Get Mystery Box with random crypto!

በርሀብ አድማ ላይ የሚገኙት የእነ አቶ ጃዋር መሃመድ እና አቶ በቀለ ገርባን የሚከታተል የግል ሃኪ | YeneTube

በርሀብ አድማ ላይ የሚገኙት የእነ አቶ ጃዋር መሃመድ እና አቶ በቀለ ገርባን የሚከታተል የግል ሃኪሞቻቸው ቡድን ሲያደርግላቸው የቆየውን የህክምና ክትትል ማቆሙን አስታውቋል።

የህክምና ቡድኑ አስተባባሪ ዶ/ር ኢሊሊ ጀማል ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት የህክምና ክትትሉን ከትናንት ምሽት ጀምሮ ለማቆም የተገደዱት በማረሚያ ቤት እና በታካሚዎች በኩል ያለው ፍላጎት ባለመጣጣሙ ነው ብለዋል፡፡ ማረሚያ ቤቱ ወደ መንግስት ህክምና ማዕከል እንዲወሰዱ ፍላጎት ሲያሳይ ታካሚዎች ደግሞ በግል ሆስፒታል ለመታየት በመፈለጋቸው ቡድኑ ህክምናውን መስጠት አለመቻሉም ተገልጿል። 

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa