Get Mystery Box with random crypto!

ጉዳፍ ፀጋይ በሌቪን ፈረንሳይ በተካሄደ የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አዲስ የአለም ክብረወሰ | YeneTube

ጉዳፍ ፀጋይ በሌቪን ፈረንሳይ በተካሄደ የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አዲስ የአለም ክብረወሰን አስመዘገበች።

አትሌቷ በፈረንጆቹ 2014 አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በካርልስሩህ ያስመዘገበችውን ክብረወሰን በ2 ሰከንድ በማሻሻል ርቀቱን በ3:53.09 ማጠናቀቅ ችላለች።

አትሌት ለምለም ሀይሉም በዚሁ የፈረንሳይ የቤት ውስጥ ሻንፒዮና ውድድር በ3000 ሜትር 8:32,55 በመሮጥ ስታሸንፍ፣ አትሌት ሀብታም አለሙ በ800 ሜትር 2:00;86 በመሮጥ 2ኛ ሆናለች።

በዚሁ የቤት ውስጥ ውድድር በ3,000 ሜትር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1-4ኛ መውጣት ችለዋል፡፡

በዚሁ መሰረት አትሌት ጌትነት ዋለ 1ኛ፣ ሰለሞን ባረጋ 2ኛ፣ ለሜቻ ግርማ 3ኛ ፣ በሪሁ አረጋዊ 4ኛ፣ ታደሰ ወርቁ 6ኛ በመሆን ጨርሰዋል፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa