Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል እርዳታ ለመስጠት የሚያስችለውን አንድ እርምጃ ወደፊት ተራምዷል | YeneTube

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል እርዳታ ለመስጠት የሚያስችለውን አንድ እርምጃ ወደፊት ተራምዷል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጀት አደነቀ፡፡

ላለፉት ተከታታይ ሳምንታት የድርጅቱ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲን ጨምሮ የተለያዩ አካላት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ አስቻይ መንገዶች አልተመቻቹም፤ የእርዳታ ሰጪ ተቋማትና ሰራተኞቻቸው ወደስፍራው እንዳያቀኑ ተከልከለዋል በሚል መንግስትን ሲወቅሱ ሰንበተዋል፡፡ምንም እንኳን መንግስት ወቀሳውን ውድቅ እንዳደረገው ቢቀጥልም የመንግስታቱ ድርጅት ግን ለመጀመሪያ ጊዜ 25 የበጎ አድራጊ ሰራተኞችን ያቀፈ ቡድን ድጋፍ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ መንግስት የይለፍ አረንጓዴ መብራት እንዳሳየ አስታውቋል፡፡

[አሐዱ ራዲዮ 94.3]
@YeneTube @FikerAssefa