Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገነባው በሀገራችን የመጀመሪያው ትልቁና ዘመናዊ የእናቶችና ህፃና | YeneTube

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገነባው በሀገራችን የመጀመሪያው ትልቁና ዘመናዊ የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታል ተጠናቀቀ ።

በ20,000 ካሬ ላይ ያረፈው ፣ 400 በላይ ተኝቶ መታከሚያ አልጋዎች ያሉት፣100 የልህቀት ማዕከል አገልግሎት መስጫ ክፍሎች፣በተመሳሳይ ሰአት ለ7 እናቶች የኦፕራሲዮን አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው ዘመናዊና ወረቀት አልባ መስተንግዶ የሚሰጠው ይህ ሆስፒታል ዘመናዊ የህክምና ቁሳቁሶች ተሟልተውለታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤናው ዘርፍ በተለይ በወሊድ እና ተያያዥ ጉዳዮች በእናቶች እና ህጻናት የሚደርሰውን የሞት ምጣኔ ለመቀነስ በአይነቱ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነና ደረጃውን የጠበቀ የእናቶች እና ህጻናት ሆስፒታል ግንባታ ያጠናቀቀ ሲሆን በክብርት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የካቲት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ተመርቆ ስራ የሚጀምር ይሆናል።

ግንባታው ቀድሞ ለመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ተብሎ የተጀመረ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩም ካቢኔ በከተማችን ትልቅ የአገልግሎት ችግር ያለበትን የእናቶችና ህጻናት ጤና ቅድሚያ በመስጠት ሰባት መቶ ሚሊየን ብር በመመደብ ተጨማሪ ግንባታ በማድረግ እና ነባሩን ግንባታ በማሻሻል ወደ ሆስፒታልነት እንዲቀየር አድርጓል።

[Addis Ababa city PS]
@YeneTube @FikerAssefa