችና ፅህፈት ቤቶች በመከፈት ላይ እንደሚገኙም አውስተዋል።

ለምርጫ አስፈጻሚዎችም ስልጠና ተሰቷል፣ ቁሳቁሶችም ተሟልተዋል ብለዋል።ለእጩዎችና ለመራጮች ምዝገባ የሚያገለግሉ ቅፆችና ቁሳቁሶች የተዘጋጁ መሆናቸውን የገለጹት ምክትል ሰብሳቢው፣ ቅፆቹና ቁሳቁሶቹ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ተዘጋጁት የምርጫ ክልሎች የማሰራጨትና የማጓጓዝ ስራው ይጀመራል ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa